የሸይጧን ወጥመዶች
ሸይጧን ጭስ አልባ ከሆነ እሳት የተፈጠረ ሲሆን መላኢካ ባይሆንም ለአሏህ በነበረው ታዛዥነት ግን በጀነት ከነሱ መካከል ነበር።
ሞት ማለት ነፍሳችን ከስጋችን የሚለያይበት ስርዓት ሲሆን ከዱንያ ወደ አሂራ የሚደረግ ጉዞ ነው። ሆኖም ሞት ማንኛውም ሰው የሚያጋጥመው ከባድ እና አስፈሪ እውነታ ነው።
ኢባዳ የሚለው ቃል ሸሪአዊ ፍቹ አሏህ የሚወደው ማንኛውም በግልፅም ይሁን በድብቅ የሚሰራን፤ በንግግር እና በተግባር የሚገልፅን ስራ ሁሉ የሚያጠቃል ቃል ነው።
አህለሱና ወልጀመአ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮት እና ምሳሌ ፣ የሶሃባዎች እና ቀደምት ደጋግ የአሏህ ባሮች መንገድ አጥብቀው የያዙ ናቸው፡፡
አህካም ወይም የፍርድ ውሳኔ ለሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር አመልካች የሆነው ሁክም የሚለው ቃል ነው። ውሳኔ ወይም ብያኔ የሚል ትርጉም አለው። በእስልምና ማንኛውም ተግባር በሚከተሉት አምስት ምድቦች ይከፈላል
ሞት ምንኛውም ሰው ከሷ ማምለጥ የማይችላት እውነታ ናት። በእያንዳንዷ ቀን ፣ ሰዓት እና ደቂቃ ወደ እሷ ነው የምንቀርበው። በ2007 በወጣው የሲ አይኤ ፍክት ቡክ መረጃ መሰረት በእያንዳንዷ ደቂቃ ሁለት ሰዎች ይሞታሉ።
ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው። የተውባ የቃል በቃል ትርጉሙ መመለስ ማለት ሲሆን አሏህን ወደ ማስታዋስ እና ወደ መታዘዝ መምጣት ማለትም ነው። ተውባ በማድረግ ሐጢያተኞች ከሐጢያታቸው
የሰው ልጅ ያለ መመሪያና ደንብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ በመሆኑ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ የሰው ልጅ መመሪያ ያስፈልገዋል። ሆኖም ፆመኛ ሙስሊም እንደሌሎቹ የእምነቱ ስርአት ሊከተላቸውና ሊተገብራቸው የሚገቡ መመሪያና ደንቦች እንደሚከተለው ተብራርተዋል።
መስተካከልን አስበን ወደ አሏህ ለመመለስ ከቆረጥን አሏህ በባሮቹ ላይ አይጨክንም። የውሸት ኑሮን አንኑር ወደ አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ብንመለስ ነው የሚሻለው። እንስተካከል ነገሮች ሁሉ ይስተካከሉልናል። ከህይወት ወከባ እናርፋለን፤ ወደ ማይቀረው አለም ስንሄድ አንፈራም እንደፍራለን