ወጣትነት እና ፍቅር

ወጣትነት እና ፍቅር ፡ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

  • ፍቅር ማለት አንድን ነገር አብልጦ መውደድ ማለት ነው።
  • አንድን ነገር ካለሱ ወይም ካለሷ ማድረግ አለመቻል ነው።
  • ሚስትን ወይም ባልን አዘውትሮ ማሰብ ነው።
  • በደስታም ሆነ በችግር ጊዜ አብሮ መሆን ነው።
  • ከባል ወይም ከሚስት ውጭ ሲሆኑ መደሰት አለመቻል ነው ወ.ዘ.ተ

ሲጀመር አንድ ሰው ፍቅር ሊያዝባቸው የሚችሉ በርካታ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ አሏህ ፣ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ፣ የአሏህ ባሮች ፣ እናት ፣ አባት ፣ እህት ፣ ወንድም ፣ ሚስት ወ.ዘ.ተ ነገር ግን ዛሬ ልዳስስ የምንፈልገው እኛ ወጣቶች ከሌላው በተለየ ስለሚያስደስተንና ስለሚፈትነን የፍቅር አይነት ነው። ማለቴ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ስላለን ግንኙነት በተመለከተ ነው።

ወጣቶችን ምርኮኛ የሚያደርጉ የዚህ ዘመን ወጥመዶች እና ፈተናዎች ከጊዜና ከቴክኖሎጅ መስፋፋት ጋር ተያይዞ እጅግ በጣም በርካታ ሆነዋል። ሆኖም እኛ ወጣቶች ይህን አውቀን ልንጠነቀቃቸውና ልንርቃቸው ይገባል።

የመጀመሪያው ወጥመድ የሴቶች ተንኮል ነው። እዚህ ላይ ተንኮል ስል የመፈተኛ መንገድ ማለቴ ነው። ሴቶች ሊያስውባቸውና ተቃራኒን ፆታ ሊያማልል የሚችል ማንኛውንም ነገር ሁሉ ያደርጋሉ።

ለዛምነው አንዳንድ ሴቶች ልብሳቸው ትንሽ ሰፋ ካለች ያስጠብቧትና ከሰውነታቸው ጋር ተላካ የሰውነታቸው ቅርፅ እንዲታይላቸው የሚያደርጉት።

አንዳንድ ሳይሞቅ ፈላ የሆኑ ሴቶች ደግሞ ጡት ሳይኖራቸው የጡት ማስያዧ የሚለብሱም አይጠፉም። ሜካፕ ፣ ቻፕስቲክ ፣ የቅንድብ ኩል ወ.ዘ.ተ ማቴርያሎች በፖርሳቸው ይዘው በየደረሱበትና ባረፉበት ቦታ ሁሉ ከፖርሳቸው እያወጡ መኳኳል ነው።

እነዚህ ነገራቶች ሃራም ከመሆናቸውም በላይ ወንዶችን ወደ ዝሙት መጥሪያ ደወሎች ናቸው። አሏህ የሰው ልጅን ባማረ አቋም ላይ ፈጥሮት እያለ የተፈጥሮን ውበት በሰው ሰራሽ መለወጥ ለምን አስፈለገ?

ሌላኛው ወጥመድ ሴቶችን ማዕከል ያደረጉ መዝናኛዎች ፣ ማስታወቂያዎች ፣ የፊልምና የሙዚቃ እንዱስትሪዎች ፣ የፋሽን ልብሶች ፣ የመረጃ አውታሮች ፣ ስፖርት ፣ የቴሌቪዥን ቻናሎች ወ.ዘ.ተ ናቸው።

ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮች ተቃራኒ ፆታ ያላቸውን ሰዎች በሃራም ነገሮች ላይ እንዲዘወትሩ ወደ ዝሙት በከፍተኛ ዘመቻ ቅስቀሳ ያደርጋሉ።

እናም ብዙ ወጣቶች በዚህ ችግር ላይ ሲወድቁ ይስተዋላል። በተለይ ቅልቅል የሆነ ማህበራዊ ህይወት ውስጥ ችግሩ እጥፍ ነው።

መቼም እኛ የተፈጠርነው ከስጋና ከደም እንዲሁም ከአጥንት እንጅ ከድንጋይና ከብረት አይደለም። ሆኖም በተለያዩ ነገሮች የተደረገልን ጥሪ እና ግፊት መቋቋም ሊሳነን ይችላል።

አልፎ ተርፎ በጣም ከባድ ወደ ሆነ የተቃራኒ ፆታ ፍላጎት ውስጥ የምንገባበት ጊዜ ይኖራል። ይሁን እንጂ ይህ ከመከሰቱ በፊት እራሳችነን ወደዚህ አይነት ነገር የሚገፋፉውንን ነገሮች መጠንቀቅና ሙሉ በሙሉ መራቅ ይኖርብናል።

በወንድና በሴት መካከል ያለው ግንኙነት የትም አለም ቢሆን ያልተገደበ ነፃነት አላቸው ማለት አይደለም። ከጋብቻ በፊት ያለውን የወንድና የሴት ልጅን ግንኙነት የሚገድቡ የሃይማኖት ህጎች ፣ የማህበረሰቡ ወግ ልማድ እና ባህል ይኖራል።

በሌላ በኩል ደግሞ በውስጡ ያለ ፍላጎት ያስቸግረዋል። በእርግጥ ችግሩ አሳሳቢና ትልቅ ነው። ይሁን እንጅ ተስፋቢስ መሆን የለብንም ምክኒያቱም ሃይማኖታችን ለሁሉም ችግሮቻችን መፍትሄዎችን አመላክቶናል ወደ ቀጥተኛውም ነገር መርቶናልና።

ለዚህ ችግር ቁርአን መፍትሄዎችን ይዞልናል። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለብን አሳውቀውናል።

ሃይማኖታዊ ህግጋቶችን ያለ ምንም መፃረር እና ተቃርኖ እንዴት መጠበቅ እንዳለብን፤ በውስጣችን ያለውን ስሜት እንዴት ማርካት እንደምንችል አመላክተውናል።

እኛ ተገቢዎች የምንሆነው ለስሜታችን ሳይሆን ለፈጠረን ጌታ ለአምላካችን አሏህ ነው። አለምን ካልነበረ ነገር ፈጥሮ ይህን ዩኒቨርስ ያስዋበ ለሆነው።

ከፍጥረታቶች ሁሉ አልቆ በመፍጠር ፍቅርን ሰጠን እናም በመጀመሪያ ደረጃ ፍቅር የሚለውን ነገር ሊኖረን የሚገባው ከአሏህ (ሱ.ወ.ተ) ጋር ነው። ባይፈጥረን ኖሮ ማፍቀርንም ሆነ መፈቀርን እንዲሁም የምንወዳቸውን ሰዎች ባላወቅናቸው ነበርና።

ውብ ፣ ማራኪ ፣ መልከመልካም ፣ ቆንጆ የሚሉትን ነገሮች በምንወደው ሰው ላይ የምናገኘው አሏህ አሳምሮ ስለፈጠራቸው ነው። አይደል እንዴ? ከሆነ በመጀመሪያ አሳምሮ የፈጠራቸውን አሏሁ አዘወጀልን ልንወድና ለትዕዛዙ ታዛዥ ልንሆን ለከለከለው ነገር ባሪያ ልንሆን ግድ ነው።

አሏህ እንድንወድ ያዘዘንን ነገር መውደድ እንድንጠላ ያዘዘንን ነገር መጥላት ይኖርብናል። እናም አሏህን እና ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) በማፍቀር ፣ እስልምናን በማወቅና ህይወታችነን በኢስላም አስተምህሮት መሠረት በመምራት ወደ ዝሙት የሚጣሩ ነገሮችን በቀላል መንገድ ማሸነፍ እንችላለን።

አንዳንድ ወጣት አፍቃሪዎች ማንኛውም ነገር በፍቅረኛቸው ዙርያ እንደሚገኝ ወይም እሱ ወይም እሷ የማንኛውም ነገር ማዕከል አድርገው ሊያስቡ ይችላሉ። ፍቅር ፣ ሰላም ፣ ደስታ ፣ መረጋጋት በፍቅረኛቸው ዙርያ እንደሆነም ያስባሉ።

በመካከላቸው ጠብ ተፈጠረ ማለት ወይም ተኮራረፉ ማለት አለም እንደፈራረሰች ህይወት የሚባል ነገር የቆመ ያህል ያስመስሉታል።

እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። አሁን አሁን ፍቅር ብለው የሚለፍፉት ነገር ጊዜያዊ የወሲብ ፍላጎት ማግኛ የሸይጧን ጩኸት እንጅ ሌላ አይደለም።

ውበት ፣ ደስታ ፣ ሰላም ፣ ተክለ ሰውነት ፣ ህይወት ወ.ዘ.ተ ከፍቅረኛሞች መካከል አንዳቸው ይህን አለም ቢነጠሉ እነዚህ ነገሮች ይጠፋሉ ማለት አይደለም። አለም ወደፊት መጏዟን ትቀጥላለች፤ ዝናብም መዝነቡን፤ ወፎችም መዘመራቸውን ይቀጥላሉ።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top