በጣም የምወደው ታናሹ ወንድሜ፤
ይፈካከረኛል ሳይቀር በህመሜ፤

ስበላ ከበላ ሳቆምም ከበቃው፤
ሀሙስ ሰኞን ፁሜ ፆምን ላስለምደው፤
ረመዷን ሲመጣ ምንም እንዳይከብደው፤

አርሰናል ስለው ማንቼ ካለኝማ፤
ለአምስት ወቅት ሰላት ምንም ሳላቅማማ፤
ልቁም ይየኝ እስኪ እሱም ይቁማ፤
እንዳይጨነቅብኝ በየውመል ቂያማ፤

ፀጉሬን ሳሳድግ ፀጉሩን ካሳደገ፤
ሱሪየን ሳስረዝም እሱም ካስረዘመ

እኔን በመከተል ሁሉን ካደረገ፤

እስኪ ቁርአን ልቅራ፤
እሱም እንዲቀራ፤
እንዲሰለፍልኝ ከአዋቂዎች ጎራ፤
ሐዲሶችን ላንብብ ሁኜ ከሱጋራ፤
አንድ ላይ አንድንሆን በጀነቱ ስፍራ፤

አንተም ለወንድምህ ሁንለት ጠንቃቃ!!!

እህቴም ለታናሽሽ ሁኝላት ተምሳሌት፤
በሱና ያደገች ሐዲሱን በመስማት፤

ቁርአን የምትቀራ በቀንና ሌሊት፤
የሶላት ጊዜ ፍፁም የማያልፋት፤

ሁኝላት ተምሳሌት እንድትሆን በኢማን ያማረች፤
ወንጀልን በመራቅ ጀነትን ያገኘች፤

ሁሉም በየቤቱ ይህን ካደረገ፤

የመጭውን ትውልድ ህይወቱን ታደገ፤

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top