የዳዕዋ ጉዞ በካንፓስ ተማሪዎች
በመልካም ነገር ማዘዝና ከመጥፎ ነገር መከልከል በኢስላም ትልቅ ሃላፊነት ሲሆን ኡለማዎች ይህን የተቀደሰ ተግባር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው ብለዋል። ምክርን እንለዋወጥ ዘንድ ሌሎችን መልካም ወደሆነ ነገር እናመላክት ዘንድ እና እርስበርሳችነም እውነት በሆነ ነገርና በትዕግስት አደራ አደራ እንባባል ዘንድ ታዘናል።

እውነትን መናገር በጣም የሚወደድ መልካም ልማድ ነው። ሁልጊዜም እውነትን የምንናገር ከሆነ እራሳችነን ከብዙ ችግሮች መጠበቅ እንችላለን። ይህ ብዙ መጥፎ ነገሮችን የሰራ ሰው ታሪክ ነው።
እውነትን መናገር በዚህ የውድድር እና እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ በሚል ማህበረሰብ ውስጥ ለወጣቶች ሃቀኛ (እውነትን ተናጋሪ) መሆን አስቸጋሪና ፈታኝ ነገር ሊሆን ይችላል። አብዛሃኛዎቻችን ጥፋት ስናጠፋ ቤተሰቦቻችን ፣ አስተማሪዎቻችን ፣ ጓደኛዎቻችን ይርቁናል ፣ ይጠሉናል ፣ በኛ ላይ መጥፎ አመለካከት ይኖራቸዋል በማለት አብዛሃኛውን ጊዜ እንዋሻለን። ለምሳሌ የቤት ስራችንን ካልሰራን ከመቀጣት ለመዳን ስንል ውሸትን እንፈበርካለን፤ እንዲሁም አንድ ጥፋት
መከራ ፣ ችግር አጋጥሞህ ጭንቀትህን ልታካፍለው አስበህ የነበረ ሰው የለም? በጣም የሚወድህ ፣ ስትጨነቅ የሚጨነቅ ፣ ደስታህን ደስታው ያደረገ ጥብቅ ጓደኛስ ኖሮህ ያውቃል? ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ እንድትጨነቅና እንድትተክዝ የሚያደርግህ ጓደኛስ አጋጥሞህ ያውቃል?