ይቺ አታላይ

ለከፊሉ እስር ቤት ለቀሪውም ገነት፤
ከፈጣሪዋ ዘንድ እንስ ያለች መሬት፤

ዱንያ ዋጋ ቢሷ ከህልም ያላለፈች፤
በእቅድ በምኞት በባዶ የተሞላች፤
እኛንም ጠራርጋ ገደል ይዛን ገባች፤

አይይቀሬውን ጉዳይ ሞትን አስረስታ፤
በብልጭልጭ ነገር ዳንኪራ አስመትታ፤
ከዚያ ከሠፊ አገር ላታስቀር ጎትታ፤

ከሞት ከሚያስፈራው ከቀብር ጨለማ፤
የዘመድን ጥሪ ከማያሠማ፤

ጌታህ ማነው ከሚል ከከባባድ ጥያቄ፤
ቀረኝ ከማያስብል ወይ ጨርቄን ማቄ፤

ከመቃብር ጭንቀት ከጠለቀው ጉድጏድ፤
አናት ከሚበሳው ከፀሃዩ ንዳድ፤

በየወንጀሉ ልክ ላብን ከሚጠምቀው፤
የጎን አጥንት ከሚያስተላልፈው፤

እናትና ልጅን ከሚያፈራርደው፤
በአፍጢም እየደፋ እሳት ከሚጥለው፤
በባለሠው እሳት ድንጋይ ባነደደው፤
እያገላበጠ ስጋን ከሚጠብሰው፤

ከዘወትር መኖሪያ ማረፊያ ከሌለው፤
መጽሐፍ ቢታተም ፅሁፍ ከማይገልፀው፤
ከዚያ ከሠፊ ሐገር ማንም ከማይቀረው፤

ዱንያ አዘናግታ አስረግጣን ጮቤ፤
ዛሬ ላይ ደረስን ስንል ምንድነው ሃሳቤ፤

አደም ልጆች ሆይ አናንቀላፋ፤
ነቃ እንበልና ለአኼራ እንልፋ፤

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top