ከአንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም

መስተካከልን አስበን ወደ አሏህ ለመመለስ ከቆረጥን አሏህ በባሮቹ ላይ አይጨክንም። የውሸት ኑሮን አንኑር ወደ አሏህ (ሱ.ወ.ተ) ብንመለስ ነው የሚሻለው። ከአንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም ነው ነገሩ።

እንስተካከል ነገሮች ሁሉ ይስተካከሉልናል። ከህይወት ወከባ እናርፋለን፤ ወደ ማይቀረው አለም ስንሄድ አንፈራም እንደፍራለን። መስተካከል የአሏህ እዝነት ነው። ጥመት ደግሞ የእሱ ቁጣ ነው። ለዚህም ነው በግዴታ ሶላቶቻችን ብቻ በቀን 17 ጊዜ አሏህን ቀጥተኛውን ጎዳና ይመራን ዘንድ የምንለምነው።

አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል ፋቲሃ ከአንቀፅ 6-7 ባለው እንዲህ ይላል፡-

“ቀጥተኛውን መንገድ ምራን። የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በእነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን።”

{አል-ቁርአን 1:6-7}

ዱንያ አስቸጋሪ ድልድይ ናት። መሰናክሎች ፣ ጉቶዎችና መንጠቆዎች ይበዙባታል። ስሜት ፣ ስጋ ፣ ነፍስ ፣ ሸይጧን ፣ ሰዎችም ጭምር መልካሙን ሰው ከመልካም ጎዳና ለማውጣት ከዚህም ከዚያም ይመነታትፉታል። ታዲያ የነገን አስቸጋሪ የጀሃነም ድልድይ ልናልፍ የምንችለው የዱንያን ድልድይ በብቃት ስንሻገር ነው።

እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ወደ ቁርአን ወደ ሱና እንመለስ። እራስችንን እናስተካክል። መስለን ከመታየት ይልቅ ሆነን መገኘትን ምርጫችን እናድርግ። ምንግዜም ዱአ ባደረግን ቁጥር ያ-ረቢ ጌታየ ቀጥተኛውን መንገድ ከመራሃቸው ባሪያውችህ መካከል አድርገኝ ማለትን አንዘንጋ።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top