ውበትሽ ነው ላንቺ ክብር መጠበቂያ፤
ወንድ ላይሳሳት ውበት መደበቂያ፤
ቀልቡ እንዳይሰበር ልቡ እንዳይሸፍት፤
እባክሽ ልበሽው ጥቅም አለው እህት፤
አይቀርም ቂያማ አብረሽ መጠየቅሽ፤
በሠራሽው ጥፋት አብረሽ መቀጣትሽ፤
ስለሂጃብ ጠንቅቀው የማያውቁ፤
አስፈላጊ አይደለም ብለው ሲያስወልቁ፤
ጥፋቱ ባንድነው በነሱ አንለጥፈው፤
ትልቅ ጥፋትስ ያለው ወደዚህ ነው፤
በቀለም አሸብርቆ ደምቆ አብረቅርቆ፤
ከአካልሽ ጋር እንደሙጫ ተጣብቆ፤
ይሄ ሂጃብ አይደል ድሮም አልተባለ፤
ያኔ የተባለው የተስተካከለ፤
በጣም ያልደመቀ ያልተጠባበቀ፤
በጌጣጌጥ ብዛት ያልተብረቀረቀ፤
ልበሱ የተባለው ይህንን ነው እህት፤
የለበሱ አሉ ትዕዛዝ ያከበሩ፤
ለአሏህ ትልቅነት ለዕውነት ያደሩ፤
ኢስላም ያከብርሿል ውዲቷ እህቴ፤
ለጋራ ጥቅም ነው እኔስ መወትወቴ፤
አሏህ ይጠብቀን ከአሳሳች ነገራት፤
ሂጃብሽን ልበሽው ነቅተሽ በዚህ ሰዓት፤
ሂጃብሽን ልበሽው ነቅተሽ በዚህ ሰዓት፤