የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 4

ክፍል አራት

ነብዩ ሙሐመድ በብሔራዊ በአላት የሰጧቸው ትምህርቶች

የአከዝ ፣ የቢጅኒህ እና የዚልማህዝ ባአሎች በአረቢያ ውስጥ በጣም የታወቁ በአላት ሲሆኑ ራቅ ካለ ቦታ ያሉ ሰዎች ሳይቀሩ በነዚህ ባአላት ይገኛሉ።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በነዚህ ባአላት ይገኙና መለኮታዊ ወደ ሆነው የሰው ልጆች የተፈጥሮ ሃይማኖትና ወደ አሏህ አንድነት ሰዎችን ይጣራሉ።

እንደዚህ አይነቱ የስብሰባ ንግግረቸው ቅን የሆኑ ትንሽ የሙስሊሞች ጀመአ እንዲፈጠር ምክኒያት ሆነ። አሏህ (ሱ.ወ.ተ) ቁረይሾችን ይሰብኩ ዘንድ አመላከታቸው።

የቁረይሾች ጥላቻ

የቀረበላቸውን መለኮታዊ እውነታ በመመልከት እምነተ ቢስነታቸውንና ጣኦት አምላኪነታቸውን ለመተው እጅግ በጣም የእፍረትና የውርደት ስሜት ተሰምቷቸው መንገዶቹን ሁሉ ሊዘጉባቸው አሴሩ።

በመጀመሪያ ደረጃ ቀላል የሆኑ መሰናክሎችን እንዲጋፈጡ በማድረግ የጀመሩ ሲሆን እያሉ እያሉ ግን ለከፋ ስቃይ ዳረጓቸው። አዲሶቹን ሙስሊሞች ወደ ጥንት ሃይማኖታቸው ለመመለስ ሲሉ ጠንካራ የተጋድሎ እንቅስቃሴ ጀመሩባቸው።

ቢላል (ረ.ዐ)

ቢላል (ረ.ዐ) ሐባሻዊ ሲሆን የኡመያ ቢን ኸውፍ ባሪያ ነው። ቢላል እስልምናን መቀበሉን ሲያውቅ አሳማሚ ጭቆናና ስቃይ አደረሰበት። ነገርግን ኢስላም ከልቡ ስለገባ ለዚህ ሁሉ ግፍና ስቃይ ቦታ አልሰጠውም።

ይልቁንስ በመለኮታዊ ፍቅር ስለተነደፈ ሲገረፍ “አሃድ” «አሏህ አንድ ነው።» የሚለውን መፈክር ጩኾ ያሰማ ነበር።

ለእስልምና እምነት እንዲህ አይነት ቅንነት ካሳየ ቡኋላ አቡበክር ሲዲቅ (ረ.ዐ) ከባርነት ነፃ የሚሆንበትን ያህል ዋጋ ከፍለው ከባርነት ነፃ አወጡት።

የሱሃቦች ስደት ወደ አቢሲንያ (ኢትዮዺያ)

አረመኔዎች ሙስሊሞችን ማሰቃየታቸውን በቀጠሉ ጊዜ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለደህንነታቸው ሲሉ ወደ ኢትዮዺያ እንዲሰደዱ ፈቀዱላቸው።

ከዚህ ፍቃድ ቡኋላ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው 12 ሙስሊም ወንዶችና 4 ሙስሊም ሴቶች በድቅድቅ ጨለማ የጅዳን ወደብ አቋርጠው ጉዟቸውን ወደ ኢትዮዺያ አደረጉ።

ኡስማን ኢብን አፋን (ረ.ዐ) ከሚስቱ ሩቅያ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጅ እና ጃእፈር ጠያር (ረ.ዐ) የዚህ ጉዞ መሪዎች ነበሩ።

ቁረይሾች ይህን ሲያውቁ ወደ ንጉስ ነጃሺ ቤተ-መንግስት መጡና እነዚህ ሰዎች የኛ ጐሳ አባሎች ናቸው። ከሃገራቸው አምልጠውነውና የመጡት ተመልሰው ለኛ ይሰጡን በማለት አቤቱታቸውን አቀረቡ።

ለዚህም ጃዕፈር (ረ.ዐ) እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ: አሏህ ምህረቱን በእኛ ላይ ችሮናል። ከመጨረሻው መለኮታዊ መጽሐፍ (ቁርአን) ጋር ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ልኮልናል። ወደ አሏህ አንድነት ጠሩን ፣ ሃጢያትንና ጣኦት አምላኪነትን እንድንተው ፣ ለአሏህ እንድንሰግድ ፣ ምፅዋት እንድንሰጥ አስተማሩን።

ማህበረሰባችነም ጠሉት። እስከሚችሉት ድረስም አሰቃዩን። እናም የትውልድ ሃገራችነን ትተን ተሰደድን አለ።

ንጉሱ ይህን በመስማት ቁርአን እንዲቀሩለት ፈለገ፤ ጃዕፈር (ረ.ዐ) ከሱረቱል መርየም የተወሰኑ አናቅፅቶችን ቀራለት። ንጉሱ ማልቀስ ጀመረና እንዲህ አለ:- ኢሳ (ዐ.ሰ) እንደተነበየው አይነት ተመሳሳይ የአሏህ መልእክተኛ ነው።

በሱ ዘመን በሂወት በመኖሬ ምስጋና ለአለማት ጌታ ይገባው አለ። እነዛም አረመኔዎች ሳይሳካላቸው ቀረና ወደቤታቸው ተመለሱ።

የሐምዛ (ረ.ዐ) ኢስላምን መቀበል

ከስድስት አመት የመካ ስብከት ቡኋላ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከሶፋ ተተራራ ላይ ሆነው እየሰበኩ ያለ ዋናው የኢስላም ጠላት አቡጃህል እንደ ድንገት መጣ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እውነተኛውን መለኮታዊ ራዕይ እየሰበኩ በማየቱ በጣም ተበሳጨና ሰደባቸው ፣ አጎሳቆላቸው ፣ እራሳቸውንም በድንጋይ ፈንክቶ አደማቸው።

ሐምዛ (ረ.ዐ) ይህን ባወቀ ጊዜ ወደ አቡጃህል ጠጋ አለና ጭንቅላቱን በቀስት መታው። ሐምዛ (ረ.ዐ) ለረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ቅርብ ሰው ነበር። ወደ እርሳቸው መጣና “አቡጃህልን ተበቀልኩላችሁ አልተደሰታችሁ ምንዴ” አላቸው።

የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እስልምናን ስትቀበል እደሰታለሁ አሉት። ይህን ከሰማ ቡኋላ እስልምናን ተቀበለ። በፅኑ እምነቱ የሚታወቅ የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋሻ ሆነ።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top