የአብዱሏህ ቤተሰብ ታሪክ የስኬት ጎዳና

የአብዱሏህ ቤተሰብ ጠንካራ ሙስሊሞች ሲሆኑ በዚህ ታሪክ ሐዲ የተባለ የዘጠኝ ዓመት ልጅ አላቸው። ሐዲ በትመህርት ቤት የሚሰጡ ፈተናዎችንና አሳይመንቶችን ይፈራና ይጠላ ነበር።

ስፖርት መጫወት በክፍል ውስጥ ካለው ውድድርና ተሳትፎ ስኬት የበለጠ ቀላልና ምቹ እንደሆነ ያስባል። ቤተሰቦቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ይረዱት ዘንድ እንዲህ ሲል ይጠይቃል:-

ሐዲ: ሁልጊዜ ስኬታማ እንዴት መሆን እችላለሁ አባየ?

አባት: ከሁሉም በላይ ስለስኬት ልነግርህ የምችለው ፍቹን ከቁርአን በማየት ነው።

እናት: ባለፈው ዓመት ያጠናኸውን ሱራ ሸምስ ታስታው ሳለህ አይደለ? ስትል እናት ጠየቀችው

ሐዲ: እማየ እኔኮ የጠየኩት በትምህርቴ እንዴት ስኬታማና ተወዳዳሪ መሆን እንደምችል ነው።

አባት: እናውቃለን ትክክለኛ ስኬት ሊሳካ የሚችለው እራስን በመቆጣጠራና እራስን ወደ ትክክለኛ ጐዳና በመምራት እንደሆነ ስለምናምን ነው። ይህን የምታደርግ ከሆነ በትምህርት ቤት ብቻ አይደለም በህይወትህ ስኬታማ ትሆናለህ።

ሐዲ: እራስን መቆጣጠርና ወደ ትክክለኛ ጐዳና በመምራት ስትል ምን ማለትህ ነው አባየ?

አባት: ህይወታችን በፈተና የተሞላች ስትሆን ልክ እንደ ትልቅ ትምህርት ቤት ናት። ቁርአን እንደሚነግረን ለእራሳችን ተዝኪያ የምናደርግ ከሆነ ፈተናውን እናልፋለን፤ ጀነትንም እንመነዳለን። ይህን ማድረግ ካልቻልን ወደ ጀሃነም እንወረወራለን።

እናት: በትክክል! ሐዲ ጀነት መግባት ትፈልጋለህ?

ሐዲ: አዎ እማየ! ነገርግን በትምህርት ቤቴም ስኬታማና ተወደዳዳሪ ከሆኑ ተማሪዎች መካከል መሆንም እፈልጋለሁ።

አባት: ተዝኪያ ካደረክ የተሻለ ነገር በትምህርት ቤት ማድረግ እንደምትችል ተስፋ አደርጋለሁ።

ሐዲ: ተዝኪያ ምንድ ነው አባየ?

አባት: በአረብኛ ተዝኪያ ማለት ሁለት ነገር ነው (1) ተዝኪያ ማለት እራስን ከመጥፎ ሃሳብና ስራዎች ማፅዳት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ (2) ጥሩ እምነትንና ጥሩ ባህሪን ማበልፀግ ማለት ነው።

ሐዲ: አሁን ተረድቻለሁ ለራሴ ተዝኪያ ካደረኩ እራሴን ማሳደግና በትምህርቴም የተሻልኩ መሆን እችላለሁ ማለት ነው።

እናት: በትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም በምታደርገው ነገር ሁሉ ስኬታማ መሆን ትችላለህ። ለዚህም ብለን አባትህና እኔ ወደ ኢስላማዊ ትምህርት ቤት እንልክሃለን። ትምህርት ቤቱም በመልካም ባህሪ እንደሚያንፅህም ተስፋ እናደርጋለን።

ሐዲ: በጣም አመሰግናለሁ እማየ። ለዚህም ሆነ ለመጭው አለም የተሻለን ነገር እንደምትመኙልኝ አውቃለሁ። አሁን እንዴት ተዝኪያ ማድረግ እንደምችል ንገሩኝ።

አባት: ይህ እስከ ህወትህ ፍፃሜ ድረስ የሚዘልቅ ነው ሐዲ። ምክኒያቱም እንደነገርኩህ ህይወት በፈተና የተሞላች ናት። ቁርአንና የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) መንገድ እና ምሳሌዎቹን ልታጠና ይገባል።

በሁሉም ስራዎችህ ጥሩና ጠንካራ ሙስሊም ልትሆን ይገባል። ሙሉ ህይወትህን ከመልካም ስራዎች ጋር ኢማንህን ጠንካራ ለማድረግና ኢህሳን ደረጃ ላይ ለመድረስ ጥረት አድርግ።

ሐዲ: በዚህ ረጅም ጉዞ ሊያግዘኝ የሚችል የምተገብረው ነገር አለ?

እናት: አዎ! ማንኛውንም ስራ በምትሰራበት ጊዜ በሶላትህ በጥናትህ ወ.ዘ.ተ ሁሉ ለአሏህ ቅን ለመሆን የቻልከውን ሁሉ አድርግ።

ሐዲ: የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። አሏህ በትምህርቴም በሂወቴም ስኬታማ ያደርገኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።

እናት: አሏህ ይቀበልህ ሐዲ።

ሐዲ: እንዳልረሳ እፈራሁ? አባት: አሏህ ያስታውስሃል ፍላጐቱ ካለህ ወጣት እያለሁ አስተማሪየ ያስተማሩኝን ልትሰራ ትችላለህ።

ሐዲ: አባየ ምንድ ነው ያስተማሩህ?

አባት: የዝርዝር ስራዎች እቅድ የሚባል ዝርዝር ነገሮችን ሰጡኝ። በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ ከመተኛቴ በፊት ሁሉንም ጥያቄዎች ቀን ስለ ሰራኋቸው ስራዎች እንዳስታውስ ነገሩኝ።

ሁሉንም ወይም አብዛሃኛውን ጥያቄ አዎ! ብየ ከመለስኩ ብዙ መልካም ስራዎችን ሰርቻለሁ መጥፎ ስራዎችን ደግሞ አስዎግጃለሁ ማለት ነው። ለዚህም ደስተኛና አሏህን አመስጋኝ እንድሆን ነገሩኝ።

አብዛሃኛውን አላደረኩም ብየ ከመለስኩ በእለት ተእለት ኢስላማዊ ተግባሬ ወድቂያለሁ ማለት ነው። አሏህን ምህረት ልጠይቅና የተሻለን ነገር በቀጣዩ ለመስራት መሞከር እንዳለብኝ ነገሩኝ።

ሐዲ: ተመሳሳይ ዝርዝር ነገሮችን ታዘጋጅልኛለህ አባየ?

አባት: አዎ! በትክክል አዘጋጅልሃለሁ።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top