የኢብን ከሲር የህይወት ታሪክ

ኢማድ አድዲን ኢስማኤል ኢብን ኡመር ኢብን ከሲር አል-በስሪ አዲመሽቂ የተወለዱት በ700 ዐ.ሂ ሲሆን አባታቸው የሞቱት የሰባት አመት ልጅ እያሉ ነው።

በታላቅ መንድማቸው በመታጀብ ወደ ደማስቆ አቀኑ፤ ብዙ እውቀት ከኢብን ሻኪር አል-አመዲ እና ከለሌሎችም ሻቱ።

ከሚታወቁባቸው ስራዎች መካከል አል-ቢዳያ ወኒሃያ (የመጀመሪያው እና የመጨረሻው) ይገኝበታል። የሰኺህ አል-ቡኻሪ ከፊሉን ተንትነዋል።

በቁርአን እና በታሪክ ትንተናቸው በደንብ ይታወቃሉ። ኢብን ሐቢብ በቁርአን ትንተና የተሰማሩ ሰዎች ሁሉ መሪ ሲሉ ገልፀዋቸዋል። ፈትዋቸው በተለያዩ አገራት ዝናን እና ተቀባይነት አግኝቷል።

ሰኺህ ሐዲሶችን የመሸምደድ ፣ የአንድን ሐዲስ ደረጃ ፣ የታሪኮችን ታማኝነት የመገምገም እና ሰኺህ የሆኑ ሐዲስሶችን ዶኢፍ ከሆኑ ሐዲሶች የመለየት ብቃት ነበራቸው።

ኢብን ከሲር የአይን ብርሃናቸውን ያጡት ከመሞታቸው ከጥቂት ጊዜ በፊት ሲሆን የሞቱትም በ774 ዐ.ሂ ነበር። የተቀበሩትም ከጓዳቸው ከኢብን ተይሚያ ጋር ከሱፊዮች መቃብር ነበር።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top