ማንኛውም ሰው ህይወቱን በተለያየ መንገድ ያሳልፋል። ነገር ግን ወሳኙ ጥያቄ የህይወቱን ሃቅ የሞላ ወይም የፈፀመ ማነው? የሚለው ነው።
እንስሳቶች የህይወታቸውን እያንዳንዷን ጊዜ እንዲሁ ያሳልፋሉ። ነገርግን ጊዜውን በጥበብ የተሰጠው የሰው ልጅ የተለያዩ ነገሮችን በመፈፀም ያሳልፋል።
ሆኖም ኩፋሮች የህይወታቸውን እያንዳንዷን ጊዜ ፅልመት በወረሰው ጠማማ መንገድ ላይ ሆነው ከቀጥተኛዋ የህይወት ጎዳና እንዳፈነገጡ ይንከራተታሉ።
ነገርግን የህይወት መመሪያቸውን በአሏህ መለኮታዊ መመሪያ ላይ ያደረጉ አማኞች ደህንነቱ በተጠበቀ ፣ ሰላምና መረጋጋት በሰፈነበት የህይወት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ።
ከሃዲያኖች ቀንና ሌሊታቸውን የሚያሳልፉት በመንፈሳዊ ፅልመት ሲሆን ሙእሚኖች ግን የቀንና የሌሊት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በመንፈሳዊ ብርሃን ነው።
ይህ ከሆነ አሁንም ሊነሳ የሚገባው ወሳኙ ጥያቄ ሙስሊሞች ከከሃዲያኖች ለመለየት እንዴት ነው የቀንና የሌሊት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ብሎ መጠየቁ አስፈላጊ ነው።
እኛ ሙስሊሞች ጊዜያችነን ከታች በተዘረዘረው መልኩ ማሳለፍ ይኖርብናል።
- ከማንኛውም የወንጀል አይነት በመቆጠብ
- ወንጀል ሲሰሩ ወዳው በመቶበት የአሏህን ሐቅ በመጠበቅ
- የወላጆቻችነን እና በዙርያችን ያሉ ሰዎችን ሃቅ በመጠበቅ
- መጥፎ ንግግርን በማስወገድ
- ስምና ዝናን ባለመፈለግሰዎች የሰራነውን ስህተት ሲነግሩን እራሳችነን ትክክለኛ አድርገን ለማቅረብ ከመሞከር ይልቅ ስህተታችነን ተቀብለን ተውበት በማድረግ
- እንቶ ፈንቶ ወሬዎችን ባለማውራትማንኛውንም አይነት ስራ ስንሰራ የሸሪአ ድንጋጌያቸውን በማስታወስ
- ማንኛውንም የኢባዳ አይነቶች ስንፈፅም ደከመኝ ሰለቸኝ ባለማለትከሌሎች ሰዎች ጋር ስንገናኝ ወይም ስንወያይ እራሳችነን ዝቅ በማድረግ ወይም በመተናነስ ወይም ደግሞ እኔ እበልጣለሁ የሚል ስሜት በማስወገድ
- ከከሃዲያኖች በመራቅየሰዎችን ስህተት ባለመፈለግና ለሰዎች መጥፎ ነገር ባለማሰብ
- የራሳችነን ስህተት በመመርመር ነፍሳችነን ወደ ኸይር ነገር በማመላከትሶላታችነን በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሱና መንገድ በወቅቱ ከተመስጦ (ከኹሹ) ጋር በመስገድ፤ የሱና ፆሞችን በመፆምና ቂያመለይል በመቆም
- በምላሳችነም ይሁን በቀልባችን አሏህን አብዝተን በማውሳትበትህትና በመናገር ወይም በመመለስ
- በዱንያ ጉዳይ ፣ በዱንያ ትርፍና ኪሳራ ሁልጊዜ ከመጨነቅ ይልቅ የአሏህን ሰፊ ችሮታ በማስተንተንየወንድሞቻችነን እና የህቶቻችነን ስህተት ባየን ወቅት በመደበቅ
- ምግብ አብዝተንም ሆነ በትንሹ አለመመገብአሏህ ለዋለለን ውለታ አመስጋኞች በመሆን
- እንግዶችን ፣ ምንገደኞችንና ኡለማዎችን በማገልገልሁሌም በምንሰራው ስራ ላይ አሏህን በመፍራት
- ሞትን በማስታወስውሸት ባለመናገር
- ሸርአዊ ድንጋጌን በሚጣሱበት ቦታና ስብሰባዎች ላይ ባለመካፈልእራስን በመልካም ስብዕና በማነፅና ሃያዕን በመላበስ
- አሏህ ፍፃሜያችነን እንዲያሳምርልን በመለመንዱአና ስቲግፋር በማብዛት
- ቁርአን አዘውትረን በመቅራትያወቅነውን ነገር ለሌሎች እህት ወንድሞቻችን በማካፈል
- በቻልነው አቅም የምንሰራቸውን ስራዎች በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱና መሰረት በማድረግና በኢህላስ በመስራትዝምድናን በመቀጠል
- ከመተኛታችን በፊት ስንሰራ የዋልናቸውንና ስንሰራ ያመሸናቸውን ነገሮች አስበን ለሰራናቸው መልካም ነገሮች አሏህን ማመስገንና ለሰራናቸው ስህተቶች ደግሞ የአሏህን መሃርታ መለመን ይኖርብናል።

