በአንድ ወቅት ሴቶች ብቻ ስለትዳር ህወታቸው የሚወያዩበት እና ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ ላይ "ምን ያህሎቻችሁ ባላችሁን ትወዳላችሁ?" ተበለው ተጠየቁ።
ለፈገግታ

በአንድ ወቅት ሴቶች ብቻ ስለትዳር ህወታቸው የሚወያዩበት እና ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ ላይ “ምን ያህሎቻችሁ ባላችሁን ትወዳላችሁ?” ተበለው ተጠየቁ። ታዲያ ሁሉም ሚስቶች ባሎቻቸውን የሚወዱ መሆኑን ለማሳየት እጃቸውን ከፍ አድርገው አወጡ።

ከዛም “ባለችሁን እወድሃለሁ ብላችሁ የነገራችሁት መቼ ነው?” ተብለው ተጠየቁ። አንዳንዳቹ ዛሬ ፣ አንዳንዶቹ ትናንት ፣ አንዳንዶቹ ሊያስታውሱት አልቻሉም ነበር።

ከዛም ስልካቸውን አውጥተው ለባሎቻቸው “የእኔ ማር እወድሃለሁ” ብለው መልዕክት እንዲልኩ እና ከጎናቸው ካለው ሰው ጋር ስልክ ተለዋውጠው ምላሹን መልዕክት እንዲያነቡ ታዘዙ። ከእነዚህ መልሶች ውስጥ የተወሰኑት እነዚህ ናቸው።

1. እእ…የልጆቼ እናት አመመሽ እንዴ?

2. አሁን ደግሞ ምንድነው? የትኛውን እቃ ሰበርሽ?

3. ምን ማለት ፈልገሽ እንደሆነ አልገባኝም

4. ደግሞ ምን አደረግሽ? አሁን ግን አልምርሽም።

5. ???

6. እሽክትር አትዙሪ፤ ምን ያህል እንደምትፈልጊ ንገሪኝ ገዝቸ እመጣለሁ

7. በህልሜ ነው?

8. ይህ መልዕክት የማን እንደሆነ ካልነገርሽኝ ዛሬ መሞትሽ ነው

9. ማን ልበል?

Related posts

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

አደም (ዐ.ሰ) ከተፈጠሩ በኋላ የተሰጣቸው የመጀመሪያው ትምህርት የስሞች ዕውቀት ነበር። ይህም ከመላእክት የላቀ ደረጃ እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መላእክትም ለእርሳቸው ሱጁድ እንዲያደርጉ (እንዲሰግዱ) ምክንያት ሆኗል። ምንም

Read More »
ወሲባዊ ግንኙነት በእስልምና እይታ

ወሲባዊ ግንኙነት በእስልምና እይታ

እስልምና ወሲባዊ ግንኙነት ሊታፈን የማይገባው እንደሆነና በተገቢው መንገድ ሊረካ የሚገባ አስፈላጊ የሰው ልጅ ፍላጎት እንደሆነ ያስተምራል። ወሲባዊ ግንኙነት እንደ ቀላል ነገር የሚታይ  አይደለም፤ እንዲሁም አንድ

Read More »

የልጆች መብት በእስልምና

የልጆች መብት በእስልምና በሚለው ትምህርት ውስጥ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸውን መብት ትማራላችሁ። ልጆችን በማሳደግ ዙሪያ ከሸሪአ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ነገሮችን ታውቃላችሁ።

Read More »

የጋብቻ ጥያቄ አደቦች (ስነ-ስርአቶች)

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ጋብቻ ጥያቄ ፅንሰ ሃሳብ እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስነ-ስርአቶችን ትማራላችሁ። በእስልምና ውስጥ የጋብቻ ጥያቄን ሲያቀርቡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶችን ታውቃላችሁ።

Read More »

Share