የዳዕዋ ጉዞ በካንፓስ ተማሪዎች

Author picture

የዳዕዋ ጉዞ በካንፓስ ተማሪዎች በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

ምስጋናና ልቅና ለአሏህ ይገባው። አሏህ የመራውን ማንም አያጠምም፤ አሏህ ያጠመመውን ማንም አይመራም።

የአሏህ ሰላም እና እዝነት በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶሃቦቻቸቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን። አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል ኢምራን አንቀፅ 104 ላይ እንዲህ ይላል:-

ከእናንተም ወደ በጐ ነገር የሚጣራ ፣ በመልካም ስራ የሚያዝ ፣ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ህዝቦች ይኑሩ። እነዚያ እነሱ የሚድኑ ናቸው።

{አል-ቁርአን 3:104}

እንዲሁም አሏህ በሱረቱል ፋሲለት አንቀፅ 33 ላይ እንዲህ ይላል:-

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

{አል-ቁርአን 41:33}

በሰኺኽ ሙስሊም እንደተዘገበው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከእናንተ መካከል መጥፎን የተመለከተ በእጁ ያስቁም። ይህን ማድረግ ያልቻለ በምላሱ ያድርግ። ይህንን ማድረግ ያልቻለ ከልቡ ይጥላ። እናም ያ ትንሹ የኢማን ደረጃ ነው ብለዋል።

በመልካም ነገር ማዘዝና ከመጥፎ ነገር መከልከል በኢስላም ትልቅ ሃላፊነት ሲሆን ኡለማዎች ይህን የተቀደሰ ተግባር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው ብለዋል።

ምክርን እንለዋወጥ ዘንድ ሌሎችን መልካም ወደሆነ ነገር እናመላክት ዘንድ እና እርስበርሳችነም እውነት በሆነ ነገርና በትዕግስት አደራ አደራ እንባባል ዘንድ ታዘናል። ደህንነታችን የሚረጋገጠው በዚህ ላይ ሲሆን እሱን ችላ ማለት ደግሞ ውጤቱ የከፋ ነው።

አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል አል-ዐስር ከአንቀፅ 1 እስከ 3 ባለው እንዲህ ይለናል

“በጊዜያት እምላለሁ። በእርግጥ ሰው ሁሉ በኪሳራ ውስጥ ነው። እነዚያ ያመኑት ፣ መልካም ስራን የሰሩት ፣ በእውነት እና በትዕግስት አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።”

{አል-ቁርአን 113:1-3}

እንደሚታወቀው ክረምት ሲጠባ ትምህርት ቤቶች ሁሉ ይከፈታሉ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም በራፋቸውን ከፍተው ተማሪዎችን ያስተናግዳሉ።

ሁሉም ዲፓርትመንቶችም ተማሪዎቻቸቸውን በwellcome fresh ይቀበላሉ። በዚህ ወቅት የሚሰራው ፋህሻ እጅግ የከፋ ሲሆን ወደ ሸይጧን መንገድ የሚጣራው በጣም ብዙ ነው።

ታዲያ አንዳንድ ሙስሊም ሴቶችም ሆኑ ወንዶች በካንፓስ ውስጥ ሲኖሩ የብቸኝነት ወይም የነፃነት ስሜት ስለሚሳማቸው ሊሆን ይችላል የተለያዩ ወንጀሎችን ሲሰሩ ይስተዋላል። የዳዕዋ ጉዞ በካንፓስ ተማሪዎች

ሆኖም ይህ አጋጣሚ የኢስላምን መልዕክት ለማስተላለፍ እራሳቸውን ላዘጋጁ ወንድሞች ትልቅ አጋጣሚ ነው። ቢሆንምግን ይህን ተግባር የካንፓሱ አሚሮች እንኳ ሳይቀሩ ችላ ሲሉት ይስተዋላል።

እውቀት ኖሮት እውቀቱን የደበቀ ሰው ውጤቱ የከፋ ነው። በሐዲስ እንደተዘገበው አሏህ የውመል ቂያማ ከጀሃነም እሳት በሆነ ልጓም ይለጉምዋል።

ምን ማድረግ ይጠበቅብናል

  • በግቢያችን ውስጥ ወጣ ያለ ባህሪ ያላቸው እህት ወንድሞቻችን እነማናቸው?
  • ዚያራ ሴክተር ላይ ምንያህል እየተሰራ ነው?
  • በእያንዳንዱ ስራችን ላይ ምን ያህል ትብብር አለን?
  • የዳዕዋ ሴክተር ድርሻ እስከምን ድረስ ነው?
  • በዳዕዋ ሴክተርና በዚያራ ሴክተር ያለው ቁርኝት ምን ይመስላል? ሁለቱን ሴክተሮች አንድ ላይ እንዴት ማስኬድ እንችላለን?
  • ጀመአችን ላይ አህላቃቸው የተበላሸ ሰብሴክተር ላይ ያሉ ሰዎችም ሆኑ አሚሮች እነማናቸው? ሙስሊም ተማሪዎች ከነዚህ ሰዎች ምን ይማራል?
  • ፍሬሽ እህት ወንድሞቻችነን እንዴት ነው የምንቀበለው?
  • ወደ ጀመአችን ለማምጣትስ ምን ያህል ጥረት እናደርጋለን?

እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን በማንሳት መልስ ማፈላለግ እና ጠንካራ መሠረት ያለው ጀመአ ለመፍጠር መጣር ይኖርብናል።

ኢንሻ አሏህ! በክፍል ሁለት የሙስሊም ወጣቶች የዳዕዋ ጉዞ በሚል ርዕስ ስር እውን ወጣቶች ዳዕዋ ማድረግ ይችላሉን? ዳዕዋ ከማድረጋችን በፊት ልንላበሳቸው የሚገቡ ባህሪያት ምንምን ናቸው? እንዴትስ ዳዕዓውዋ ማድረግ እንችላለን? የሚሉ ንዑስ አርዕስቶችን እንዳስሳለን።

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top