ወጣትነት እና መዝናኛዎቻችን

Author picture
በመጀመሪያ ከቅጥ ያለፈ መዝናናት የሚያስፈልገው ችግር በመኖሩ ምክኒያት ነው። ማለቴ አንድ ሰው መንፈሳዊ ችግር ወይም አለመረጋጋት ካለበት መዝነናናት እንዳለበት ያስባል። ሆኖም ብዙ ችግሮች ሲገጥሙት በዛውልክ ብዙ መዝናናትን ይመርጣል።

ወጣትነት እና መዝናኛዎቻችን በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ምስጋናና ልቅና ለአለማቱ ጌታ ለአሏህ ይገባው። የአሏህ ሰላምና እዝነት በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በባልደረቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

የወጣትነት ጊዜያችነን ከሚገሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በሃይማኖታችን ክልክል የሆነ መዝናኛ ነው። ለምሳሌ:- ጫት መቃም ፣ የአልኮል መጠጥ ፣ ናይት ክለብ ፣ ቁማር ፣ ሙዚቃ የተለለያዩ ጌሞች ወ.ዘ.ተ ናቸው።

እነዚህ ነገሮች ሐራም የሆኑ የመዝናኛ ማዕከሎች ሲሆኑ ወርቃማውን የወጣትነት ጊዜያችነን ይገላሉ። በመጀመሪያ ከቅጥ ያለፈ መዝናናት የሚያስፈልገው ችግር በመኖሩ ምክኒያት ነው።

ማለቴ አንድ ሰው መንፈሳዊ ችግር ወይም አለመረጋጋት ካለበት መዝነናናት እንዳለበት ያስባል። ሆኖም ብዙ ችግሮች ሲገጥሙት በዛውልክ ብዙ መዝናናትን ይመርጣል።

ሰዎች ለመዝናናት ፣ ለመሳቅ ፣ ለመጫወት ፣ ራሳቸውን ፈታ ለማድረግ ይረዱናል ብለው የሚያስቧቸው የመዝናኛ አይነቶች በሁለት ይከፈላሉ።

አንዳንዶቹ በሃይማኖታችን የተከለከሉ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ የተፈቀዱ ናቸው። ለምሳሌ:- ከተከለከሉ የመዝናኛ አይነቶች መካከል አስካሪ መጠጥ ፣ ቁማር ፣ ሙዚቃ ጫት ፣ ሽሻ ፣ ሲጋራ ፣ ሴቶችና ወንዶች ተቀላቅለው የሚዝናኑባቸው ነገሮች ወ.ዘ.ተ ናቸው።

ከእነዚህ ነገሮች ከምንርቅባቸው መንገዶች አንዱ ጠንካራ ኢማን ያለው መሆን ነው። ጠንካራ ኢማን ከሌለን ፣ አሏህን በብቸኝነት የማንገዛ ከሆነ ፣ ያዘዘንን የማንታዘዝ፤ የከለከለንን ነገር የማንከለከል ከሆነና እሱን በማውሳት እስካልተጠመድን ድረስ አዕምሯችን ፣ ቀልባችን ፣ መንፈሳችን ሁሉም ይራባል።

ደስታ ሳይሆን ሃዘን በልባችን ይነግሳል። ለዚህም መፍትሄው በመዝናናት ስም ጊዜን ማቃጠልና የአሏህን ህግጋት መጣረስ ሳይሆን አሏህን በብቸኝነት መገዛት ፣ የአሏህ ፍራቻ ያለው መሆን ፣ ልቡን በዚክር ማርጠብ ነው።

ይህን ማድረጋችን ሰላምና ደስታን ፣ የአዕምሮ ረፍትና ፅናትን ያጐናፅፈናል። እናም መዝናናት የሚለው ነገር ብዙም አስፈላጊ ሆኖ አናገኘውም።

በእርግጥ ሃላል በሆኑ ነገሮች መዝናናት ኢስላም አይከለክልም። እነዚህም እኛን ለማርካት በቂዎች ናቸው።

በህይወታችን ትክክለኛ ደስታ የምናጣጥመው ራሳችነን ለአሏህ ትዕዛዝ ተገዢ ስናደርግ ብቻና ብቻ ነው።

ስለዚህ ደስታን የምንፈልግ ከሆነ ራሳችነን በኢማን በተቅዋ በማነፅ ለህይወታችን ህይወት እንስጣት፤ በኢባዳ ተግባሮች እናስውባት፤ ከሃጢያት በመራቅ እንጠብቃት።

እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ አሏህ እሱን በብቸኝነት ተገዝቶው፤ ተቅዋን በልባቸው ዘርተው፤ እሱን ቀን ማታ አውስተው፤ የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ሱና ተከትለው በዱንያም ሆነ በአኺራ ደስታ ከሚጐናፀፉት ባሮቹ ያድርገን። አሚን!!!

Related posts

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »

ስንፍናን የምንቀርፍባቸው 10 መንገዶች

ስንፍና ምንድ ነው? ስንፍና ጥረት እንዳናደርግ እና ጠንክረን እንዳንሰራ የሚያደርግ የውስጥ ግፊት ነው። ይህም ብዙ ጊዜ ነገሮች ባሉበት እንዲቀጥል የሚያደርግ ሲሆን አንዳንዴ ትንሽ ሰነፍ መሆን

Read More »
የእውቀት ታላቅነት

የእውቀት ታላቅነት

የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ማለትም አደም አለይሂ ሰላም ወደዚች አለም ሲመጣ ከአሏህ ዘንድ የነገራቶችን ስምና እውቀት አሏህ ችሮት ነው። ከዚህም አልፎ ለነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻው

Read More »

Share