ምድርን በጭንቅላትህ ላይ አትሸከማት

Author picture
ምድርን በጭንቅላትህ ላይ አትሸከማት! ይህ ጽሑፍ ከመጠን ያለፈ ስጋትን አስወግደው የአእምሮ ሰላም የሚያገኙበትን መንገድ ያሳየዎታል። ጠንካራ ቀልብ በመገንባት ፣ ችግሮችን በድፍረት በመጋፈጥ የተረጋጋና ደስተኛ ህይወት ይኑሩ።

ምድርን በጭንቅላትህ ላይ አትሸከማት! አንዳንድ ሰዎች በመኝታ ፍራሻቸው ላይ እንደተጋደሙ በነፍሶቻቸው ውስጥ የአለም ጦርነት ያካሂዳሉ።

ከዚያም ጦርነቱ ሲያበቃ የጨጓራ በሽታን ፣ የደም ግፊትንና የስኳር በሽታን ማርከው ያርፋሉ።

ከክስተቶች ጋር አብረው ይቃጠላሉ፤ በኑሮ ውድነት ይናደዳሉ፤ ዝናብ በመዘግየቱ ይግላሉ፤ የብር ዋጋ በመቀነሱም ይንጫጫሉ። ሁሌም ጭንቀት ውስጥ ናቸው። ትካዜም ያንዣብብባቸዋል።

እኔ ደግሞ የምመክርህ ምድርን በጭንቅላትህ ላይ አትሸከማት ብየ ነው። አስከፊ ክስተቶችን እዚያው ምድር ላይ እንደሆኑ ተዋቸው። ጨጓራህ ውስጥ አታስገባቸው።

አንዳንድ ሰው ቀልቡ እንደ እስፖንጅ ነው። አሉቧልታዎችንና የመንደር ወሬዎችን ይመጣል። በቀላሉ ይጨነቃል፤ ለሆነ ላልሆነው ይንቀጠቀጣል። ለሁሉም ነገር ውስጡ ይናወጣል።

ቀልብ ደግሞ ባለቤቱን የማፍረስና ማንነቱን የመናድ ሃይል አለው።

የሐቅ ጓዶች ግሳፄዎችና ተሞክሮዎች ባላቸው እምነት ላይ ጥንካሬን ይጨምሩላቸዋል። የክህደት ጓዶች ደግሞ ነውጦች ፍራቻቸውን ያባብሱባቸዋል።

በአስከፊና በአስቸጋሪ ጊዜያት ደግሞ ከጠንካራ ቀልብ የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም። ምክኒያቱም ጀግና የሆነ ሰው ምንጊዜም ሆደ ሰፊና ፅኑ ነው። በአሏህ ላይ ያለው መተማመን ሥር የሰደደ ነው። መንፈሱ የተረጋጋ ነው። ልበ ሰፊም ነው።

ፈሪ ግን በየቀኑ በብዥታ ህልም ፣ ትንቢትና አሉቧልታ ሰይፍ በተደጋጋሚ ራሱን ያደርዳል። የተረጋጋ ህይወት መኖር ከፈለክ ችግሮችን በድፍረትና በጥንካሬ ተጋፈጣቸው።

ቂሎችም እንዳያታልሉህ በሚያሴሩትም አትጠበብ። ከሚያጋጥሙህ ችግሮች በልጠህ ለመገኘት ሞክር። ከጐጂ ነፍሶች በልጠህ ለመበፈርታት ጣር።

ከአውሎ ንፋስም የባሰ ጠንክር። እነዚያ ቀልበ ደካሞች አቤት ሲያዝኑ ጊዜ ሲወዘውዛቸው ይኖራሉ። በህይወት ላይ የሚጓጉ ኾነው ታገኛቸዋለህ።

ጠንካሮች ግን የአሏህ እገዛ ሁሌም አብሯቸው ነው። ቃሉንም በተስፋ ይጠባበቃሉ። በነሱም ላይ እርጋታን አወረደ።

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share