እህትነት እና ልባዊ የእህትነት ውዴታ

Author picture
እህትነት እና ልባዊ የእህትነት ውዴታ ከኢስላም የመመሪያ ብርሃን የሚመነጭ ግኑኝነት ወይም ማህበሪዊ ትስስር ሲሆን ይህ ፍቅር በማንኛውም አለማዊ አና ስውር በሆነ ጥቅም ያልተመረዘ ነው።
እህትነት እና ልባዊ የእህትነት ውዴታ

እህትነት እና ልባዊ የእህትነት ውዴታ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

እህትነት እና ልባዊ የእህትነት ውዴታ ከኢስላም የመመሪያ ብርሃን የሚመነጭ ግኑኝነት ወይም ማህበሪዊ ትስስር ሲሆን ይህ ፍቅር በማንኛውም አለማዊ አና ስውር በሆነ ጥቅም ያልተመረዘ ነው።

አንዲትን ሙስሊም ሴት ጁኦግሪፊያዊ መነሻ ፣ ጎሳ ፣ የቆዳ ቀለም ፣ የአይን ቀለም ወይም የፀጉር ቴክስቸር እና ቋንቋ ሳይገድባት ከእህቶቿ ጋር ልብ ለ ልብ የሚያስተሳስር ብቸኛ ሰንሰለት ነው። ሰንሰለቱም መሰረት ያደረገው የአሏህን (ሱ.ወ.ተ) የእምነት ገመድ ላይ ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሑጅራት 49:10)

“አማኞች ወንድማማቾች ናቸው። በመካከላቸውም እርቅን ፍጠሩ። እናም ምህረትን ታገኙ ዘንድ አሏህን ፍሩ።”

ይህ ፍቅር አንዱ የእምነት ጥፍጥና መገለጫ ነው።

አነስ (ረዐ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) የሚከተሉት ሶስት ባህሪያቶች ያሉት ሰው የእምነት ጥፍጥና ይኖረዋል ብለዋል። {አል-ቡኻሪ ጥራዝ 1 መጽሃፍ 1 የሐዲስ ቁጥር 15}

  • አሏህ እና መልእክተኛው ከማንኛውም ነገር በላይ ውድ የሆኑለት
  • ሰውን የሚወድና ውዴታውም ለአሏህ ብሎ የሆነ
  • ወደ ጀሃነም እሳት መወርወር እንዲሚጠላ ሁሉ መክፍርን (መጥመምን) የሚጠላ የሆነ

እናም ይህ ፍቅር እውቅናን ፣ ስልጣንን ፣ ዝናን እና ክብርን ለማግኘት ተብሎ ያልሆነ ሲሆን ንፁህ እና ብርሃን የሆነ ቀልብን የሚፈልግ ውዴታ ነው። ከሰው ልብ ጥላቻን ፣ ቅናትን እና ባላንጣነትን ለማጥፈት ብቸኛው መንገድ ለአሏህ ብሎ መዋደድ ነው።

እናም ውድ ሙስሊም እህቶቼ አሏህ በእሱ መንገድ ከተዋደዱት፤ በእሱም መንገድ ተባብረው ከሚሰሩትና አርሽ ጥላ ስር ከሚቀመጡት፤ አብረው ከሚቀሰቀሱትም ያድርገን። አሏህ ኢማን እና ተቅዋን ያጎናፅፈን። አሚን!! እኔ ለአሏህ ብየ እወዳችኋለሁ!!!

Related posts

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share