ሶላትን አደራ

ሶላትን አደራ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ በመታገስ እና በሶላት ተረዱ፤”

{አል-ቁርአን 2:153}

ፍርሃት ሲያካብብህ ሀዘን ሲያንዣብብህ እና ትካዜ ሊያስርህ ሲሻ ወዲያውኑ ወደ ሶላት ተነሳ ነፍስህ ትረጋጋለች ፤ ውስጥህም ሰላም ያገኛል። ሶላት በአሏህ ፈቃድ የሀዘንና የጭንቀት ባህርን የመቅዘፍ እንዲሁም ትካዜን የማባረር ኃይል አላት።

ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ጉዳይ ሲያስጨንቃቸው «ቢላል ሆይ በሶላት አሳርፈን» ይሉ ነበር። የዓይን ማረፊያቸውና የደስታ ምንጫቸውም ነበረች።

በተለያዩ የታሪክ ማህደሮችም ችግሮች ሲያጋጥሟቸው እና ጉዳዩች አልፈፅም ብለዋቸው መላ ሲያጡ ኹሹዕ ያላትን ሶላት ሰግደው ኃይላቸው ተመልሶላቸው ፣ ጉዳያቸው ተፈፅሞ ፣ ወኔያቸውም የሚመለስላቸው ሰዎች እንደነበሩ አንብቤያለሁ።

ጭንቅላቶች ተቆርጠው በሚበሩባቸው ፣ ነፍሶችም በሰይፍ ከአካላት የሚለዩባቸው የጦርነት ጊዜያት ፅናት ይኖርዘንድ እና እርጋታ ይሰፍን ዘንድም ሰላተል ኸውፍ ተደነገገ።

መንፈሳዊ በሽታዎች የወረሩት ይህ ትውልድ ከመስጅዶች ጋር መተዋወቅ አለበት ፤ ጌታውን ለማስደሰትና ከሚሳቀቅበት መሪር ስቃይ ለመላቀቅም ግንባሩን መሬት ላይ መድፋት አለበት። አለበለዚያ እንባዎች ዓይኑን ሲያቃጥሉት ይኖራል።

ሀዘንም ህዋሶቹን ይንድበታል። ከሶላት ውጭ ሰላምና መረጋጋትን ሊሰጠው የሚችል ኃይልም አያገኝም።

መገንዘብ የምንችል ብንሆን በየቀኑ የምንሰግዳቸው አምስቱ ሶላቶች እጅግ ከፍተኛ ከሆኑ ፀጋዎች ውስጥ እንደሚቆጠሩ እንገነዘብ ነበር። ምክኒያቱም ወንጀሎቻችን እንዲታበሱ ምክኒያት ናቸውና ፤ ጌታችን ዘንድ ደረጃችን ከፍ እንዲል ፤ ለጭንቀታችን እና ለበሽታዎቻችን ታላቅ ፈውስ ናቸው።

ልቦናችን ውስጥ መረጋጋትን ያፈሱባቸዋል ፤ አካሎቻችንንም በደስታ ይሞሏቸዋል። እነዚያ መስጅዶችን ርቀው ሶላትን የተዉ ሰዎች ግን ከጭንቀት ከሐዘንና ከጥበት ውስጥ ይዋኛሉ።

“ለነሱ ጥፋት ተገባቸው ፤ ሥራዎቻቸውንም አጠፋባቸው።”

{አልቁርአን 47:8}
Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top