ለሌሎች መልካም መስራት የልብ እርጋታ ይሰጣል

Author picture
ጭንቀት ወይም ትካዜ ይሰማዎታል? ለሌሎች መልካም መስራት እንዴት የልብ እርጋታ ፣ ደስታና እርካታ እንደሚሰጥ ይወቁ። ይህ ጽሁፍ መልካም መስራት በራስዎ ህይወት ላይ የሚያመጡትን አስደናቂ የስነ-ልቦናና መንፈሳዊ ጠቀሜታዎች ያብራራል፤ ጭንቀትን ለማስወገድ ምርጡ መፍትሄ እንደሆነም ያሳያል።

መልካም መስራት፡ መልካም ነገር እንደስሙ መልካም ነው። ጥሩውም ሁሉ እንደ ጣዕሙ ጥሩ ነው። ሰዎችን በማስደሰት የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች እነዚሁ አስደሳቾች ናቸው።

የመልካም ስራዎቻቸውን ፍሬ ከማንም በፊት በነፍሶቻቸው ፣ በባህሪያቸውና በልቦናቸው ያገኙታል። በመሆኑም የልብ እርጋታን ፣ ደስታንና እርካታን ያጣጥማሉ።

ጭንቀት ቢጐበኝህ ወይም ትካዜ ቢነካህ ለሌሎች መልካም ነገር ስራላቸው በጎ ዋልላቸው ደስታና እረፍት ታገኛለህና።

ላጣ ሰው ስጥ፤ የተበደለን ሰው እርዳ፤ ለተቸገረ ሰው ድረስለት፤ የተራበን ሰው አብላ ፤ የታመመን ጠይቅ፤ አደጋ የደረሰበትን አግዝ ደስታ በዙሪያህ አካቦህ ታገኘዋለህ።

መልካም መስራት እንደ ሽቶ ሻጭ ፣ ተሸካሚዋን እና ገዢዋን ታውዳለች። መልካም ስራዎችን በመስራት የሚገኘው ደስታም ልቦቻቸውን በመልካም ስራና በበጐ ተግባራት በገነቡ ሰዎች ልቦች ውስጥ ካሉ መድሃኒት ቤቶች የሚከፋፈሉ የተባረኩ ክኒኖች ናቸው።

የፀባይ ድሆችን ብሩህ ፈገግታን ማከፋፈል በእሴቱ ዓለም ውስጥ ያለ ምንዳው የማይቋረጥ ምፅዋት ነው። «መልካም ስራን አትናቅ።

ወንድምህን ፈካ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን» ፊትን ማጨፍገግ መነሻውን ከአሏህ ውጪ የማያውቀውን ጦር በሌሎች ላይ እንደ መምዘዝ ነው።

አንዲት ዝሙት አዳሪ አንድን ውሻ አንድ እፍኝ ውሃ ማጠጣቷ ስፋቱ የሰማያትና የምድሮች ያክል የሆነን ገነት አሰጥቷታል።

ምክኒያቱም የምንዳው ባለቤት መሃሪ አመስጋኝ መልካም መስራት እና መልካም ስራን የሚወድ ሃብታምና ምስጉን ነው።

የጭንቀት ፣ የድንጋጤና የፍርሃት ጭራቆች የሚያስፈራሯችሁ ሰዎች ሆይ!…. ወደ መልካም ስራዎች ኑ።

ሌላውን በመጥቀም ፣ በማስተናገድ ፣ በማፅናናት ፣ በመርዳትና በማገልገል እራሳችሁን አዝናኑ፤ የደስታን ጣእም ፣ ቀለምና ቃና ታገኛላችሁና።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ለይል 92:19-21)

“ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ ይህንን ሠራ። ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል።”

Related posts

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share