ከፍርዱ ቀን በፊት የሚከሰቱ ምልክቶች አሉ። ነገርግን ለሰአቱ በጣም የቀረቡ አይደሉም። ይልቁንም የሚከሰቱት በተለያየ ጊዜያት ነው። አንዳንዶቹ ቀድመው ተከስተዋል።
የጨረቃ መሰንጠቅ
“ሰአቷ ተቃርባለች፤ ጨረቃዋም (ከሁለት) ተሰንጥቃለች”
(አል-ቁርአን 54፡1)
ይህ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ሁሉም አይተዋታል።
በሞንጎሎች እና በታርታርስ ሚከፈት ጦርነት
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ፀጉራም ጫማ የሚለብሱ ሰዎችን እና ትንሽየ አይኖች ፣ ቀይ ፊት እና ደፍጣጣ አፍንጫ እና ፊታቸው ልክ እንደ ዝርግ ጋሻ የሚመስል ፊት ያላቸውን ቱርኮች እስካልተፋለማችሁ ድረስ ሰአቷ አትመጣም።” (ቡኻሪ)
እንደ ሙሑራኖች ገለፃ ይህ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ የሙስሊሙ አለም ያጠቁ ታታሮች ከሂጅራ በኋላ በ656ዓ.ሂ ሙስሊሞችን ያሸነፉ እና ሙስሊሞችም በ658ዓ.ሂ ኤን ጀሉት ጦር ሜዳ ላይ ያሸነፉበት የታሪክ ክስተት ጋር የሚገጥም ነው ብለዋል።
የሂጃዝ እሳት
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ከሂጃዝ ምድር እሳት እስካልታየ ፣ በስራ ውስጥ ከግመል አንገቶች ላይ ብርሃኑን ወርውሮ እስካልታየ ድረስ ሰአቷ አትመጣም።” ብለዋል። (ቡኻሪ)
በእርግጥ ይህ እሳት ጁምአ ስድስተኛው ጁማዱል አሂር 654ዓ.ሂ ተነስቷል። አስጊ በሆነ ፍጥነት በየቦታው ተዛምቷል። ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ እስኪያበቃም ሶስት ወር ወስዷል።
የፐርዥያና የሮም አገዛዝ ውደቀት
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ኸስራው በሞተ ጊዜ ሌላ ኸስራ አይኖርም። ሴዛር በሞተ ጊዜ ሌላ ሴዛር ከእሱ በኋላ አይኖርም።” (ቡኻሪ)
በአሁኑ ጊዜ የሚታዩ ብዙ ጥቃቅን ወይም ትናንሽ ምልክቶች አሉ።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ “ከሰአቷ ምልክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። ሃይማኖታዊ እውቀት ይጠፋል፤ ድንቁርና ይስፋፋል ፣ የአልኮል መጠጥ መጠጣት ይስፋፋል ፣ ዝሙት ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል።” (ቡኻሪና ሙስሊም)
በቡኻሪና በሙስሊም በተዘገቡ ሌሎች ሐዲሶች የሚከተሉት ምልክቶች እንዳሉም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተጠቅሰዋል
ሀ. ብዙ ደም መፋሰስ እና የመሬት መንቀጥቀወቀጥ ይኖራል
ለ. ስግብግብነት በሰዎች ልብ ውስጥ ይነግሳል
ሐ. ፈተና እና ውጣውረድ መመከራው ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል
መ. ሴቶች ወንዶችን በቁጥር ይበልጣሉ
የፍርዱ ቀን ትናንሽ ምልክቶች አንዳንዶቹ ገና አልተከሰቱም ለምሳሌ
ሀ. ሙስሊሞች ይሁዳዎችን ፈለስጢን ውስጥ እንደሚዋጓቸውና እንደሚያሸንፏቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሰአቷ አትመጣም ሙስሊሞች ይሁዳዎችን እስካልተዋጓቸውና እስካልገደሏቸው ድረስ” ብለዋል። (ቡኻሪና ሙስሊም)
ለ. የኤፍራጠስ ሃብት፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሰአቷ አትመጣም ኤፍራጠስ ሰዎች የሚጋደሉበትን የወርቅ ተራራውን እስካልገለጠ ድረስ” ብለዋል። (ቡኻሪና ሙስሊም)
ሐ. በሶሪያ ሰሜኑ ክፍል ከሁለተኛው የኮንስታንቲኖፕል ድል በፊት በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች ደም የሚፋሰሱበት ጦርነት ይኖራል።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ‹ሰአቷ አትወጣም ሮማውያኖች አመቅ እና ዳቢቅ እስካላረፉ ድረስ” ብለዋል። (ሙስሊም) ዳቢቅ በአሌፓ አቅራቢያ የሚገኝ መንደር ሲሆን አመቅ ደግሞ በዳቢቅ አቅራቢያ በአሌፓ እና በአንቲየክ መካከል የሚገኝ አውራጃ ነው።
(አላመቱ ሰአ አል-ኩብራ፤ የፍርዱ ቀን ትልልቅ ምልክቶች ተመልከቱ)