አግብተሃል ወይስ ለማግባት እየተዘጋጀህ ነው

Author picture
ልጄ አሁንማ ጎልማሳ ሁነሃል፤ እናት የልጇን እራስ እያሻሸች....ነገ ምግብህን አብሳይ እና ሚስጥርህን ሁሉ የምትጋራህ አዲስ እናት ይኖርሃል። ከዚህ ቡኋላ እኔ አልሆንም። እኔን ከምትወደኝ በላይም ቢሆን አዲሷ እናትህን ውደድ። በእሷ እቅፍ ከመሆንህ በፊት ግን ትንሽ ልምከርህ!

አግብተሃል ወይስ ለማግባት እየተዘጋጀህ ነው? እንግዲያውስ እናት ለልጇ ከጋብቻ ቀኑ በፊት የሰጠችውን ምክር አንብብ!

ልጄ አሁንማ ጎልማሳ ሁነሃል፤ እናት የልጇን እራስ እያሻሸች…. ነገ ምግብህን አብሳይ እና ሚስጥርህን ሁሉ የምትጋራህ አዲስ እናት ይኖርሃል። ከዚህ ቡኋላ እኔ አልሆንም። እኔን ከምትወደኝ በላይም ቢሆን አዲሷ እናትህን ውደድ።

በእሷ እቅፍ ከመሆንህ በፊት ግን ትንሽ ልምከርህ!

ከአባትህ ጋር የተጨቃጨኩባቸው ፣ የተጯጯሁበት ጊዜ ነበር። ቁጣው ከባድ ነው። እኔም እሱም ቁጡ ነን። ደደብ ብየው አውቃለሁ። በንዴት እኔን እየተመለከተ እንዴት እንደዛ ብየ ልጠራው እንደደፈርኩ ይጠይቀኛል።

ወዲያውኑ ደደብ ፣ ቂል ፣ እብድ ብየ እሰድበዋለሁ። ምን እንደሚያደርግ ገምት…. ለመማታት እጁን አላነሳም። ወዲያውኑ በሩን ገጭ አድርጎት ወጥቶ ሄደ።

ልጄ አባትህ ቢመታኝ ፣ አይኔን ቢያጠፋኝ ኖሮ ዛሬ እዚህ እኔ ጋር በመቀመጥህ እንዴት ነበር የሚሰማህ? እንዳባትህ ታየው ነበር? ትኮራበታለህ ወይስ ስለሰደብኩት እኔን ትወቅሳለህ?

ፈፅሞ ሚስትህ ላይ እጅህን እንዳትሰነዝር! ምንም ትበልህ ምንም ጥለህ ውጣ…. ነገሮች ተረጋግተው ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ተመልሰው ታገኛቸዋለህና። አሁን የነገርኩህን ታሪክ አስታውስ!

አባትህ ከሄደ ቡኋላ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማኛል። በዚሁ ቀን ምሽት አንድ አልጋ ላይ ነው የምንተኛው። በቀጣዩ ቀን ግን ይቅርታ እጠይቀዋለሁ፤ እንዳዘንኩ ለማሳየትም የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ። እናም ይቅርታ ያደርግልኛል።

በጣም የሚወደውንም ምግብ እሰራለታለሁ። አዎ የአትክልት ሾርባና ዶሮ ወጥ እንደሚወድ ታውቃለህ። ከዛ ቀን ቡኋላ ስም ሰጥቼው አላውቅም፤ ለእሱ ያለኝ ክብር አስር እጥፍ ጠንካራ ሆኗል።

ልጄ በጥሞና አድምጠኝ! ሁሌም ልታደርገው የሚገባ ጠቃሚ ነገር…. በችግሯም በደስታዋም ፣ በተገፋችበትና በተበደለችበት ጊዜ ሁሌም ከጎኗ ሁን። አለሁልሽ በላት። ሰዎች የሚጠሏት ከሆነ…. ንግስት ሆና እንድትታይ ማድረግ የአንተ ግዴታ ነው።

አጎትህ፤ ማለቴ አጎትህ የሱፍ ፈፅሞ አይወደኝም። ነገርግን ለእኔ ያለውን አመለካከት እስኪቀይር ድረስ አባትህ ሁሌም ይረዳኛል አለሁልሽ ይለኝም ነበር።

አንድ ቀን የስራ አጋሮቹን እና ጓደኞቹን ከቤት ጋቡዟቸው መጥተው ነበር። ያንቀን ኩሽና ውስጥ ለእነሱ ምግብ አብስየ አባትህ የሚጠጣ ነገር ገዝቶ መጥቶ ምግቡ ቀርቦ ሁሉም መብላት ጀመሩ። ምግቡ ላይ ጨው አለመጨመሬ ድንገት ትዝ አለኝ።

ተዋረድኩ ስል …. አባትህ ሁኔታየን አይቶ ምግቡን ቀምሶ ዘወር በማለት በባለፈው ወር የጤና እክል ገጥሞት ሚስቱ ምግብ ስታበስል ጨው እንዳትጨምርበት ነግሯት መሆኑን በሚያስቅ መልኩ ነገሯቸው…ሁሉም ሳቁ!

ጨውን እንዳመጣ ጠይቆኝ… እያንዳንዳቸውም እንደየፍላጎታቸው ጨምረው በሉ። ያኔ አባትህ ምግቡን ያለጨው ነበር የበላው። እንግዶቹ እንደሄዱም በጉልበቱ ተንበርክኮ ለዋሸበት የአሏህን ምህረት ለመነ።

ሚስትህ አንዳንዴ የምትለውን የምትሰራውን ላታውቅ ትችላለች…. እናግራትና ለመግባባት ፣ ለመረዳዳት ሞክር። እናትህን እንደምትወድ ችግሮችህን ሁሉ እንደምትነግረኝ አውቃለሁ ነገርግን አሁን ነገሮች ሁሉ የተለዩ ይሆናሉ።

ከእኔ በፊት ችግሮችህን የምታውቀው የመጀመሪያዋ ሚስትህ ትሁን….. ስትጣሉ/ ስትጨቃጨቁ ወደ እኔ አትምጣ…. ቀኑ እስኪያልፍ ጠብቅና ስለነገሩ አውራት ፣ ተረዳዱ…. ዱአ አድርግ! የተፈጠረውንም ችግር ለማንም አትግለጥ!

በየወሩ ከሚስትህ ጋር እየመጣህ ጠይቀኝ። ቤትህን አሏህ ይባርክልህ…. ዱአ አብዛ ሁሌም የአሏህን እርዳታ ፈልግ… በደስታና በፍቅር የተሞላች ጎጆ ይኖርሃል!

0%
2
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሙስሊም ቤተሰብ

ጥያቄና መልስ፡ የጋብቻ ጥያቄ ስነምግባሮች

‹‹የጋብቻ ጥያቄ አደቦች›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 የጋብቻ ጥያቄ ሲቀርብ አንዲትን ሴት ለመመልከት ከግምት ውስጥ ማስገባት ካለበት ነገር መካከል

2 / 6

Bookmark question icon

2 የትዳር አጋር ለመምረጥ አንድ ሰው መስፈርቱ ሊያደርግ ሚገባው ነገር ምንድን ነው?

3 / 6

Bookmark question icon

3 መመልከት የተፈቀደው ለወንድ ነው እንጅ ለሴት አይደለም።

4 / 6

Bookmark question icon

4 ወንዱ ወይም ሴቷ እንከን ኖሮባቸው አንደኛቸው በዚህ ምክኒያት አያገባኝም ብለው ባሰቡ ጊዜ ይህን እንከን መደበቅ አለባቸው።

5 / 6

Bookmark question icon

5 የጋብቻ ስነ-ስርአት ከመከተል ጥቅሞች መካከል አንዱ

6 / 6

Bookmark question icon

6 የእጮኛ መልክ ማድነቅ ሃይማኖቱን አጥብቆ የያዘ እና ጥሩ ባህሪ ያለው ሚለው መስፈትት ይተካል።

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 19%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

አደም (ዐ.ሰ) ከተፈጠሩ በኋላ የተሰጣቸው የመጀመሪያው ትምህርት የስሞች ዕውቀት ነበር። ይህም ከመላእክት የላቀ ደረጃ እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መላእክትም ለእርሳቸው ሱጁድ እንዲያደርጉ (እንዲሰግዱ) ምክንያት ሆኗል። ምንም

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share