ትንሽ ምክር ሚስታቸው ነፍሰጡር ለሆነች ባሎች

ለሚስትህ በእርግዝና ጊዜዋ የምታደርግላት ነገር ለእሷም ለሚወለደውም ልጅ አስተዋጽኦ እንዳለው ታውቃለህ?

ወንድሜዋ አድምጠኝ! ባሎች ነፍሰጡር ለሆነች ሚስታቸው ትኩረት ሳይሰጡ እና ጊዜያዊ ለውጦችን መሸከም አቅቷቸው ሲያማርሩ አይቻለሁ ሰምቻለሁ!

የእርግዝና ጊዜ ለዘጠኝ ወር እንጅ ለዘላለሙ የሚቆይ አይደለም። ከገበያ አልገዛችው ፣ ሶፍትዌር አይደለ ከኢንተርኔት አላወረደችው። አንተው በተከልከው ዘር ነው የሚበቅለው። ዘሩ እንዲያድግ ደግሞ እየተንከባከበ እየመገበ የሚሸከመው ይፈልጋል….ሚስት ይህን የመሸከም ሃላፊነት አለባት። አንተም በአካል ባይሆንም በሃሳቡ የመሸከም ግዴታ አለብህ።

በእርግዝና ወቅት ሚስትህ አካላዊ ለውጦችን ታሳያለች። በዚህም ምክኒያት የተወሰነ ነገር ልታደርግና ልትጠይቅህ ትችላለች።

  • አንዳንዴ ልትነጫነጭ/ልትጨቃጨቅ ትችላለች
  • አንዳንዴ የማይታሰብ ነገር ልትጠይቅ ትችላለች
  • አንዳንዴ ድክምክም ልትል ትችላለች….ምግብህን ሁሉ ላትሰራ ትችላለች
  • በሰአቱ ፍላጎቷን ማሟላት የማትችለውን ነገር ልትጠይቅህ ትችላለች
  • አንዳንዴ ምግብ በቀመሰች ቁጥር ሊያስታውካት ይችላል
  • አንዳንዴ እንቀልፍ እንቅልፍ ይላታል
  • አንዳንዴ ትኩሳት ይኖራታል
  • ክብደት ልትጨምር ትችላለች
  • ጢቅ ጢቅ ያስብላታል

ይህን ሁሉ አውቀህ መቀበል ለእሷ ምቾት መፍጠር የአንተ ግዴታ ነው። ባህሪዋ የሚያበሳጭ ሊሆን ይችላል…ብዙ ጊዜ ላትቋቋመው ትችላለህ… ሚስትህ ላንተ የዘርህ መተኪያ ናትና ሁሌም ከጎኗ ሁን።

ማስታወሻ

  • የሚስትህን እግሮች ሁሌም ተመልከት… ብዙ ጊዜ ያብጣሉና ለብ ባለ ውሃ እግሯን እንድትዘፈዝፍ እርዳት
  • ዘወትር ምን እንደሚሳማትና ልጇ እንዴት እንደሆነ ጠይቃት
  • በእርግዝና ጊዜዋ እንዴት ውብ እንድሆነች ንገራት። ለምሳሌ፦ “ማሬ ይሄ እርግዝና ግን እንዴት ውብ አድርጎሻል፤ እኔማ በየወሩ ማስረገዝ አለብኝ…እንደገና ትኩስ ሆንሽ አደል እንዴ” በላት
  • አንዳንዴ ምቾት ልታጣ ሊያማት ይችላልና….ህመሟ ይሰማህ…አካሏን ማሳጅ አድርግላት….ብቻዋን እኮ አትሸከመውም…የአንተም ልጅ ነው…ይሰማህ ወንድሜዋ!
  • ስራህን አታቋርጥ
  • አንዳንዴ ወደ ውጭ ይዘሃት ሂድና አዝናናት ወንድሜ ለሚስትህ በእርግዝና ጊዜዋ በጣም ቅርብ ሁን….ምክኒያቱም ከምታስፈልጋት ጊዜ ውስጥ አንዱ ነውና!
Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top