እውቀት እና ወጣትነት

Author picture

Table of Contents

እውቀት እና ወጣትነት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

"በሽምግልና እድሜ የሚገኝ እውቀት ልክ በውሃ ላይ እንደሚፅፍ ሰው ሲሆን በወጣትነት ጊዜ የሚገኝ እውቀት ደግሞ ልክ በድንጋይ ላይ እንዳለ ማህተም ነው።"

በወጣትነት ጊዜ የአእምሮ የመሸምደድ አቅም ከፍተኛ ነው። ለዛም ነው እውቀትን መሻት በልጅነት ጊዜ የሚጀምረው። እንዲሁም ቁርአንን የመሸምደድ ተግባር የሚጀምረው በልጅነት ጊዜ ነው።

ሱፍያን ቢን ኡየይና (ረ.ዐ) ሙሉ ቁርአንን የሃፈዘው በ4 ዓመቱ ነበር። በአሁኑ ወቅት እድሚያቸው ከ8-9 የሆኑ ልጆች ቁርአንን እያኸፈዙ ይገኛሉ።

በወጣትነት እድሜ እውቀትን መሻት አስፈላጊ የሚያደርገው ነገር የጊዜ ጉዳይ ነው። እውቀትን መሻት አትኩሮት ፣ ድግግሞሽ የሚፈልግ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ምቹ ጊዜ የወጣትነት እድሜ ነው።

ጊዜው ካለፈ በስራ መጠመድ ፣ ማግባት ፣ መውለድ ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር ይኖራል። ይህ ደግሞ እውቀት የምንሻበትን ጊዜ ይቀንስብናል፤ ምናልባት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ጊዜ እንዳይኖረን ሊያደርግ ይችላል።

እንዲሁም ጊዜው ካለፈ ፍላጐታችን ፣ አትኩሮታችን ፣ አዲስ ነገር የማወቅ ጉጉታችን እና ተነሳሽነታችን ብሎም የአእምሯችን የመያዝ አቅም ይዳከማል። ይሁን እንጂ እኛ ወጣቶች እውቀትን ለመሻት እንቅፋት የሆኑነን ብዙ ነገሮች ልንዘረረዝር እንችላለን።

በእርግጥም የወጣትነት ጊዜ አስቸጋሪ ነው። ይሁን እንጅ እውቀትን በመሻት ጉዳይ በጣም ወሳኝ እና ምቹ ጊዜ ቢኖር ደግሞ ይህ የዕድሜ ክልል ነው።

ከዚህም በላይ ነብያችን ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ከልጅነታችን እስከ እለተሞታችን ድረስ እውቀትን እንድንሻ መክረውናል። በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሠረት «እውቀትን መሻት በእያንዳደንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው» ብለዋል።

ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በሐዲሳቸው «ሁሉም ሰዎች ይሞታሉ አሊሞች ሲቀሩ፤ ሁሉም አሊሞች ይሞታሉ በእውቀታቸው የተስራሩት ሲቀሩ፤ እንዲሁም ሁሉም ይሞታሉ ቅኖች(ኢህላስ) ያላቸው ሲቀሩ» ብለዋል።

እዚህ ላይ ልንረዳው የሚገባ ነገር ቢኖር እውቀትን መሻት በራሱ በቂ አለመሆኑን እና ከቅንነት ጋር እውቀትን ወደ ተግባር መቀየር እንዳለብን ነው።

እውቀት የእስልምና ህይወት፤ የእምነቱ መሠረት ሲሆን እውቀትን ለሚሻ ሰው አሏህ ይመነዳዋል። በዱንያም በአሂራም ከፍ ያደርገዋል። የአሏህ ባሪያ እውቀትን በሻተ ቁጥር የማያውቀውን የበለጠ እንዲያውቅ ያደርገዋል።

እናም እውቀቱን በኢህላስ ወደ ተግባር የሚቀይር ሰው አዲስ እውቀትን በቀላሉ ያገኛል። አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል አል-ዐለቅ ከአንቀፅ 1 እስከ 5 ባለው እንዲህ ይለናል፦

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

“አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን፤ ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን፡፡”

{አል-ቁርአን 96:1-5}

ሌላው ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ትምህርት ወይም እውቀት በትምህርት ቤቶች (በመድረሳዎች) ብቻ የሚሰጥ ወይም የሚገኝ አድርገን ማሰብ አይኖርብንም።

በእርግጥ ከአሊሞች ጠጋ ብለን እውቀትን መከሰብ ከሁሉም ነገር በላይ በላጭ ነው! ይሁን እንጂ ነገሮች አልተመቻቹልንም በማለት እራሳችነን ከትምህርት አለም ማግለል አይኖርብነም።

ምን ለማለት ፈልጌ ነው በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እውቀት የትም ቦታ ይገኛል። ኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ሰዎች ከሀ-ፐ ትምህርት በwizq ፣ በIOU ፣ በunderstand Quran accadamy ይሰጣል ፤ በርካታ መፅሐፎች በpdf ፣ በHTML ፣ በEPU እና በapplication መልክ ይገኛሉ።

እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ጊዜያችነን በአግባቡ እንጠቀም! ስለዲናችን ያላወቅነውን ነገር ለማወቅ ጉጉት ፣ ተነሳሽነት እና አትኩሮት ይኑረን! የምናውቀውንም ነገር ወደ ተግባር እንቀይር!

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top