ሂጃቤ ውበቴ ሂጃቤ ነፃነቴ

በቀላሉ ባለባበሴ ምክኒያት እኔን ተመልክታችሁ ጭቁን ስትሉ ትጠሩኛላችሁ። ከውስጤ ያለውን ሳታውቁ በኩራት የለበስኩትን ልብስ ትገመግማላችሁ። አካሌ ለእናንተ እይታ አይደለም፤ ለሰውነቴ ሳይሆን ለአይምሮየ ልታናግሩት ይገባል።

እኔ የወንድ ባሪያ ያላደለሁ አንድ ግለሰብ ነኝ። ለፈጣሪየ ትአዛዝ ተገዥ ነኝ። በጣም የምጓጓለት እና የምመኘው የአሏህን ውዴታ ነው፤ በልቤ ውስጥ ቃላቶቹን ይዣለሁ፤ ድምፅም አለኝ እሰማለሁ።

“እናተ ሴቶች ሆይ በደንቆሮዎች እንዳትቸገሩ እራሳችሁን ሸፋፍኑ!”

ወንድ እንዴት መልበስ እንዳለብኝ የሚነግረኝ ሳይሆን ከአሏህ የሆነ የማከብረው እና ለትእዛዙም ተገዥ የምሆንለት ህግ ነው። ጭቁን አንድ ነገር ነው፤ እኔ ግን ጭቁን አይደለሁም፤ በራሴ ምርጫ እና ፍላጎት የማደርገው አለባበሴ ነው።

እህቴ ይህን ከብዙ አመት በፊት ኢስላም ላንችም ለኔም የሰጠን ነፃነታችን ነው።

ይህ አለባበሴ በአንድ አሊም ወይም ሸኽ የተጣለብኝ ግዴታ ሳይሆን መለኮታዊ ትእዛዝ ነው። እናም እህቶቼ ለአሏህ ትእዛዝ እራሳችነን ተገዥ እናድርግ ማንነታችነን እንጠብቅ።

አሏህ ህይወታቸውን በቁርአን እና በሐዲስ ብቻ ከሚመሩት መካከል ያድርገን። አሚን!!!

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top