ሰባቱ የአለማችን ድንቃድንቆች ምንድን ናቸው?

Author picture
በአንድ ወቅት አንድ መምህር ተማሪዎች ሰባቱ የአለማችን ድንቃድንቆች ምንድን ናቸው? በማለት እንዲዘረዝሩና እና ታሪካቸውን እንዲያብራሩ ይጠይቃቸዋል።
ሰባቱ የአለማችን ድንቃድንቆች ምንድን ናቸው?

በአንድ ወቅት አንድ መምህር ተማሪዎች ሰባቱ የአለማችን ድንቃድንቆች ምንድን ናቸው? በማለት እንዲዘረዝሩና እና ታሪካቸውን እንዲያብራሩ ይጠይቃቸዋል።

“የአለማችን ድንቃድንቆች”

ምንም እንኳ አለመስማማት ቢኖርም የሚከተሉት ግን አብላጫ ድምፅ አግኝተዋል።

  1. የግብፅ ፒራሚዶች
  2. ታጅመሃል
  3. ታላቁ ቦይ ካንየን
  4. የፓናማ ቦይ
  5. የአንፒየር ስቴት ህንፃ
  6. ፔተር ባሳሊካ
  7. የቻይና ትልቁ ግንብ

መምህሩ የተማሪዎቹን የክፍል ስራ እየሰበሰበ እያለ አንድ ተማሪ ግን የክፍል ስራዋን ያለጨረሰች መሆኑን ተመለከተ። መስራት ከበደሽ እንዴ? ብሎ ይጠይቃታል።

አዎ! በጣም ብዙ ስላሉ የትኛውን አንስቼ የትኛውን እንደምተው ከብዶኝ ነው” ስትል መለሰች።

“እስኪ የፃፍሽውን ብቻ ንገሪን። ከቻልን እናግዝሻለን አላት።”

ተማሪዋም እንደማመንታት እያለች እኔ እንደማስበው የአለማችን ሰባቱ ድንቃድንቅ ማየት ፣ መስማት ፣ መንካት ፣ መቅመስ ፣ ማሽተት ፣ መሳቅ እና መውደድ ናቸው አለች።

የመማሪያ ክፍሉ ፀጥ አለ። ኮሽታ እንኳ አልነበረም። እንደ ቀላል እና እንደተለመድ ነገር ልናስበው እንችላለን። ነገርግን እጅግ በጣም አስደናቂ ነገሮች ናቸው። እነዚህ ነገሮች በህይወታችን ውስጥ እፁብ ድንቅ የሆኑ የሰው ልጅ ሊሰራቸው ወይም የሰው ልጅ ሊገዛቸው የማይችላቸው ናቸው።

አስኪ አንድ ጊዜ አሏህ በኛ ላይ ያደረጋቸውን ውብ ፀጋዎች አስበን አልሃምዱ ሊላህ እንበል? እኔ አልኩ…. አልሃምዱ ሊላህ!

መልዕክቱን ከወደዱት ቢያንስ ለሶስት ሰዎች ሼር አድርጉት።

Related posts

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው። በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው።

Read More »
እስልምና በኢትዮጵያ፡

እስልምና በኢትዮጵያ፡ ከጥንታዊ ሥረ-መሠረቱ እስከ ዘመናዊ ስርጭቱ

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዷ ስትሆን በርካታ እምነቶች ያስተናገደች ምድርም ነች። ከእነዚህም መካከል እስልምና እና ክርስትና ይገኙበታል። እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ የራሱን ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ሃይማኖት

Read More »
የቀናት አቆጣጠር

የእስልምና የቀናት አቆጣጠር

ከእስልምና በፊት አረቦች የራሳቸው የሆነ የቀናት አቆጣጠር አልነበራቸውም። ምንም እንኳ አስራ ሁለቱን የጨረቃ ወራቶች ቢያውቁም ጊዜን የሚያሰሉት አንድ ልዩ ክስተት ከፊቱ ወይም ከኋላው የተከሰተበትን ጊዜ

Read More »
መስጅደ ነበውይ

መስጅደ ነበውይ የነብዩ መስጅድ

ነብዩ ያኔ ያስሪብ ተብላ ወደምትጠራው የአሁኗ መዲና በተሰደዱ ጊዜ ጋልበዋት በነበረችው ግመል ዙሪያ ተከታዮቻቸው እና የከተማዋ ሹማምንት ምርጥ ልብሶቻቸውን እና የብረት መከላከያ ልብሶችን እንደለበሱ ተቀበሏቸው።

Read More »

Share