ነብዩ ሙሳ (    ) ከቁርጥ ውሳኔ መልዕክተኞች አንዱ ሲሆኑ ከሊሙሏህ (አሏህ ያናገራቸው) ተብለውም ይታወቃሉ። ሃያሉ አሏህ በሲና ተራራ አናግሯቸዋልና።

ጨቋኙ የግብፅ ንጉስ የነበረው ፊርኦን ከእስራኤል ልጆች አነዱ ሲያሸንፈው በህልሙ አየ፡፡ ሆኖም ቀሳውስቱን እና ድግምተኞቹን ሰበሰበ። ከእነሱ መካከል አንድ ወንድ ልጅ  ይወለዳል፤ የግብፅ ህዝቦችም በእጆቹ ይጠፋሉ ሲሉ አብራርተው አስረዱት።

በዚህም ምክኒያት አዲስ የሚወለዱ ሁሉም የእስራኤል ወንድ ልጆች እንዲገደሉ ፊርአውን አዘዘ።

ነብዩ ሙሳ መወለድ

ወንድ ልጆች በሚገደሉበት በዚህ ጊዜ ነብዩ ሙሳ ( ) ተወለዱ። እናት ልጄን ይገሉብኛል ብላ ፈራች ፣ ተጨነቀችም። እናም በሚስጥር ማጥባት ጀመረች። ለልጇ ሳጥን እንድታበጅ ፣ ሳጥኑ ውስጥ ልጇን እንድታስገባ እና ወደ አባይ ወንዝ ወስዳ ወንዙ ላይ ሳጥኑን እንድታስቀምጥ አሏህ ( ) አሳወቃት።

ይህን እንዳደረገችም በጣም አዘነች። ነገርግን በእርግጠኝነት አሏህ እንደሚጠብቀው ታውቅ ነበር።

ቅርጫቱ የቤተ-መንግስቱ የወንዝ ዳርቻ ላይ ባረፈ ጊዜ ጠባቂዎች ወደ ቤተመንግስት ወሰዱት። የፊርአውን ሚስት አማኝ ነበረች። ቆንጅየውን ልጅ እንዳየች ወዲያውኑ በጣም ወደደችው። መፀነስ አትችልም ነበርና ልጁን ተንከባክበን እናሳድገው ስትል ባሏን ተማፀነች።

ሆኖም ነብዩ ሙሳ ( ) የፊርአውን ቤተመንግስት ውስጥ ሆኖ አደገ። ነብዩ ሙሳ ( ) የሌሎች እናቶችን ጡት አልጠባም በማለቱ አሏህ የእናቱን ጡት እንዲያገኝ አደረገ።

አሏህ (   ) ለሙሳ (    ) ጤና ፣ ጥንካሬ ፣ እውቀት እና ጥበብ ሰጥቶታል። ደካሞች እና ጭቁኖች የእሱን መጠለያ እና ፍትህ ይፈልጉ ነበር። አንድ ቀን አንድ እስራኤላዊ በአንድ ግብፃዊ ሲደበደብ ደርሶ እንዲረዳው ይለምነዋል።

ነብዩ ሙሳ (    ) በጠባቸው መሃል ይገባል፤ ወዲያውም በቁጣ አንድ ጊዜ ከባድ ምት ይመታውና ይሞታል። እንደገደለው ሲያውቅ ሙሳ (   ) በሃዘን ተውጦ ወዲያውኑ የአሏህን ምህረት ለመነ።

የነብዩ ሙሳ ስደት

ሙሳ (    ) ግብፃዊውን ሰው በመግደሉ ቅጣቱ ሞት እንደሆነ ያውቃል። ሆኖም በጣም ፈራ። የከተማው ሹማምንት እሱን ለመግደል መከሩ። በአንድ ቅን ሰው ምክር ምክኒያት ከተማዋን ለቆ ሊወጣ ወሰነ።

ነብዩ ሙሳ (   ) ግብፅን ለቆ በመውጣት ጉዞውን ወደ ሚድያን ሐገር አደረገ። ሚድያን እንደደረሰም ከአንድ ዛፍ ጥላ ስር አረፈ።  በጎቻቸውን ውሃ የሚያጠቱ እረኞችንም ከርቀት ተመለከቶ ወደ ምንጩ የውሃ ጉድጓድ ሄደ። ሁለት ሴቶች በጎቻቸው ከሌሎች በጎች ጋር እንዳይቀላቀሉ ሲከላከሉ ተመለከተ።

ሴቶቹ እርዳታ እንደሚሹ ተሰማውና በጎቻቸውን ውሃ አጠጣለቸው። ወጣቶቹ ሴቶች ወደ ቤታቸው እንደ ተመለሱ ከቀድሞው ጊዜ በተለየ ፈጠን ብለው የተመለሱበትን ምክኒያት ከውሃው ጉድጓድ ያጋጠማቸውን ክስተት ለአባታቸው አጫወቱት። ይህን ደግ እንግዳ ወደ ቤት እነድትጠራው ከሴት ልጆቹ አንዷን ላካት።

የነብዩ ሙሳ እረኝነት

አንደኛዋ ልጅ ጠንካራና ታማኝ ነው ሙሳን ቅጠረው ስትል ለአባቷ ሃሳብ አቀረበች። ሽማግሌው ይህን በመስማቱ ደስ ተሰኘ። ለስምንት አመት ያህል ካገለገልከኝ ከሁለቱ ሴት ልጆቼ አንዷን እድርልሃለሁ አለው። አስር አመት ልሙላ ካልክ ውለታው ከአንተ ነው።

ሙሳ ( ) በዚህ በመስማማቱ የሽማግሌውን አንደኛዋን ልጅ አግብቶ ሽማግሌውን እያገለገለ ለአስር አመት ያህል ተቀመጠ።

ነብዩ ሙሳ (    ) ግብጽ ያሉ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ከቤተሰቡ ጋር ሚዲያን ለቆ በደቡብ በኩል በረሃውን አቋርጦ ሄደ። አንድ ቀን ድቅድቅ ጨለማ እና ብርድማ በሆነ ሌሊት ላይ መንገዱ ጠፋባቸው።

ወዲያውም በጡር ተራራ አቅጣጫ በኩል ከርቀት እሳት አየ። የምንሞቀው እና ለመንገዳችን መሪ የሚሆነን እሳት ይዜ ልምጣ፤ እናንተ እዚሁ ጠብቁኝ ብሎ ሄደ።

ወደ እሳቱ እንደቀረበም ከጡዋ ሸለቆ በስተቀኝ በኩል ከምትገኝ አንዲት ዛፍ ላይ ከፍ ባለ ድምፅ ሲጠራው ሰማ ሙሳ ሆይ! እኔ አሏህ ነኝ፤ የፍጥረተ አለሙ ጌታ። እዚህ ቦታ ላይ አሏህ ሁለት ተአምራትን ለሙሳ (  ) ሰጠው።

በትሩ ወደ ሚያስፈራ እባብ ይቀየር ነበር። እንዲሁም እጁን ከልብሶቹ እጥፋት ሲያወጣ ነጭ እና የሚያፀባርቃል ይሆን ነበር።

የነብዩ ሙሳ ተአምራት

ነብዩ ሙሳ (   ) ከወንድሙ ሐሩን (   ) ጋር በመሆን ፊርአውን አሏህን ብቻ እንዲያመልክ እንዲጠራው እና የእስራኤል ልጆችን ይዞ እንዲወጣ አሏህ አዘዘው።

ሙሳ ( ) ለፊርአውን ተአምራዊ ምልክቶቹ ባሳየው ጊዜ በእብሪተኝነት እውነቱን ካደ። ፈርኦንም እንዲህ አይነቱን መተት በደጋሚዎቼ እፈጥራለሁˮ አለ።

ይህን ለማስተባበል ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ላይ እንዲሆን ተስማሙ። ነብዩ ሙሳ (   ) በጣም ብዙ ሰዎች የሚሰባሰቡበትን የቤተመቅደሱን ታላቅ ቀን መረጠ። በዚህ ታሪካዊ ቀን ሙሳ (   ) የደጋሚዎቹን መተት አጋለጠ።

እውነትን ይዞ የመጣ መሆኑን በመረዳት ደጋሚዎቹ ሱጁድ አደረጉ (ሰገዱ)። በፍጥረተ አለሙ ጌታ ያመኑ መሆኑን አወጁ።

ጊዜ እንዳለፈ ሙሳ(  ) ህዝቦቹን ይዞ ግብፅን ለቆ ወደ ፈለስጢን በሌሊት እንዲሄድ አሏህ (   ) አዘዘው። ሆኖም ግብፅን ለቀው ሄዱ። ፈርኦንና ወታደሮቹም ተከተሏቸው።

ሁለቱ አካል ጠዋት ማለዳ ላይ እርስ በርስ በተያዩ ጊዜ የሙሳ ሰዎች በእርግጥ ተያዝን፤ አለቀልንˮ አሉ። በፊርአውን እና በወታደሮቹ ላይ አሏህ ይረዳናል ሲል ሙሳ (   ) አረጋገጠላቸው።

እናም ሙሳ (    ) ባህሩን በበትሩ እንዲመታ አሏህ ገለፀለት። ባህሩ ልክ እንደ ትልቅ ግዙፍ ተራራ ሆኖ ተከፈለ። ሙእሚኖችም በሰላም ተሻግረው አለፉ።

ፊርአውን እና ወታደሮቹ መካከል ላይ እንዳሉ ውሃው ሙሉ በሙሉ አጥለቀለቃቸው። ሁሉም ሰጠሙ፤ ጠፉም። አሏህ ሙሳን ተከታዮቹን አዳናቸው።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top