Table of Contents

ምን ያማረ ስም ነው ጣፋጭ
ይዞጭልጥ የሚል ልብ መሳጭ

በአንተነትህ የተጥራራህ
ከፍጥረታት የተብቃቃህ
ሰማይና ምድርን የዘረጋህ
ምስጋና ሁሉ የሚገባህ

አጋዥ የለህ አማካሪ
ያሻህን ሁሉ ሰሪ
አስተካካይ አሳማሪ

ራስህን የቻልክ ተብቃቂ
ይፋ ድብቅ ሁሉ አዋቂ

ህይወት ሰጭ ጥበበኛ
ስለ እውነት ፈራጅ ዳኛ

ምን እናድርግ የኔ ጌታ
ምን እንፍጠር መላ እንምታ?

ምን እናውጣ ምን እናውርድ?
ምን እንምከር ምን እንዘይድ?

እንድንወጣ ከማዕበሉ
ከዱንያ ውሽንፍሩ
ከድቅድቁ ከጨለማው
ከነገሰው ካንሰራፋው

ምን እናድርግ ያረህማኑ
እንዲደርሰን ብርሃኑ

እንዲታየን ጭላንጭሉ
የእምነት ብርሃን ወጋግኑ

ምን እናድርግ የኔ ጌታ?
ምን እንፍጠር መላ እንምታ?

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top