ልቡ ጥሩ አሳቢ ምላሱ የገራ፤
ብዙ የሚሠማ ትንሽ የሚያወራ፤

ፊቱ በተዋዱዕ በኢማን ያበራ፤
ፈገግታው የሚስብ ከሩቅ የሚጣራ፤

በፈርዱ የቆመ ከሱናውም ያለ፤
ደበረኝ ሰለቸኝ ደከመኝ ያላለ፤

ለረጅሙ ጉዞ ጥሩን የሰነቀ፤
ለማይቀረው ዓለም መሄዱን ያወቀ፤

ፀባዩ የሚጥም ወግ አመሉ ሸጋ፤
እኔስ ሰው ጠፍቶኛል እንሂድ ፍለጋ፤

ልቤን ሰው ሰው አለው የኢማን ጋደኛ፤
ቀኑን ፁሞ የሚውል ሌሊቱን የማይተኛ፤

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top