የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 3

Author picture
ነብዩ ሙሐመድ 40 ዓመት በሞላቸው ጊዜ በ5ኛው ረቢዑል አወል የመላዕኮች አለቃ የሆነው ጅብሪል ረሱልን የአሏህ የመጨረሻው ነብይ አድርጐ ሊያውጅ ከመለኮታዊ ትዕዛዝ ጋር ወደ ነብዩ መጣ። በዚያን ጊዜ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በሂራ ዋሻ ውስጥ ዱአ እያደረጉ ነበር።
የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ

የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ ክፍል ሶሰት

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የነብይነት አዋጅ

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) 40 ዓመት በሞላቸው ጊዜ በ5ኛው ረቢዑል አወል የመላዕኮች አለቃ የሆነው ሩሁል አሚን ጅብሪል (ዐ.ሰ) ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ የመጨረሻው ነብይ አድርጎ ሊያውጅ ከመለኮታዊ ትዕዛዝ ጋር ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጣ።

በዚያን ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሂራ ዋሻ ውስጥ ዱአ እያደረጉ ነበር። ጅብሪልም እንዲህ አለ: ሙሐመድ ሆይ! መልካም የምስራች አለህ፤ አንተ የአሏህ መልዕክተኛ ነህ። እኔ ጅብሪል ነኝ። በጌታህ ስም አንብብ አሏቸው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምንም ነገር ለማንበብ እንደማይችሉና እንዳልተማሩ ነገሩት። ጅብሪል (ዐ.ሰ) አጥበብቆ እቅፍ አደረጋቸው።

ደጋግሞ እንዲህ ካደረጋቸው ቡኋላ ወደ ቤታቸው መጡና አልጋቸው ላይ ተኙ። ወዲያውኑ ትኩሳት ፣ ብርድብርድ ፣ ፍርሃት ይሰማቸው ጀመር።

ይህን ተከትሎ ኸድጃ(ረ.ዐ) ልብስ እንድታለብሳቸው ጠየቋት። ትንሽ ከታገሰላቸው ብኋላ እንዲህ እንዲህ አይነት አጋጣሚ አጋጠመኝ ብለው በነገሯት ጊዜ የአጐታቸው ልጅ ወደሆነው ዋርቃ የኖፍል ልጅ ወሰደቻቸው።

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሙሉ ክስተቱን ተረኩለት። ይህን ከሰማ ቡኋላ ለሙሳ (ዐ.ሰ) እንደወረደው ያለ ተመሳሳይ ጅብሪል እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ አለ።

ከጥቂት ቀናት ቡኋላ ወደ ሂራ ዋሻ አቀኑና የመጀመሪያውን የቁርአን ወህይ ማለትም አምስቶቹ የሱራ አል-አቅ አናቅፅቶች ተገለፁላቸው።

እነዚህ 5 አናቅፅቶች በኢስላም የማንበብ መለኮታዊ ጥቅምን የሚያሳዩ አናቅፅቶች ናቸው።

አል-ቁርአን

ሱረቱል አለቅ 96:1-5

“አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ ያ ሰውን በብርዕ ያስተማረ፡፡ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡”

0%
5
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ስለ ነብዩ ሙሐመድ ምን ያህል ያውቃሉ?

ስለ ነብዩ ሙሐመድ ሕይወት ከቀረቡት ከሚከተሉት ጥያቄዎች ውስጥ ስንቱን በትክክል መመለስ እንደሚችሉ  እራስወን ይፈትሹ።

1 / 9

Bookmark question icon

1 ነብዩ ሙሐመድ የተወለዱት በየትኛው ከተማ ነው?

2 / 9

Bookmark question icon

2 የነብዩ ቅድመ አያት ማን ነበሩ?

3 / 9

Bookmark question icon

3 ‹ዓመል ፊል› (የዝሆኑ ዓመት) ተብሎ የተሰየመው ከሚከተሉት በየትኛው በተሰነዘረ ጥቃት ነው?

4 / 9

Bookmark question icon

4 በ‹ዓመል ፊል› (የዝሆኑ ዓመት) ጥቃቱ የተፈጸመው በየትኛው ወር ነበር?

5 / 9

Bookmark question icon

5 ነብዩ ሙሐመድን በልጅነታቸው ስትንከባከብ ያገዘችው አገልጋይ ማን ትባላለች?

6 / 9

Bookmark question icon

6 ነብዩ ሙሐመድ በልጅነታቸው ከገጠር (ከበደዊኖች) ጋር እንዲያድጉ ከመካ በተላኩ ጊዜ፣ ያጠባቻቸው ሞግዚት (አጥቢ) ማን ትባላለች?

7 / 9

Bookmark question icon

7 ኸዲጃ (አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና) ከጋብቻቸው በፊት ከነብዩ ጋር ለንግድ የላከችው አገልጋይ ማን ይባላል?

8 / 9

Bookmark question icon

8 ነብዩ የተወለዱት በየትኛው ወር ነው?

9 / 9

Bookmark question icon

9 እስልምናን የተቀበለ የመጀመሪያው ነፃ የወጣ ባሪያ ማን ነበር?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 12%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ሶላት

ጅብሪል (ዐ.ሰ) ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ከሂራ ዋሻ ከተራራው ስር ወሰዳቸውና ጅብሪል (ዐ.ሰ) ራሱ ውዱእ አደርጎ አሳያቸው።

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ልክ እንደ ጅብሪል (ዐ.ሰ) በተመሳሳይ መንገድ ውዱእ አደረጉ። ጅብሪል (ዐ.ሰ) ኢማም ሆኖ ሶላት አብረው ሰገዱ።

የነብዩ ሙሐመድ የስብከት ጅማሮ

ከጅብሪል (ዐ.ሰ) ጋር የመጀመሪያ ሶላት ከሰገዱ ብኋላ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤታቸው ተመልሰው ውድ ሚስታቸውን ኸድጃን መስበክ ጀመሩ።

ይች ሴት የመጀመሪያዋ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊም ሚስት ሆነች። ኢስላምን እንደተቀበለች ሶላቷን መስገድ ጀመረች።

አልይ (ረ.ዐ) የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአጐታቸው ልጅ ፣ አቡበክር ሲዲቅ (ረ.ዐ) ሁሉም በመጀመሪያው ቀን ኢስላምን ተቀበሉ።

የነሱ ወደ ኢስላም መግባት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ታላቅነት ፣ ቅድስና ፣ ደግነትቸውንና መልካምነታቸውን ያረጋገጠ ነበር።

በመቀጠልም አሏህ በሱራ አል-ሒጀር ላይ በግልፅ ይሰብኩ ዘንድ ደነገገባቸው። በመጀመሪያ ደረጃ ቤተሰባቸውንና ወዳጅ ዘመዳቸውን ወደ ኢስላም ይጣሩ ዘንድ በሱረቱል አሹራ 214 ላይ አሏህ አዘዛቸው።

አረመኔዎች በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ያደረጉት ዘመቻ

የሰው ልጆች የሁል ጊዜም አርአያ ፣ ተምሳሌት የሆኑት የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ ይህ ነው። የአረመኔዎችን ማህበራዊ ክፋት ፣ ሃጢያት ፣ ጣኦት አምላኪነትንና የአሏህን አንድነት ስላስተማሩ የመካ ሙሽሪኮች አምርረው በመቃወም በጣም ከባድና የከፋ ዘመቻቸውን በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ከፈቱ።

በቻሉት አቅም በተለያዩ ጊዚያት ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) አወገዙ ፣ ተሳደቡ። ሙሐመድ በጅኒዎች የተለከፈ እብድ ነው አሉ። ሙሐመድ ጠንቋይ ፣ ድግምተኛ ፣ ገጣሚ ነው ሲሉም ተሳደቡ።

ይሁንእንጂ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በፅናት የኢስላምን መልዕክት ለሁሉም የሰው ልጆች ማድረሳቸውን ቀጠሉ።

በእያንዳንዱ ስብሰባ ፣ በእያንዳንዱ በአል ፣ በእያንዳንዱ አውራጎዳና ፣ በእያንዳንዱ የእግር መንገድ የአሏህን አንድነትን በህዝባቸው ላይ ያሰርፁ ጀመር።

ከእምነተ ቢስነት ፣ ከዝሙት ፣ ከጣኦት አምላኪነት ፣ ሴት ልጆችን በህይወት መቅበርን እና ቁማርተኝነትን ከለከሏቸው።

0%
5
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ጥያቄና መልስ፡ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ 2

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት ታሪክ 2 ፈተና 7 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 6 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 7

Bookmark question icon

1 የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሞቱት በረቢኡል አወል ወር ሰኞ ቀን _____ አመት ነው።

2 / 7

Bookmark question icon

2 በሒጅራ በሶስተኛው አመት ላይ የተካሄደው ጦርነት የትኛው ነው?

3 / 7

Bookmark question icon

3 በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ መሰረት የሚከተሉትን ክስተቶች ከሩቁ ወደ ቅርቡ ሰድረህ አስቀምጥ?
የአቀባ ቃልኪዳን
ይፋዊ ጥሪ
ወደ አቢሲንያ (ኢትዮጲያ) የተደረገው ስደት
ኢስራዕ እና ሚዕራጅ
ሚስጥራዊ ጥሪ (ዳዕዋ)

4 / 7

Bookmark question icon

4 የሚከተሉትን ጦርነቶች በቅደም ተከተላቸው ከሩቁ ወደ ቅርቡ ክስተት ሰድረህ (አስተካክለህ) አስቀምጥ?
የአህዛብ ጦርነት
የበኒ ነዲር ጦርነት
የኡሁድ ጦርነት
የኸይበር ጦርነት
ታላቁ የበድር ጦርነት

5 / 7

Bookmark question icon

5 የኢስራዕ እና ሚዕራጅ ክስተት የተፈፀመው

6 / 7

Bookmark question icon

6 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩት በስንት አመታቸው ነው?

7 / 7

Bookmark question icon

7 ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ወደ መዲና የተሰደደው ማን ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 15%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ነብዩ ሙሐመድ

ነብዩ ሙሐመድ

ሙስሊም ሰው ከነብዩ ሙሐመድ ዝርዝር ታሪኮች ጋር እራሱን ማስተዋወቅ አለበት። ያ ሲሆን በሁሉም የህይወት ጉዳዮች ምሳሌነታቸውን መከተል ይችላል። ምክኒያቱም የህይወት ታሪካቸው ተጨባጭ የእስልምና እና የህግጋቱ

Read More »
የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

አሏህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት እና ስብዕናዎች ከሁሉ የተለዩ አድርጓቸዋል። ይህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት ልቦች በፍቅራቸው እና በውዳሴያቸው እንዲነጉዱ ያደርጋል። በዚህ ጽሁፉ ውስጥ ከእነዚህ ባህሪያት የተወሰኑትን

Read More »

የነብዩ ሙሐመድ መልዕክት

ሃያሉ አሏህ መልዕክተኞችን ከላቀ ጥበብ ጋር የላካቸው ሲሆን ነብዩ ሙሐመድ ከሁሉም በላይ አልቆ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ (ማብቂያ) አድርጓቸዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ እነዚህንም ጥበቦች እና ነብዩ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share