አግብተሃል ወይስ ለማግባት እየተዘጋጀህ ነው

እንግዲያውስ እናት ለልጇ ከጋብቻ ቀኑ በፊት የሰጠችውን ምክር አንብብ!

ልጄ አሁንማ ጎልማሳ ሁነሃል፤ እናት የልጇን እራስ እያሻሸች…. ነገ ምግብህን አብሳይ እና ሚስጥርህን ሁሉ የምትጋራህ አዲስ እናት ይኖርሃል። ከዚህ ቡኋላ እኔ አልሆንም። እኔን ከምትወደኝ በላይም ቢሆን አዲሷ እናትህን ውደድ።

በእሷ እቅፍ ከመሆንህ በፊት ግን ትንሽ ልምከርህ!

ከአባትህ ጋር የተጨቃጨኩባቸው ፣ የተጯጯሁበት ጊዜ ነበር። ቁጣው ከባድ ነው። እኔም እሱም ቁጡ ነን። ደደብ ብየው አውቃለሁ። በንዴት እኔን እየተመለከተ እንዴት እንደዛ ብየ ልጠራው እንደደፈርኩ ይጠይቀኛል።

ወዲያውኑ ደደብ ፣ ቂል ፣ እብድ ብየ እሰድበዋለሁ። ምን እንደሚያደርግ ገምት…. ለመማታት እጁን አላነሳም። ወዲያውኑ በሩን ገጭ አድርጎት ወጥቶ ሄደ።

ልጄ አባትህ ቢመታኝ ፣ አይኔን ቢያጠፋኝ ኖሮ ዛሬ እዚህ እኔ ጋር በመቀመጥህ እንዴት ነበር የሚሰማህ? እንዳባትህ ታየው ነበር? ትኮራበታለህ ወይስ ስለሰደብኩት እኔን ትወቅሳለህ?

ፈፅሞ ሚስትህ ላይ እጅህን እንዳትሰነዝር! ምንም ትበልህ ምንም ጥለህ ውጣ…. ነገሮች ተረጋግተው ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ተመልሰው ታገኛቸዋለህና። አሁን የነገርኩህን ታሪክ አስታውስ!

አባትህ ከሄደ ቡኋላ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማኛል። በዚሁ ቀን ምሽት አንድ አልጋ ላይ ነው የምንተኛው። በቀጣዩ ቀን ግን ይቅርታ እጠይቀዋለሁ፤ እንዳዘንኩ ለማሳየትም የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ። እናም ይቅርታ ያደርግልኛል።

በጣም የሚወደውንም ምግብ እሰራለታለሁ። አዎ የአትክልት ሾርባና ዶሮ ወጥ እንደሚወድ ታውቃለህ። ከዛ ቀን ቡኋላ ስም ሰጥቼው አላውቅም፤ ለእሱ ያለኝ ክብር አስር እጥፍ ጠንካራ ሆኗል።

ልጄ በጥሞና አድምጠኝ! ሁሌም ልታደርገው የሚገባ ጠቃሚ ነገር…. በችግሯም በደስታዋም ፣ በተገፋችበትና በተበደለችበት ጊዜ ሁሌም ከጎኗ ሁን። አለሁልሽ በላት። ሰዎች የሚጠሏት ከሆነ…. ንግስት ሆና እንድትታይ ማድረግ የአንተ ግዴታ ነው።

አጎትህ፤ ማለቴ አጎትህ የሱፍ ፈፅሞ አይወደኝም። ነገርግን ለእኔ ያለውን አመለካከት እስኪቀይር ድረስ አባትህ ሁሌም ይረዳኛል አለሁልሽ ይለኝም ነበር።

አንድ ቀን የስራ አጋሮቹን እና ጓደኞቹን ከቤት ጋቡዟቸው መጥተው ነበር። ያንቀን ኩሽና ውስጥ ለእነሱ ምግብ አብስየ አባትህ የሚጠጣ ነገር ገዝቶ መጥቶ ምግቡ ቀርቦ ሁሉም መብላት ጀመሩ። ምግቡ ላይ ጨው አለመጨመሬ ድንገት ትዝ አለኝ።

ተዋረድኩ ስል …. አባትህ ሁኔታየን አይቶ ምግቡን ቀምሶ ዘወር በማለት በባለፈው ወር የጤና እክል ገጥሞት ሚስቱ ምግብ ስታበስል ጨው እንዳትጨምርበት ነግሯት መሆኑን በሚያስቅ መልኩ ነገሯቸው…ሁሉም ሳቁ!

ጨውን እንዳመጣ ጠይቆኝ… እያንዳንዳቸውም እንደየፍላጎታቸው ጨምረው በሉ። ያኔ አባትህ ምግቡን ያለጨው ነበር የበላው። እንግዶቹ እንደሄዱም በጉልበቱ ተንበርክኮ ለዋሸበት የአሏህን ምህረት ለመነ።

ሚስትህ አንዳንዴ የምትለውን የምትሰራውን ላታውቅ ትችላለች…. እናግራትና ለመግባባት ፣ ለመረዳዳት ሞክር። እናትህን እንደምትወድ ችግሮችህን ሁሉ እንደምትነግረኝ አውቃለሁ ነገርግን አሁን ነገሮች ሁሉ የተለዩ ይሆናሉ።

ከእኔ በፊት ችግሮችህን የምታውቀው የመጀመሪያዋ ሚስትህ ትሁን….. ስትጣሉ/ ስትጨቃጨቁ ወደ እኔ አትምጣ…. ቀኑ እስኪያልፍ ጠብቅና ስለነገሩ አውራት ፣ ተረዳዱ…. ዱአም አድርግ! የተፈጠረውንም ችግር ለማንም አትግለጥ!

በየወሩ ከሚስትህ ጋር እየመጣህ ጠይቀኝ። ቤትህን አሏህ ይባርክልህ…. ዱአ አብዛ ሁሌም የአሏህን እርዳታ ፈልግ… በደስታና በፍቅር የተሞላች ጎጆ ይኖርሃል!

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top