እስልምና ወሲባዊ ግንኙነት ሊታፈን የማይገባው እንደሆነና በተገቢው መንገድ ሊረካ የሚገባ አስፈላጊ የሰው ልጅ ፍላጎት እንደሆነ ያስተምራል።
ወሲባዊ ግንኙነት እንደ ቀላል ነገር የሚታይ አይደለም፤ እንዲሁም አንድ ሰው ሊርቀው የሚገባ ነገርም አይደለም።
ይሁን እንጅ የእስልምና ሃይማኖት አንድ ሰው ይህንን ፍላጎት የሚቆጣጠርበትን እና የሚያረካበትን የተወሰኑ ሕጎች አስቀምጧል።
አንደኛው ይህንን ፍላጎት በእንስሳዊ ወይም በፍትወት የተሞላና ቁጥጥር በሌለው መንገድ አለማርካት ነው።
ይህ ፍላጎት ሊረካ የሚገባው ብቸኛው ህጋዊ መንገድ ትዳር ነው። በእስልምና የትዳር የመጨረሻ ግብ ሁለቱ የትዳር አጋሮች የስነ ልቦና እና ስሜታዊ መረጋጋትን ማግኘት ነው።

አላህ እንዲህ ይላል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡187)
“እነሱ ለናንተ ልብስ ናቸው፤ እናንተም ለእነሱ ልብስ ናችሁ።”
ይህ በቁርአን ውስጥ ያለ እጅግ በጣም ያማረ ገለጻ ነው፡፡
ባል እና ሚስት እርስ በርሳቸው መሸፈኛ መሆናቸው በባል እና ሚስት መካከል ያለውን ቅርርብ ስውር በሆነ ቋንቋ እንዲሁም በግልጽ የፍቅር ስሜት የሚንጸባረቅበትን መንገድ ይወክላል።
ኢብን ከሲር ታላቅ የቁርአን ትርጓሜ ላይ እንዲህ ብለዋል፡-
“ከነቢዩ ባልደረቦችና ከደቀ መዛሙርቶቻቸው መካከል ያሉ ተንታኞች] ይህ አንቀጽ ‘ሚስቶቻችሁ ለእናንተ መሸሸጊያ ናቸው፤ እናንተም ለእነርሱ መሸሸጊያ ናችሁ’ ማለት እንደሆነ ተናግረዋል። አረቢዕ ቢን አነስ ደግሞ ‘እነርሱ ሽፋንችሁ ናቸው፤ እናንተም ሽፋናቸው ናችሁ’ ብለዋል። በአጭሩ ሚስት እና ባል የቅርብ ግንኙነት ያላቸውና እርስ በርስ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ናቸው…።”
እስልምና አንድ ሰው ዝሙት ወይም አስገድዶ መድፈር እንዳይፈጽም በመስጋት የወሲብ ፍላጎትን ሊያነሳሳ የሚችል ማንኛውንም ነገር በመከልከል ግለሰቡን እና ማኅበረሰቡን ይጠብቃል።
ይህ በእርግጥ በሥነ ምግባር ሊያሳድጓቸው የሚችሉ ወላጆች አልባ ሕገወጥ ልጆች እንዲበዙ ያደርጋል።
ከዚያም በህብረተሰቡ ውስጥ በሌሎች ላይ ጥላቻ እና ንዴት ያዘሉ ቡድን ሆነው ይወጣሉ።
ከዚህ በተጨማሪም በሽታዎች በመላው ህብረተሰብ ውስጥ ይስፋፋል።
አሏህ እንዲህ ይላል:
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢስራዕ 17:32)
“ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!”

Share