Table of Contents

ነብዩ ሉጥ( ) የተላኩት በሙት ባህር ምዕራባዊ ዳርቻ በኩል ለምትገኝ የሶዶም ከተማ ህዝቦች ነው። ነዋሪዎቿ ሱስ ከሆነባቸው ከብዙ ሃጢያታቸውና ከመጥፎ ምግባራቸው ይቆጠቡ ዘንድ አስተማሩ። ከእነሱ በፊት የነበሩ ሌሎች ህዝቦች ፈፅመውት የማያውቁትን ነውረኛ ባህሪያቸውን እንዲተው ህዝቦቹን አስጠነቀቀ።

እነሱም ሴት ሲያስፈልጋቸው ወንዶችን ይቀርቡ ነበር። አውራጎዳና ላይ ይዘርፋሉ ፣ በስብሰባዎቻቸው መሃል እርጉም ተግባራትን ይፈፅሙም ነበር። በምግባራቸው እጅግ በጣም የዘቀጡ በመሆናቸው የሉጥን ስብከተ ሃይማኖት መስማት እንኳ ፈፅሞ አይፈልጉም ነበር። ከአሏህ ቅጣት ባስጠነቀቋቸው ጊዜ }አስተምህሮትህን የምትቀጥል ከሆነ ከዚች ከተማ አስወጥተን እናባርርሃለን~ ሲሉ ዛቱ።

በተውበት ወደ አሏህ እንዲመለሱ ለብዙ አመት ጥሪ ሲያደርግላቸው የቆየ ቢሆንም እንኳ ከቤተሰቦቹ ውጭ ጥሪውን የተቀበለ እና ያመነ አንድም ሰው አልነበርም። እንዲያውም ከቤተሰቦቹ ውስጥ ሚስቱ በግትርነት አልተቀበለችም፤ አላመነችም።

ነብዩ ሉጥ(   ) በፅናት እና በትዕግስት ላይ ሆነው ቆዩ። ብዙ አመታቶች አለፉ። አንድም ሰው ግን በእሱ ያመነለት አልነበረም። ይልቁንም ያሾፉ እና ይቀልዱበት ነበር። እንዲህም ሲሉ አፌዙበት }ከእውነተኞች መካከል አንዱ ከሆንክ የአሏህን ቅጣት በእኛ ላይ አምጣብን!~ (አል-ቁርአን 29፡29)

በመጨረሻም ሉጥ( ) አሏህ ድልን እንዲሰጣቸው እና ምግባረ ብልሹ ህዝቦቹን እንዲያጠፋቸው ተማፀኑ። ነብዩ ኢብራሂም( ) ብዙ ጥበብ እና እውቀት ያለው ልጅ እንደሚወልድ ብስራት ሊሰጡት መልአክቶች በመጡ ጊዜ የሉጥን መጥፎ ህዝቦች እንዲያጠፉ እንደተላኩም ነገሩት።

ከነብዩ ኢብራሂም( ) ተነጥለው እንደሄዱ ወዲያውኑ ወደ ሰዶም አቀኑ። እዚያ ነብዩ ሉጥ( ) በእንግድነት የሚቀበሏቸው መሆኑን ጠየቁ። መጥፎ ህዝቦቹን የሚቀጡ ከአሏህ የተላኩ መልአክቶች መሆናቸውን አላወቀም፤ ውብ መልከመልካም ወጣቶች ነበሩና ከህዝቦቹ መጥፎ ምግባር ለመታደግ ለሊቱን እዚያው እንዲያሳልፉ ሊያሳምናቸው ሞከረ። አንድም ሰው እንዳያያቸውም እስኪመሽ ድረስ እንዲጠብቁ ነገራቸው።

በመሸ ጊዜ ሉጥ( ) እንግዶቹን አጅቦ ወደ ቤቱ ወሰዳቸው። የሉጥ ሚስት እንዳየቻቸው ወዲያውኑ ከቤት ወጥታ በመሄድ ዜናውን ለአካባቢው ሰዎች አዳረሰች። ወሬው እንደ ሰደድ እሳት ተዛመተ። ይህን ዜና የሰሙ ሰዎች በፍጥነት ጉዟቸውን ወደ ሉጥ( ) ቤት አደረጉ። ሉጥ( ) እንግዶቼን ተዋቸው፤ የአሏህን ቅጣት ፍሩ ሲል ሰዎቹን ለመነ። በንቀት ሳይቀበሉ ቀሩ። እሱም ሃይል ቢኖረኝ እና ከእንግዶቼ ገፍትሬ ባላቀኳቸው ሲል ተመኜ።

እንግዶቹ ሁኔታውን አይተው እንዲህ አሉ፡ }አትፍራ፤ አትዘንም። በእርግጥ ከሚስትህ በቀር አንተን እና ቤተሰቦችህን እናድናችኋለን። እሷ ኋላ ቀሚቀሩት ናት።~ (አል-ቁርአን 29፡33) የሉጥ(  ) ሚስት ከሚጠፉት ህዝቦቹ ጋር አብራ ለመጥፋት ተሰለፈች።

ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ነብዩ ሉጥ(  ) ከሚስቱ በቀር ሌሎች ቤተሰቦቹን ይዞ ቤቱን ለቆ እንዲወጣ መልአክቶቹ አስጠነቀቁት። እናም አሏህ ሶዶምን እና መጥፎ ነዋሪዎቿን አጠፋቸው። በጣም ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የድንጋይ ዝናብ ከተማዋን አናወጣት። ሙሉ ከተማዋ ከስር ፈልፍለው የገለበጧት ትመስላለች። የሉጥ ሚስትን ጨምሮ ሁሉም ነገር ጠፉ።

ይህን ክስተት ቁርአን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፡ ከሚስቱ በቀር እሱን እና ቤተሰቦቹን አዳን። ከኋላ ከቀሩትም ሰዎች አደረግናት። በእነሱም ላይ (የድንጋይ) ዝናብ አዘነብንባቸው። የተስጠንቃቂዎች (የሙንዚሮች) ዝናብ ምንኛ ትከፋ!) (አል-ቁርአን 27፡57-58)

እናም ነብዩ ሉጥ(  ) እና ቤተሰቦቹን አሏህ(   ) አዳናቸው። ይህን ታሪክም ለሚረዱና ለሚያውቁ ሰዎች ምልክት አደረገው።

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top