የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ

ክፍል ሶሰት

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የነብይነት አዋጅ

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) 40 ዓመት በሞላቸው ጊዜ በ5ኛው ረቢዑል አወል የመላዕኮች አለቃ የሆነው ሩሁል አሚን ጅብሪል (ዐ.ሰ) ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ የመጨረሻው ነብይ አድርጐ ሊያውጅ ከመለኮታዊ ትዕዛዝ ጋር ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጣ።

በዚያን ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሂራ ዋሻ ውስጥ ዱአ እያደረጉ ነበር። ጅብሪልም እንዲህ አለ: ሙሐመድ ሆይ! መልካም የምስራች አለህ፤ አንተ የአሏህ መልዕክተኛ ነህ። እኔ ጅብሪል ነኝ። በጌታህ ስም አንብብ አሏቸው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምንም ነገር ለማንበብ እንደማይችሉና እንዳልተማሩ ነገሩት። ጅብሪል (ዐ.ሰ) አጥበብቆ እቅፍ አደረጋቸው። ደጋግሞ እንዲህ ካደረጋቸው ቡኋላ ወደ ቤታቸው መጡና አልጋቸው ላይ ተኙ። ወዲያውኑ ትኩሳት ፣ ብርድብርድ ፣ ፍርሃት ይሰማቸው ጀመር።

ይህን ተከትሎ ኸድጃ(ረ.ዐ) ልብስ እንድታለብሳቸው ጠየቋት። ትንሽ ከታገሰላቸው ብኋላ እንዲህ እንዲህ አይነት አጋጣሚ አጋጠመኝ ብለው በነገሯት ጊዜ የአጐታቸው ልጅ ወደሆነው ዋርቃ የኖፍል ልጅ ወሰደቻቸው።

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሙሉ ክስተቱን ተረኩለት። ይህን ከሰማ ቡኋላ ለሙሳ (ዐ.ሰ) እንደወረደው ያለ ተመሳሳይ ጅብሪል እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ አለ።

ከጥቂት ቀናት ቡኋላ ወደ ሂራ ዋሻ አቀኑና የመጀመሪያውን የቁርአን ወህይ ማለትም አምስቶቹ የሱራ አል-አቅ አናቅፅቶች ተገለፁላቸው።

እነዚህ 5 አናቅፅቶች በኢስላም የማንበብ መለኮታዊ ጥቅምን የሚያሳዩ አናቅፅቶች ናቸው።

“አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ ያ ሰውን በብርዕ ያስተማረ፡፡ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡”

{አል-ቁርአን 96:1-5}

ሶላት

ጅብሪል (ዐ.ሰ) ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ከሂራ ዋሻ ከተራራው ስር ወሰዳቸውና ጅብሪል (ዐ.ሰ) ራሱ ውዱእ አደርጐ አሳያቸው። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ልክ እንደ ጅብሪል (ዐ.ሰ) በተመሳሳይ መንገድ ውዱእ አደረጉ። ጅብሪል (ዐ.ሰ) ኢማም ሆኖ ሶላት አብረው ሰገዱ።

የነብዩ ሙሐመድ የስብከት ጅማሮ

ከጅብሪል (ዐ.ሰ) ጋር የመጀመሪያ ሶላት ከሰገዱ ብኋላ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤታቸው ተመልሰው ውድ ሚስታቸውን ኸድጃን መስበክ ጀመሩ።

ይች ሴት የመጀመሪያዋ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊም ሚስት ሆነች። ኢስላምን እንደተቀበለች ሶላቷን መስገድ ጀመረች። አልይ (ረ.ዐ) የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአጐታቸው ልጅ ፣ አቡበክር ሲዲቅ (ረ.ዐ) ሁሉም በመጀመሪያው ቀን ኢስላምን ተቀበሉ።

የነሱ ወደ ኢስላም መግባት የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ታላቅነት ፣ ቅድስና ፣ ደግነትቸውንና መልካምነታቸውን ያረጋገጠ ነበር።

በመቀጠልም አሏህ በሱራ አል-ሒጀር ላይ በግልፅ ይሰብኩ ዘንድ ደነገገባቸው። በመጀመሪያ ደረጃ ቤተሰባቸውንና ወዳጅ ዘመዳቸውን ወደ ኢስላም ይጣሩ ዘንድ በሱረቱል አሹራ 214 ላይ አሏህ አዘዛቸው።

አረመኔዎች በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ያደረጉት ዘመቻ

የሰው ልጆች የሁል ጊዜም አርአያ ፣ ተምሳሌት የሆኑት የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ ይህ ነው። የአረመኔዎችን ማህበራዊ ክፋት ፣ ሃጢያት ፣ ጣኦት አምላኪነትንና የአሏህን አንድነት ስላስተማሩ የመካ ሙሽሪኮች አምርረው በመቃወም በጣም ከባድና የከፋ ዘመቻቸውን በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ከፈቱ።

በቻሉት አቅም በተለያዩ ጊዚያት ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) አወገዙ ፣ ተሳደቡ። ሙሐመድ በጅኒዎች የተለከፈ እብድ ነው አሉ። ሙሐመድ ጠንቋይ ፣ ድግምተኛ ፣ ገጣሚ ነው ሲሉም ተሳደቡ።

ይህ ሁሉ ይሁንእንጂ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በፅናት የኢስላምን መልዕክት ለሁሉም የሰው ልጆች ማድረሳቸውን ቀጠሉ።

በእያንዳንዱ ስብሰባ ፣ በእያንዳንዱ በአል ፣ በእያንዳንዱ አውራጐዳና ፣ በእያንዳንዱ የእግር መንገድ የአሏህን አንድነትን በህዝባቸው ላይ ያሰርፁ ጀመር።

ከእምነተ ቢስነት ፣ ከዝሙት ፣ ከጣኦት አምላኪነት ፣ ሴት ልጆችን በህይወት መቅበርን እና ቁማርተኝነትን ከለከሏቸው።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top