ሁለቱ በአደን የሚተዳደሩ ሰዎች

ሁለት በአደን እሚተዳደሩ ሰዎች ነበሩ። ሁለቱም ለዘመናት ያህል አብረዉ ይሰሩና አበረው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን አንደኛው ከአማኞች ሲሆን ሌላኛው ግን ከእምነት ወጪ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን አደን ላይ ዉለዉ አንድ ቦታ ላይ ለዕረፈት ተቀምጠው ጠመንጃቸውን (መሳርያቸዉን) እየወለወሉ (እያጸዱ) እያለ መሳርያዉ ድንገት ይፈነዳና ከእመነት ዉጪ የሆነውን ሰዉ ጣት ትቆርጠዋለች።

በዛ ጉዳት የደረሰበት ሰዉ አሞት ብዙ ሲጮህ ያ ጓደኛው አይዞህ ለኸይር ይሆናል ይለዋል። በዛ ንግግር የተቆጣው ተጎጂ እንዴት ለኸይር ነው ትላለህ? እጄን መቆረጤ አሰደስቶሀልን? በማለት ይዞ በአንድ ቤት አስሮ አስቀመጠዉ።

አደንም ለብቻው ሆኖ ማደን ጀመር። እዛ አካባቢ በጣም ጫካ በመሆኑ ሰው ሚባል ማየት ብርቅ ነዉ። ግን እዛ አካባቢ ሰዎች በዓመት አንዴ እየመጡ የሚገዙት ጣኦት አለ።

ጣኦታቸዉን የሚገዙት በየአመቱ ሰዉን እያረዱ ነበረ ሚያከበሩትና ለዚህ አመታዊ በዓላቸው የሚያርዱትን ሰዉ እያደኑ (እያፈላለጉ) ሳለ ለዚህ ብቻውን እንስሳትን የሚያድነዉን ያገኙታል። ይዞዉም የእርድ ስነ-ስርዓት ወደ ሚፈፀምበት ቦታ ይወስዱታል።

ታድያ ለእርድ በተዘጋጀበት ሰዓት ነበር ጣቱ እንደተቆረጠ ያወቁት። ይህንን ሲያዉቁ አካለ ጎደሎ እንዴት ለአምላካችን እናርዳለን በማለት ይለቁት እና በምትኩ ሌላ ያፈላልጉ ጀመር።

ሱብሃነሏህ! የዛኔ ነበር ያ ሙእሚን ጓደኛው እጅህ መቆረጥህ ለኸይር ያለዉን ትክክል መሆኑን የገባው። ወዲያው አስሮ ወዳስቀመጠበት ቤት ይሄድና ይፈተዋል። ስለ ገጠመዉ ሁኔታ ይነግረዉ እና በእሱ ላይ ላደረሰበት የተሳሳተ ቅጣት ይቅርታ ይለዋል።

አሁንም ግን ያ ኢማን ያለዉ ሰዉ በድጋሚ እንዲህ ይለዋል፦ የኔ መታሰርም እኮ ለኸይር ነው ይለዋል። በንግግሩ በመገረም ያንተ መታሰር ደሞ ምን ኸይር አለዉ? ብሎ ጠየቀዉ። አንተን ለማረድ ይዘዉህ ነበር፤ አካለ ጎደሎ ብለው ሲለቁህ አብሬህ ብኖር እኔን ነበር የሚያርዱኝ። ስለዚህ እስር ላይ መቆየቴ ለኸይር ነው አለዉ።

ሱብሃነ አሏህ!

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top