አንድ አይነበሲር ልጅ ከአንድ ህንፃ መወራረጃ ላይ ኮፍያ ይዞ ተቀምጧል፤ ልጁም አይነበሲርነኝ እባካችሁ እርዱኝ የሚል መልዕክት የያዘ ሲሆን ከኮፍያው ያሉት ሳንቲሞች ትንሽ ነበሩ።
አንድ ሰው በጎኑ እየተጓዘ እያለ ከኪሱ ሳንቲሞችን አውጥቶ ኮፍያው አስቀመጠለትና ልጁ የያዘውን መልዕክት አንስቶ በመገልበጥ አዲስ ፅሑፍ ፅፎለት በልጁ ጎን የሚያልፉ ሰዎች እንዲያዩት ለእይታ ምቹ በሆነ መልኩ ፅፎ አስቀመጠው።
እናም ኮፍያው መሙላት ጀመረ በርካታ ሰዎችም ለዛ ልጅ ገንዘብ ሰጡት። ከቀትር ሰዓት ብኋላ ያ መልዕክቱን ቀይሮ የፃፈለት ሰውየ እንዴት እንደሆነ ሁኔታውን ሊመለከት መጣ።
ልጁም የእግርኮቴውን ተከታትሎ እየተጠራጠረ ጧት መልዕክቱን የቀየርከው አንተነህ? ምነበር የፃፍከው? ሲል ጠየቀው። ሰውየውም ያልከውን ነገር በተለየ መንገድ ነበር የፃፍኩት አለው።
የፃፈውም ዛሬ ቆንጆና ውብ የሆነ ቀን ነው ነገርግን እኔ አላየውም የሚል ነበር። የመጀመሪያውና ሁለተኛው መልዕክት ተመሳሳይ ነገር የሚሉ ይመስላችኋል።
በእርግጥ ሁለቱም መልዕክቶች ልጁ አይነበሲር እንደሆነ ለሰዎች ያስተላልፋሉ። ነገርግን የመጀመሪያው መልዕክት የሚለው ልጁ አይነበሲር ነኝ ነው።
ከዚህ ባሻገር ግን ሁለተኛው መልዕክት ሰዎች አይነበሲር ባለመሆናቸው እድለኞች መሆናቸውን የሚያስታውስ መልዕክት ነው። ታዲያ ሁለተኛው መልዕክት የሰዎችን ቀልብ የሚስብ ቢሆን ምን ያስገርማል?
አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል አል-ሉቅማን አንቀፅ 20 ላይ እንዲህ ይላል:-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ሉቅማን 31:20)
“ፀጋዎቹም ግልፅም ድብቅም ሲሆኑ የሞላችሁ መሆኑን አታዩምን።”
አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል ሙዕሚኑን አንቀፅ 78 ላይ እንዲህ ይላል:-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ሙዕሚኑን 23:78)
እርሱ ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው። ጥቂትን እንጂ አታመሰግኑም።
እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ የአሏህ ፀጋዎች እጅግ በጣም በርካታዎች ናቸውና አስብና አመስግን።




Share