ዛሬ ዛሬ ፈትዋ የሚሰጠው በዝቷል። ወንድ ፣ ሴት ፣ ወጣት ፣ አዛውንት ሳሩ ቅጠሉ ሁሉም ፈትዋ ሰጭ ሆኗል። ለ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኡማ ትልቁ ፈተና ፈትዋ ለመስጠት መቻኮል ነው።
ይህን ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር አራቱ የመዝሐብ ባለቤቶች የኔ ፈትዋ ከቁርአን እና ከሱና ጋር ካልገጠም ተውት ሲሉ ዛሬ ላይ ግን የኔ ፈትዋ ትክክል ነው ብለው የሚሞግቱ አይጠፉም።
የራሳቸውን ጥቅም የሚያሳድዱ አሊም ነኘ ዱአት ነኝ ያሉ በኡማው ክፍፍል ላይ ጧት ማታ ይሠራሉ። የዲን ላይ ነጋዴዎች በኡማው መካከል መበታተንን እና መከፋፈልን ፈጥረዋል።
ከዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ): “የኔ ኡመት በ73 ቡድን ይከፋፈላል ከነዚህም መካከል አንዷ ብቻ ናት የጀነት”ብለው የለ የሚል ነው።
አዎ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ብለዋል እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ነገር ቢኖር ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ይከፋፈላሉ እንጂ ተከፋፈሉ የሚል አንድም ቦታ ላይ በሐዲሳቸው የለም። እንዲሁም ሙስሊሞች ተከፋፈሉ የሚል አንድም የቁርአን አያ የለም።
ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ፈትዋ ለመስጠት አንቻኮል፤ እራሳችነንም ለክፍፍል ምቹ አናድርግ (ምቹ ሁኔታ አንፍጠር)፤ ህይወታችንን በቁርአን እና በሐዲስ ብቻ እንምራ! ማንም ሰው ሱፍያ ፣ ወሐቢያ ፣ ሰለፊይ ፣ ኸዋሪጅ ከነዚህ መካከል የትኛው ነህ? ብሎ ቢጠይቅህ መልስህ “እኔ ሙስሊም ነኝ” ብቻ ይሁን!!!