ህዝቦቹ ከጠመሙ በኋላ ለእራሱ ህዝቦች አሏህ የላከው የመጀመሪያው መልዕክተኛ ኑህ ( ) ነው። ያመልኳቸው የነበሩ ጣኦቶች መልካም ነገር ያመጡልናል ፣ ከመጥፎ ነገር ይጠብቁናል ፣ ፍላጎታችነን ሁሉ ይሞሉልናል ብለው ያምኑ ነበር። ለጣኦቶቻቸውም ወድ ፣ ሱዋእ ፣ የጉስ ፣ የኡቅ እና ነስር የሚባሉ ስሞችን ሰጥተዋል።
በመሰረቱ እነዚህ ስሞች ከእነሱ ጋር አብረው ይኖሩ የነበሩ ደጋግ ሃይማኖተኛ ሰዎች ይጠሩባቸው የነበሩ ስሞች ናቸው። ነገርግን እነዚህ ደጋግ የአሏህ ባሮች ከሞቱ ቡኋላ ትውስታቸውን ጠብቀው ለማቆየት ሲሉ በእነሱ ስም ሃውልት አቆሙ።
የእነሱ ተተኪ ትውልዶች ሃውልቶቹ ለምን እንደቆሙ እንኳ አያውቁም። የሚያውቁት ወላጆቻቸው ያመልኳቸው እንደነበር ብቻ ነው። እነሱም ይህንኑ አደረጉ። የጣኦት አምልኮ የተጀመረው በዚህ መልኩ።
የጠመሙ ህዝቦቹን እንዲመራ አሏህ መልዕክተኛው ኑህ ( ) ላከው። ልክ እንደ ሰማይ ፣ ምድር እና ጨረቃ ባሉ እፁብ ድንቅ የአሏህ ፍጥረቶች እንዲያሰላስሉ አደረገ። ለረዥም ጊዜ እንዴት ሰይጣን እንዳሳሳታቸው ገለፀላቸው፤ የአሏህን አስገራሚ ፍጡሮች ነገራቸው።
እናም አሏህ በእነሱ ላይ ያደረገውን እልቆ ቢስ ስጦታ አስታወሳቸው። አሏህን እንጅ ሌላን እንዳያመልኩ፤ በአሏህ አሳማሚ ቅጣት አስጠነቀቃቸው።
ኑህ ( ) አንተ ልክ እንደኛው ሰው ብቻ ነህ ሲሉ ወቀሱት። እሱን የተከተሉት ድሆች እና ጉስቁሎች እንደሆኑ ሲያውቁ ይሳለቁ ያላግጡበት ጀመር። ምንም እንኳ በትዕቢተኝነት እውነቱን ባይቀበሉም ኑሕ ( ) በአሏህ እንዲያምኑ ቀን እና ሌሊት ፣ ህዝቡ በተሰባሰበበት እና በግለሰብ ደረጃ በተናጠል ሰዎችን መስተማሩን ቀጠለ።
የአሏህን ምልክቶች እና ፍጡራኖቹን በመፍጠር ያለውን የአሏህ ብቃት እና ጥበብ ገለፀላቸው። ነገርግን ወደ አሏህ በጠሯቸው ጊዜ ከእሱ ይሸሻሉ። የአሏህን ምህረት እንዲጠይቁ በነገራቸው ጊዜ እውነታውን ላለመስማት በእልህ ጆሯቸውን በጣቶቻቸው እና በልብሶቻቸው ይጠቀጥቃሉ።
ኑህ ( ) ህዝቦቹ በአሏህ እንዲያምኑ ለዘጠኝ መቶ ሃምሳ አመት ጥሪ ማድረጋቸውን ቀጠሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን እያንዳንዱ ትውልድ መጭውን ትውልድ በኑህ እንዳያምኑ እና እውነቱን እንዳይከተሉ ያስጠነቅቁ ነበር።
የአማኞቹ ቁጥር ከዚህ የበለጠ እንደማይጨምር ሲያውቁ፤ መጥፊያቸውን ለመኑ።
አሏህ ( ) የኑህን ( ) ፀሎት ተቀበላቸው። መርከብ እንዲሰሩም አዘዛቸው። ቀን ማታ ታግለው እና የህዝቦቹን ስላቅ ችላ ብለው መርከቡን አቆሙ።
አሰቃቂው ቀን ደረሰ። የምድር ምንጮች መጉረፍ ጀመሩ። በአሏህ ትዕዛዝ ኑህ ( ) አማኞችን መርከቡ ላይ አሳፈሩ፤ ዘራቸውን ለመጠበቅ ከእያንዳንዱ እንስሳት ፣ አዕዋፍ እና ነፍሳት ጥንድ ጥንድ(ሴትና ወንድ) አድርጎ አሳፈረው ወሰደ።
የኑህ ( ) ልጅ ወደ ተራራ ጫፍ በመሄድ ከጎርፍ ማዕበል እንደሚያፈገፍግ በማሰብ ወደ መርከቡ ሳይገባ ቀረ። የተራራው ጫፍ በጎርፍ የሚጥለቀለቅ መሆኑን አላወቀም።
የዝናቡ እና ምድር የተፋችው ውሃ ከባድ ማዕበል እና ውሽንፍር ምድር አይታው የማታውቀቀውን ከባድ ጎርፍ አስተናገደች። ከእነዚህ ከሃዲዎች የተረፈ አንድም አልነበረም። የኑህ ልጅ እንዲሁም ከሃዲ የነበረችው ሚስቱም ሞተዋል።
በአምላክ ትዕዘዛዝ ምድር ሰላሟ ተመለሰላት። ውሃውም ሸሸ፤ ደረቁ መሬት (የብሱ) ተገለጠ። አሏህ ኑህንና ተከታዮቹን አተረፋቸው።