የፍርዱ ቀን ትልልቅ ምልክቶች

Author picture

የፍርዱ ቀን ትልልቅ ምልክቶች አንዱ ካንዱ ቡኋላ የሚከሰቱ ሲሆን የፍርዱ ቀን ወዲያውኑ ይከተላል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን አስመልክተው ሰአቷ አትወጣም ከሷ በፊት አስር ምልክቶች ያያችሁ ቢሆን አንጅ ብለዋል። አስሩን ምልክቶች ሲጠቅሱ

የፍርዱ ቀን ትልልቅ ምልክቶች

ጭሱ ፣ ደጃል ፣ አውሬው ፣ የፀሐይ በምዕራብ መውጣት

የፍርዱ ቀን ትልልቅ ምልክቶች

የመርየም ልጅ ኢሳ (እየሱስ)  መምጣት ፣ ጎግ እና ማጎግ

የፍርዱ ቀን ትልልቅ ምልክቶች

 በሶስት ቦታዎች የመሬት መንሸራተት ፣ አንዱ በምዕራብ አንዱ አረቢያ ውስጥ በመጨረሻም ከየመን እሳት መቃጠል እና ሰዎች ወደ መሰብሰቢያቸው መምጣት (ሰሂህ ሙስሊም ቁ.2901)

የማህዲ መምጣት፡ ከነብዩ ቤተሰብ እና ስሙ ልክ እንደሱ የሆነ ምድር በፍትህ መጓደልና በመጥፎ ነገሮች ከተሞላች በኃላ ይህ ሰው ምድርን በፍትህ እና በደግነት ይሞላታል።

ቁርአን ስለጭሱ እንዲህ ይላል፡

ሰማይ ግልፅ የሆነ ጭስ የምታወጣበትን ቀን ጠብቅ፤ ሰዎችን ትሸፍናለች። ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው።

(አል-ቁርአን 44፡10-11)

ደጃል (ውሸታሙ መሲህ) ያልተለመደ ጀብዱ ይፈፅማል። በምድርም ላይ ብዙ ፈተናዎችን እና መከራዎችን ይፈጥራል። ሁሉንም ቦታዎች ያወድማል።

ነገርግን መካና መዲና መግባት አይችልም ምክኒያቱም በመልአኮች ይጠበቃሉና። በመጨረሻ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኢሳ ከመጣ በኋላ ይገለዋል።

ፀሐይ በምዕራብ በወጣች ጊዜ የተውበት በሮች ይዘጋሉ። እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እንደተዘጉ ይቆያሉ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እነዲህ ብለዋል፡ በእርግጥ አሏህ እጁን ሌሊት ላይ ይዘረጋል፤ ቀን ሃጢያት የሰሩ ሰዎች ይቶብቱ ዘንድ። በእርግጥ በቀን እጁን ይዘረጋል የሌሊት ሃጢያተኞች ይቶብቱ ዘንድ። ፀሐይ በምዕራብ እስክትወጣም ድረስ ይህንኑ ያደርጋል ብለዋል። (ሙስሊም)

ቁርአን ስለ አውሬው አንዲህ ይላል፡-

በእነሱም ላይ (የቅጣት) ቃሉ በተረጋገጠ ጊዜ ሰዎቹ በአንቀፆቻችን የሚያረጋግጡ የምትነግሯቸውን እንስሳ ለእነሱ ከምድር እናወጣለን።

(አል-ቁርአን 27፡82)

ስለዚች አውሬ ተፈጥሮ ወይም ባህሪ የሚያውቀው አሏህ ብቻ ነው።

ነብዩ ኢሳ (ዐ.ሰ) በድጋሚ ይመጣል። ነገርግን እንደ ነብይ ሆኖ አይነግስም። አዲስም ህግ ይዞ አይመጣም። ምክኒያቱም ሃይማኖቱ ኢስላም ነው፤ የነብያቶች መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐወ) ናቸውና ነው።

ይልቁንም የሚከተለው ቁርአን እና የረሱልን ሱና ነው። ነብዩ (ሰ.ዐወ) እንዲህ አሉ፡ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ፤ በእርግጥ የመርየም ልጅ ኢሳ (እየሱስ) ፍትሃዊ መሪ ሆኖ ከእናንተ መሃል ይመጣል። መስቀሉን ይሰባብራል ፣ አሳማዎችን ይገላል ፣ ጅዝያን (ሙስሊም መንግስታት ከካፊሮች የሚቀበሉት ግብር) ያጠፋል። ሃብት ማንም ሰው ጉዳይ የማይለው እስኪሆን ድረስ ይትረፈረፋል። አንዲት ስግደት ከከሙሉ አለምና በውስጧ ከያዘችው ሁሉ በላይ በላጭ ትሆናለች ብለዋል። (ቡኻሪና ሙስሊም)

ነብዩ ኢሳ (ዐ.ሰ) ለተወሰነ ጊዜ በምድር ይኖሩና በመጨረሻ ጊዜ ሞተው መዲና ውስጥ ይቀበራሉ።

የጎግ አን ማጎግ (የእጁጅ እና ማዕጁጅ) ሃያላን ጎሳዎች መምጣት

አሏህ እንዲህ ይላል፡

(96) የእጁጅ እና መእጁጅ እነሱ ከየተረተሩ የሚንደረደሩ ሲሆኑ ግድባቸው በተከፈተች ጊዜ (97) እውነተኛውም ቀጠሮ በቀረበ ጊዜ ያኔ እነሆ የእነዚያ የካዱት ሰዎች አይኖች ይፈጣሉ። ዋ! ጥፋጣችን! ከዚህ (ቀን) በእርግጥ በዝንጋቴ ላይ ነበርን። እውነትም በዳዮች ነበርን ይላሉ።

(አል-ቁርአን 21፡96-97)

ደጃልን ከገደለ ከአጭር ጊዜ በኋላ ነብዩ ኢሳ (ሰ.ዐ.ወ) የእጁጅና መእጁጅ መለቀቃቸውን ይነግሩታል። የአሏህን ትዕዛዝ በማክበር ሙስሊሞችን ለደህንነታቸው ወደ ጡር ተራራ ይዟቸው ይሄዳል። ማንም አያሸንፋቸውም።

የእጁጅ እና መእጁጅ ግዙፍ ወታደሮቻቸው ሲጠማቸው የሚጠጡበት የሆነውን የታይቤሪያስን ሃይቅ አልፈው ወደ እየሩስ አሌም በመሄድ እዚያ ብዙ ጥፋቶችን ፣ ውድመቶችን እና ደም መፋሰስን ያስከትላሉ።

በመጨረሻ ነብዩ ኢሳ (ዐ.ሰ) እና ሃዋሪያዎቹ ከምድረገፅ እንዲጠፋ ይፀልያሉ። አሏህም ያጠፏቸዋል፤ ምድርን በሙት አካላቸው ይሞላሉ።

  • የመሬት መንቀጥቀጥ በምስራቅ ፣ በምዕራብ እና በአረቢያ ውስጥ ይከሰታል
  • ከፍርዱ ቀን በፊት የሚታይ ሌላኛው ትልቁ ምልክት የሰደድ እሳት መፈንዳት ነው። በሙስሊም እንደተዘገበው ይህ እሳት የመን ውስጥ ይነሳል። እሳቱም ሰዎችን ወደ መሰብሰቢያ ቦታቸው ይነዳቸዋል። የመሰብሰቢያ ቦታው ሻም (ሶሪያ ፣ ፈለስጢን ፣ ሊባኖስ እና ጆርዳን) ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ኢሳን ፣ ደጃል እና የውመል ቂያማን ተመልከቱ

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top