እስልምና ተከታዮቹ ምስጉን ስነምግባር ወይም ውብ አህላቅ እንዲላበሱ ጥሪ ያደርጋል። አሏህ መልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-
“በእርግጥ በታላቅ ምግባር ላይ ነህ።”
(አል-ቁርአን 68፡4)
ብዙ የቁርአን አንቀፆች ሙስሊሞች መልካም ባህሪ እንዲኖራቸው ያበረታታል። አሏህ እንዲህ ይላል፡-
“ለሰዎችም መልካምን ነገር ተናገሩ”
(አል-ቁርአን 2፡83)
ሰዎችን ወደ መልካም ምግባር ወይም ባህሪ ሚጣሩ ብዙ ነብያዊ ሐዲሶች አሉ። የሚከተሉት ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው።
“የትም ቦታ ብትሆኑ አሏህን ፍሩ፤ መጥፎ ስራንም በመልካም አስከትሉ፤ ያጠፋዋልና። ለሰዎችም መልካምን አድርጉ።” (ትርሚዚ)
“በአሏህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ነገር ይናገር ወይም ዝም ይበል። በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር። በአሏህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር።” (ሙስሊም)
“አንዳችሁም አላመናችሁም ለእራሱ የወደደውን ነገር ለወንድሙም እስካልወደደ ድረስ።”
(ቡኻሪና ሙስሊም)
- “በፍረርዱ ቀን የሙዕሚኖች ሚዛን ላይ የሚቀመጠው ከባዱ ነገር መልካም ባህሪ ይሆናል። አሏህም ፀያፍ ስድብና የብልግና ቃል (ንግግር) ይጠላል።” (ትርሚዚ)
- “ በፍርዱ ቀን ከእናንተ መካከል ለእኔ በጣም ተወዳጁና ቅርብ የሆኑት ምስጉን ባህሪ (ምግባር) ያላቸው ናቸው።” (ትርሚዚ)
- አኢሻ (ረ.ዐ) ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባህሪ ተጠይቃ ስትመልስ “ባህሪው የቁርአን ባህሪ ነው። ባህሪው ቁርአን ነው።” ብላ ነበር። ይህ ማለት የቁርአን አስተምህሮቶች ሰርተውበቸዋል፤ ኑረውበታል ማለት ነው።