የጋብቻ ጥያቄ አደቦች (ስነ-ስርአቶች)

Author picture
በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ጋብቻ ጥያቄ ፅንሰ ሃሳብ እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስነ-ስርአቶችን ትማራላችሁ። በእስልምና ውስጥ የጋብቻ ጥያቄን ሲያቀርቡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶችን ታውቃላችሁ።

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ጋብቻ ጥያቄ ፅንሰ ሃሳብ እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስነ-ስርአቶችን ትማራላችሁ።

የጽሁፉ አላማ

  1. የጋብቻ ጥያቄ ፅንሰ ሃሳብን ትረዳላችሁ።
  2. በእስልምና ውስጥ የጋብቻ ጥያቄን ሲያቀርቡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶችን ታውቃላችሁ።

የጋብቻ ጥያቄ አንድ ሰው በአሏህ ህግ (ሸሪአ) እና በነብዩ ሱና መሰረት አንዲትን ሴት ሊያገባት እንደሚፈልግ ለሴቷ ጠባቂ የቅርብ ዘመድ ማሳወቅ ነው።

ከአሏህ ፀጋዎች ውስጥ አንዱ ደስታን ፣ ጥሩ ምርጫን እና ማረጋገጫን ፣ ሁለቱም ጥንዶች አንዳቸው ካንዳቸው ጋር ተስማምተው እና ተግባብተው ለመተጫጨት የሚረዳቸውን ስነ-ስርአት ማውጣቱ ነው።

የጋብቻ ጥያቄ ስነ-ስርአቶች ውስጥ

  1. አንድ ሙስሊም ሰው ለጋብቻ የጠየቃትን ሴት ሌላ ሙስሊም ሰው መጠየቅ የለበትም።

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 5142 ፣ ሙስሊም 1412)

‹‹ቀድሞ የተስማማበትን ሽያጭ ሌላ ሰው (ከፍ ያለ ዋጋ ስላቀረበለት) ሽያጩን አይሰርዝ። በሙስሊም ወንድሙ ቀድማ የታጨችን ሴት እጇን አይጠይቅ (እሷን ለማግባት አይጠይቅ)።የመጀመሪያው ጠያቂ እስካልተዋት ወይም እንዲጠይቃት እስካልፈቀደለት በቀር።››

  1. እጮኛው እሷን ለማግባት የሚገፋው ነገር በእሷ ውስጥ ይመለከት ዘንድ እሷን ማየት ይችላል። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ትርሚዚ 1087)

‹‹ተመልከቷት፤ በእርግጥ ያነ በሁለታቸው መካከል ውዴታ እንዲፀና ያደርጋልና።››

ይበልጥ ነገሮችን የተሻለ ያደርጋልና። ከዚህ በተጨማሪ ሴቷ እጮኛዋን የማየት መብት አላት። ከእውቀት ሰዎች ከፊሎቹ ይበልጥ እሱን የመመልከት መብት ያላት እሷ ናት ይላሉ።

ጃቢር ኢብን አብዱሏህ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አቡዳውድ 2082)

‹‹አንዳችሁ አንዲትን ሴት ለጋብቻ በጠየቃችሁ ጊዜ እሷን ለማግባት በእሷ ውስጥ የሚገፋፋውን ነገር ከቻለ ይመልከት አሉ። ጃቢርም እንዲህ አለ፡ ‹‹አንዲትን ሴት ለጋብቻ ጠየኩኝ፤ እሷን ለማግባት የገፋፋኝን ነገር እስካገኝ ድረስ በሚስጥር እመለከት ነበር። ከዚያም አገባኋት።››

እጮኛን የመመልከት አደብ

1 እጮኛው ሴቷን ሊመለከታት የሚገባው ሊያገባት ከወሰነ ብቻ ነው።

2 እሷን ባለመውደዱ የጋብቻ ጥያቄውን በመሰረዝ እሷን ላለመጉዳት እና ላለማስከፋት የጋብቻ ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት ሊያያት ይገባል።

3 በምርጫው እርግጠኛ ይሆን ዘንድ ብዙ ጊዜ ደጋግሞ ማየቱ የተፈቀደ ነው።

4 የጋብቻ ጥያቄ ስነ-ስርአቶች ውስጥ አንዱ ጥሩ ዘሮቹን ለማብዛት ለምለም (ወላድ) ሴትን ለማግባት መፈለግ ነው።

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ተወዳጅ እና ለምለም (ወላድ) ሴትን አግቡ፤ ሌሎች ህዝቦችን በእናንተ ቁጥር እበልጣለሁና።››

5 ምክር መፈለግ እና ዱአ ማድረግ ያስፈልጋል። በእርግጥ ሙስሊም ሰው ዱአ ያደርጋል፤ ጌታውን ይማፀናል ፣ አሏህን የሚፈሩ እና ጥሩ ግንዛቤ ያላቸውን ሰዎችም በሁሉም ጉዳዮቹ ያማክራል።

ነገርግን ለማግባት መወሰን በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ጠቃሚ ውሳኔ ነው። ሆኖም ምክር ማግኘት እና ዱአ ማድረግ መቅደም አለበት።

6 ሁለቱ ጥንዶች በሁሉም ጉዳዮች ዙሪያ ግልፀኝነት እና ታማኝነት ሊኖራቸው ይገባል። እንከኖቻቸውን መደበቅ ፣ ሆንብሎ መዋሸት አይኖርባቸውም።

ምክኒያቱም ወደ ፊት ከተጋቡ በኋላ ትዳራቸው ላይ ተፅኖ ይፈጥራልና ነው።

7 የጋብቻ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሃይማኖታዊ መስፈርቶችን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል።ይህ የጋብቻ ቃልኪዳን ነው እንጅ ጋብቻው ተፈፀመ ማለት አይደለም።

ሆኖም ሁለቱ የወደፊት አጋሮች እጅ ለእጅ መጨባበጥ ፣ ለብቻቸው ተገልለው መቀመጥ ፣ ማሬ በሚል ቃል መጠራራት እና አንዳቸው ለአንዳቸው ሽቶ መነስነስ እና መጊያጊያጥ የለባቸውም።

0%
2
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሙስሊም ቤተሰብ

ጥያቄና መልስ፡ የጋብቻ ጥያቄ ስነምግባሮች

‹‹የጋብቻ ጥያቄ አደቦች›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 የጋብቻ ጥያቄ ሲቀርብ አንዲትን ሴት ለመመልከት ከግምት ውስጥ ማስገባት ካለበት ነገር መካከል

2 / 6

Bookmark question icon

2 የትዳር አጋር ለመምረጥ አንድ ሰው መስፈርቱ ሊያደርግ ሚገባው ነገር ምንድን ነው?

3 / 6

Bookmark question icon

3 መመልከት የተፈቀደው ለወንድ ነው እንጅ ለሴት አይደለም።

4 / 6

Bookmark question icon

4 ወንዱ ወይም ሴቷ እንከን ኖሮባቸው አንደኛቸው በዚህ ምክኒያት አያገባኝም ብለው ባሰቡ ጊዜ ይህን እንከን መደበቅ አለባቸው።

5 / 6

Bookmark question icon

5 የጋብቻ ስነ-ስርአት ከመከተል ጥቅሞች መካከል አንዱ

6 / 6

Bookmark question icon

6 የእጮኛ መልክ ማድነቅ ሃይማኖቱን አጥብቆ የያዘ እና ጥሩ ባህሪ ያለው ሚለው መስፈትት ይተካል።

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 19%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

አደም (ዐ.ሰ) ከተፈጠሩ በኋላ የተሰጣቸው የመጀመሪያው ትምህርት የስሞች ዕውቀት ነበር። ይህም ከመላእክት የላቀ ደረጃ እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መላእክትም ለእርሳቸው ሱጁድ እንዲያደርጉ (እንዲሰግዱ) ምክንያት ሆኗል። ምንም

Read More »
ወሲባዊ ግንኙነት በእስልምና እይታ

ወሲባዊ ግንኙነት በእስልምና እይታ

እስልምና ወሲባዊ ግንኙነት ሊታፈን የማይገባው እንደሆነና በተገቢው መንገድ ሊረካ የሚገባ አስፈላጊ የሰው ልጅ ፍላጎት እንደሆነ ያስተምራል። ወሲባዊ ግንኙነት እንደ ቀላል ነገር የሚታይ  አይደለም፤ እንዲሁም አንድ

Read More »

የልጆች መብት በእስልምና

የልጆች መብት በእስልምና በሚለው ትምህርት ውስጥ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸውን መብት ትማራላችሁ። ልጆችን በማሳደግ ዙሪያ ከሸሪአ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ነገሮችን ታውቃላችሁ።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share