ድቅድቁን ጨለማ ከላይ ሰመለከት፤
ከርቀት አየሁኝ የካንፓስ ከዋክብት፤
ብርሃን ጨረሯ ልብን ይማርካል፤
አለው ልዩ ውበት ከርቀት ይስባል፤
ውስጤንም ጠየኩት ማናት ያቺ ኮከብ፤
በካምፓስ አድማስ ላይ የለበሰች ጅልባብ፤
ብርሃን ጨረሯ ልብን ይማርካል፤
አለው ልዩ መስህብ ከርቀት ይስባል፤
በካንፓስ ጎዳና ስመለከት ሂጃብ ፤
በእውነት ድንቅነው አለው ልዩ መስህብ፤
የካንፓስ ከዋክብት ሂጃብና ጅልባብ፤
ደምቀው ይታያሉ ላስተዋለው ከልብ፤
የከዋክብት ጥቅም በቁርአን ተብራርቷል፤
አላማና ጥቅሙ በደምብ ተቀምጧል፤
የቅርቢቱን ሰማይ ለማስጌጥ ታስቦ፤
ሸይጧንን ለመምታት በነበልባል ችቦ፤
መንገድን ለመምርት የባህር ቀዛፊን፤
በነፍስያ ማዕበል እንዳንሰምጥ በፋሽን፤
በሂጃብ ብርሃን ለመምራት ህዝቦችን፤
በኢስላም መፍትሄ ለሰው ልጆች መድህን፤
የማታ ኮከቦች የቀን ተምሳሌት ፀሃይ፤
ቃሉን ተቀብለው መለኮታዊ ራዕይ፤
ነፀብራቅ ሆነዋል ለካንፓሱ ሰማይ፤
ጨለማው ይገፈፍ በጅልባቡ ብርሃን፤
የዛሬዋ ኮከብ የነገ ሁረልአይን፤
በሂጃብሽ በርቺ ጀነትን አስበሽ፤
ዳዕዋሽ ይድረሳቸው ሰዎች ይመልከቱሽ፤
ሀያዕን ሳትረሺ አኽላቅሽን ተላብሰሽ፤
በሰለፎች መንገድ ከኢህጢላጥ ርቀሽ፤
በካንፓስ ውስጥ አብሪ ከዋክብት ሆነሽ፤
በካንፓስ ውስጥ አብሪ ከዋክብት ሆነሽ፤