ከፍርዱ ቀን በፊት የሚከሰቱ ምልክቶች አሉ። ነገርግን ለሰአቱ በጣም የቀረቡ አይደሉም። ይልቁንም የሚከሰቱት በተለያየ ጊዜያት ነው። አንዳንዶቹ ቀድመው ተከስተዋል።
የጨረቃ መሰንጠቅ

አል-ቁርአን
(ሱረቱል ቀመር 54፡1)
“ሰአቷ ተቃርባለች፤ ጨረቃዋም (ከሁለት) ተሰንጥቃለች”
ይህ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ሁሉም አይተዋታል።
በሞንጎሎች እና በታርታርስ ሚከፈት ጦርነት
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“ፀጉራም ጫማ የሚለብሱ ሰዎችን እና ትንሽየ አይኖች ፣ ቀይ ፊት እና ደፍጣጣ አፍንጫ እና ፊታቸው ልክ እንደ ዝርግ ጋሻ የሚመስል ፊት ያላቸውን ቱርኮች እስካልተፋለማችሁ ድረስ ሰአቷ አትመጣም።”

እንደ ሙሑራኖች ገለፃ ይህ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ የሙስሊሙ አለም ያጠቁ ታታሮች ከሂጅራ በኋላ በ656ዓ.ሂ ሙስሊሞችን ያሸነፉ እና ሙስሊሞችም በ658ዓ.ሂ ኤን ጀሉት ጦር ሜዳ ላይ ያሸነፉበት የታሪክ ክስተት ጋር የሚገጥም ነው ብለዋል።
የሂጃዝ እሳት

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“ከሂጃዝ ምድር እሳት እስካልታየ ፣ በስራ ውስጥ ከግመል አንገቶች ላይ ብርሃኑን ወርውሮ እስካልታየ ድረስ ሰአቷ አትመጣም።” ብለዋል።
በእርግጥ ይህ እሳት ጁምአ ስድስተኛው ጁማዱል አሂር 654ዓ.ሂ ተነስቷል። አስጊ በሆነ ፍጥነት በየቦታው ተዛምቷል። ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ እስኪያበቃም ሶስት ወር ወስዷል።
የፐርዥያና የሮም አገዛዝ ውደቀት

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“ኸስራው በሞተ ጊዜ ሌላ ኸስራ አይኖርም። ሴዛር በሞተ ጊዜ ሌላ ሴዛር ከእሱ በኋላ አይኖርም።”
በአሁኑ ጊዜ የሚታዩ ብዙ ጥቃቅን ወይም ትናንሽ ምልክቶች አሉ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“ከሰአቷ ምልክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። ሃይማኖታዊ እውቀት ይጠፋል፤ ድንቁርና ይስፋፋል ፣ የአልኮል መጠጥ መጠጣት ይስፋፋል ፣ ዝሙት ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል።”
በቡኻሪና በሙስሊም በተዘገቡ ሌሎች ሐዲሶች የሚከተሉት ምልክቶች እንዳሉም ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ተጠቅሰዋል

ሀ. ብዙ ደም መፋሰስ እና የመሬት መንቀጥቀወቀጥ ይኖራል
ለ. ስግብግብነት በሰዎች ልብ ውስጥ ይነግሳል
ሐ. ፈተና እና ውጣውረድ መመከራው ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል
መ. ሴቶች ወንዶችን በቁጥር ይበልጣሉ
የፍርዱ ቀን ትናንሽ ምልክቶች አንዳንዶቹ ገና አልተከሰቱም ለምሳሌ

ሀ. ሙስሊሞች ይሁዳዎችን ፈለስጢን ውስጥ እንደሚዋጓቸውና እንደሚያሸንፏቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“ሰአቷ አትመጣም ሙስሊሞች ይሁዳዎችን እስካልተዋጓቸውና እስካልገደሏቸው ድረስ” ብለዋል።

ለ. የኤፍራጠስ ሃብት፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“ሰአቷ አትመጣም ኤፍራጠስ ሰዎች የሚጋደሉበትን የወርቅ ተራራውን እስካልገለጠ ድረስ” ብለዋል።
ሐ. በሶሪያ ሰሜኑ ክፍል ከሁለተኛው የኮንስታንቲኖፕል ድል በፊት በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች ደም የሚፋሰሱበት ጦርነት ይኖራል።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ‹ሰአቷ አትወጣም ሮማውያኖች አመቅ እና ዳቢቅ እስካላረፉ ድረስ” ብለዋል። (ሙስሊም) ዳቢቅ በአሌፓ አቅራቢያ የሚገኝ መንደር ሲሆን አመቅ ደግሞ በዳቢቅ አቅራቢያ በአሌፓ እና በአንቲየክ መካከል የሚገኝ አውራጃ ነው።

አላመቱ ሰአ አል-ኩብራ፤ የፍርዱ ቀን ትልልቅ ምልክቶች ተመልከቱ

