ደጃል (ውሸታሙ መሲህ) መታየቱ የፍርዱ ቀን መቃረብ ዋና ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። ሰዎችን ለማሳመን ያልተለመደ ጀብዱ የመፈፀም ሃይል አለው።

የደጃል (ውሸታሙ መሲህ) መታየቱ የፍርዱ ቀን መቃረብ ዋና ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። ሰዎችን ለማሳመን ያልተለመደ ጀብዱ የመፈፀም ሃይል አለው።

እናም መለኮታዊ ባህርያት አለኝ ይላል። በአይኖቹ መካከል ከ..ፋ..ራ የሚሉ ሶስት ፊደላት አሉት። ትርጉሙ ካፊር ወይም ከሐዲ ማለት ነው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደሚከተለው ገልፀውታል “ግዙፍ አካል ፣ ቀይ መልክ ፣ የተጠቀለለ ፀጉር ያለው ፣ የቀኝ አይኑ የታወረ እና አይኑ ያፈነገጠ ወይን የሚመስል ነው” (ቡኻሪ)

አለምን በሙሉ ይዞራል። ነገርግን መካና መዲና መግባት አይችልም። ምክኒያቱም እነዚህ ቅዱሳን ከተሞች ወደ እነሱ እንዳይገባ በሚከለክሉት መላዕክት ይጠበቃሉና ነው።

ልዩ ከሆኑ ተግባራቶቹ ውስጥ ዝናብ ሆኖ እንዲወርድ ደመናን ያዛል፤ አይነስውር እና ቆማጣ ሆነው የተወለዱትን ያድናል። ወጣት ልጅን በሰይፍ ከሁለት በመቁረጥ በፈገግታወው ሲያዘው ወጣቱ ወደ ህይወቱ ይመለሳል።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ተከታዮቹን አንድ አይናው ውሸታም (መሲሁ ደጃል) ያስጠነቀቀ ቢሆን እንጅ ነብይ አልተላከም። ተጠንቀቁ! አንድ አይኑ እውር ነው።

ነገርግን ጌታችሁ እንዲህ አይደለም። በአይኖቹ መካከል የተፃፈ ቃል ካፊር (ከሃዲ) የሚል አለው ብለዋል። (ቡኻሪ)

እሱ ውሃና እሳት አለው። እሳት የሚመስለው ደስ የሚል ቀዝቃዛ ውሃ ነው። ውሃ የሚመስለው ደግሞ በእርግጥ እሳት ነው። በመጨረሻም ነብዩ ኢሳ ወይም እየሱስ (ዐ.ሰ) ተመልሶ ይመጣና ደጃልን አሸንፎ ይገለዋል።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሱረቱል ካህፍ የመጀመሪያዎቹን አስር ምዕራፎች የሸመደደ ከደጃል የተጠበቀ ይሆናል ብለዋል። (ሙስሊም)

ለበለጠ መረጃ መካ ፣ መዲና ፣ ኢሳ ፣ ትልልቆቹ የምፅአት ቀን ምልክቶች የሚሉ ርዕሶችን ተመልከቱ

Related posts

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው። በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው።

Read More »
እስልምና በኢትዮጵያ፡

እስልምና በኢትዮጵያ፡ ከጥንታዊ ሥረ-መሠረቱ እስከ ዘመናዊ ስርጭቱ

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዷ ስትሆን በርካታ እምነቶች ያስተናገደች ምድርም ነች። ከእነዚህም መካከል እስልምና እና ክርስትና ይገኙበታል። እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ የራሱን ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ሃይማኖት

Read More »
የቀናት አቆጣጠር

የእስልምና የቀናት አቆጣጠር

ከእስልምና በፊት አረቦች የራሳቸው የሆነ የቀናት አቆጣጠር አልነበራቸውም። ምንም እንኳ አስራ ሁለቱን የጨረቃ ወራቶች ቢያውቁም ጊዜን የሚያሰሉት አንድ ልዩ ክስተት ከፊቱ ወይም ከኋላው የተከሰተበትን ጊዜ

Read More »
መስጅደ ነበውይ

መስጅደ ነበውይ የነብዩ መስጅድ

ነብዩ ያኔ ያስሪብ ተብላ ወደምትጠራው የአሁኗ መዲና በተሰደዱ ጊዜ ጋልበዋት በነበረችው ግመል ዙሪያ ተከታዮቻቸው እና የከተማዋ ሹማምንት ምርጥ ልብሶቻቸውን እና የብረት መከላከያ ልብሶችን እንደለበሱ ተቀበሏቸው።

Read More »

Share