አህለሱና ወልጀመአ

Author picture
አህለሱና ወልጀመአ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)  አስተምህሮት እና ምሳሌ ፣ የሶሃባዎች እና ቀደምት ደጋግ የአሏህ ባሮች መንገድ አጥብቀው  የያዙ ናቸው፡፡

አህለሱና ወልጀመአ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)  አስተምህሮት እና ምሳሌ ፣ የሶሃባዎች እና ቀደምት ደጋግ የአሏህ ባሮች መንገድ አጥብቀው  የያዙ ሰዎች ለማመላከት የምንጠቀመው መጠሪያ ስም ነው።

ይህ ማዕረግ ወይም መጠሪያ እውነትን አጥብቀው የሚከተሉ ሰዎችን በሃይማኖት ከሚፈላሰፉ እና ፈጠራቸውን ከሚከተሉ ሰዎች እንደመለያነት ያገለግላል።

አህለሱና ወልጀመአ እውነትን የሚከተሉ እና በመካከላቸውም በሃማኖት ቡድንተኝነት የማይከፋፈሉ፤ የዚህ ኡማ ቀደምት ሷሊሆች በተስማሙበት ነገር ብቻ የሚከተሉ ናቸው። በእምነት ጉዳይ በሃይማኖት ቡድኖች ጽንፍ መካከለኛ አቋምን የያዙ ናቸው።

በተመሳሳይ ሁኔታ በአምልኮት ተግባራት እና ባህሪያቶች በጽንፈኞች እና በቸልተኞች መካከል መካከለኛ አቋም የያዙ ናቸው። በዚህ አለም “አሸናፊዎች” በመጭው አለም ህይወት  ደግሞ ነጃ የሚወጡ (ሚድኑት) ናቸው።

ሌላው አህለሱና ወልጀመአ ጋር በተያያዘ የሚጠቀሰው መጠሪያ ሰለፉነ ሷሊሂን ነው። የቃል በቃል ትርጉሙ “ቀደምት ሷሊሆች  ፃድቃናት” የሚል ነው።

ይህ የሚያመለክተው የነብዩ ሶሃባዎች ፣ የእነሱ ፃድቅ (ሷሊህ) ወራሾ እና የአሏህን መጽሐፍት እና የመልእክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) ሱና  የነብዩ ሶሃባዎች በተረዱበት መንገድ አጥብቀው የያዙትን ተከታይ መራሾች ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ቢድአና ሱና ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Share