የእርጋታ ቁልፎች ፡ ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ መቀየር

Author picture
በኢስላም እይታ፣ ችግር የውድቀት ምልክት ሳይሆን፣ ወደ ላቀ ደረጃ የምናድግበት መለኮታዊ አጋጣሚ ነው።

መግቢያ

ህይወት ባልተጠበቁ ፈተናዎችና ችግሮች የተሞላች ናት። አንዳንዴ የሚገጥሙን ጉዳዮች እንደ ከባድ ሸክም ሆነው መንገዳችንን ይዘጋሉ። ነገርግን ኢስላም ኮምጣጣውን ሎሚ ወደ ጣፋጭ መጠጥ የመቀየር ጥበብን ያስተምረናል። ይህ ጽሑፍ ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ መቀየር ስለሚቻልበት አስደናቂ የኢስላም አስተምህሮ ይዳስሳል።

አስተዋይ ሰው መከራን ወደ በረከት ፣ ፈተናን ደግሞ ወደ ትምህርት እንዴት እንደሚለውጥ ከታላቁ ነብያችን (ﷺ) እና ከቀደምት ደጋግ ምሁራን ህይወት ተሞክሮዎችን በመቀመር እናያለን። ይህ የጽናት ፣ የተስፋና የአላህ ውሳኔን በጥበብ የመቀበል ጉዞ ነው፤ ይቀላቀሉን።

ችግር ወይስ አጋጣሚ? የአመለካከት ለውጥ

ኮምጣጣውን ሎሚ ወደ ጣፋጭ መጠጥ ቀይረው፡፡ ችግሮችህን ወደ መልካም አጋጣሚን ቀይራቸው፡፡

ብዙ ጊዜ በህይወታችን ውስጥ ችግሮችና ፈተናዎች ያጋጥሙናል፡፡ ከባድ ሸክም ሆነውም ይታዩናል።

በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙን ፈተናዎች በራሳቸው ጥሩ ወይም መጥፎ አይደሉም፤ ትርጉም የሚሰጣቸው እኛ የምንቀበልበት መንገድ ነው።

ኢስላም የሚያስተምረን ቁልፍ ጥበብም ይሄ ነው፤ ችግሮችን እንደ እንቅፋት ሳይሆን እንደ እድገት አጋጣሚ ማየት።

አስተዋይ ምእመን መከራን ወደ በረከት ፣ ህመምን ደግሞ ወደ ጥንካሬ ይለውጣል። ከመከራውም ጠቃሚ ትምህርት ይወስዳል።

ታላቁ ተምሳሌት ፡ ከስደት ወደ ህንጸተ-ሀገር

ምርጡ የሰው ልጅ አርአያ የሆኑት የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ተመልከቱ። የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ከተወለዱባትና ካደጉባት ውዷ ከተማቸው መካ እንዲወጡ ሲገደዱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘንና ህመም እስቲ ለአፍታ እናስበው።

ይህ በወቅቱ ትልቅ ሽንፈትና መከራ መስሎ ሊታይ ይችላል። ነገር ግን እርሳቸው በጽናትና በትዕግስት (ሰብር) በኢስላም አስተምህሮ መሰረት የአላህን ውሳኔ ተቀበሉ።

ውጤቱስ ምን ሆነ? አሏህም በነብዩ ከተማ (በመዲና) አዲስ መኖሪያን አደረገ፤ ሁኔታዎችን ለዋወጠላቸው። ዝናው የታሪክን መስሚያና ማያ ያጣበበ ሐገር መሰረቱ፡፡

ይህች የነብዩ ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ በሙስሊሞች ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ ይዛ ትገኛለች። መከራው ወደ ታላቅ በረከት ተቀየረ።

ከእስር ቤት የወጡ ብርቅዬ ምሁራን

በድሮ ጊዜ የነበሩ ደጋግ የአሏህ ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ከባድ ችግሮችን ተጋፍጠዋል። በርካታ ኡለማዎች (ምሁራን) ታስረዋል ፣ ከፊሎቹም ከሐገራቸው ተባረዋል፡፡

እንዲሁም ከእነሱ ውስጥ ተገርፈዋል፤ የከፋ እንግልትና ስቃይ ደርሶባቸዋል። ነገርግን ይህ የገጠማቸው በደል ይበልጥ እንዲጠነክሩ አደረጋቸው፡፡

ከእስር ቤት ሲወጡም ይበልጥ ፅኑ ፣ ቁርጠኛ ፣ ጠንካራና ውጤታማ ሆነው ወጡ። በእስር ቤት ጨለማ ውስጥ ሆነው የኢስላምን ድንቅ የዕውቀት ብርሃን የፈነጠቁ ኪታቦችን ጽፈዋል።

የደረሰባቸው በደል ይበልጥ ጽኑ ፣ ቁርጠኛ እና ውጤታማ እንዲሆኑ አደረጋቸው። ፈተናው ለነሱ የእውቀትና የጥበብ መፍለቂያ ሆነ።

የምእመን አስደናቂው ቀመር፡ ሁሉም ነገር መልካም ነው

ችግር ሲያጋጥምህ ጽና፤ ብሩህ ጎኑን ተመልከት። በአንድ ሙዕሚን ሰው ህይወት ውስጥ ፍፁም የሆነ ክፉ ነገር የለምና። ይልቁንም በእያንዳንዱ ውሳኔና ሁኔታ ውስጥ ጥበብንና መልካም ነገርን ታገኛለህ።

ለምንድነው በምእመን ህይወት ውስጥ እያንዳንዱ ክስተት ወደ መልካም ነገር የሚቀየረው? ምክንያቱም አማኝ እያንዳንዱን ክስተት ከአላህ ጥበብ ጋር ያገናኘዋል። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

አል-ቁርአን

(ሱረቱል በቀራ 216)

“…ለናንተ የተሻለ ሆኖ ሳለ አንድን ነገር ትጠላላችሁ፤ ለናንተም መጥፎ ሆኖ ሳለ አንድን ነገር ትወዳላችሁ። አላህ ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም።”

ይህንን መለኮታዊ መርህ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) በሚከተለው ውብ ሐዲሳቸው አብራርተውታል፦

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“የምእመን ነገር ሁሉ ይገርማል! ነገሩ ሁሉ ለእሱ መልካም ነው። ደስታ ሲያገኘው ያመሰግናል፤ በዚህም ለእሱ መልካም ይሆንለታል። ችግር ሲደርስበት ይታገሳል፤ በዚህም ለእሱ መልካም ይሆንለታል። ይህ ከምእመን በስተቀር ለማንም አይደለም።”

አንድ የከበረ ድንጋይ ዋጋውን የሚያገኘው በሚያጠራውና በሚያፀዳው ታላቅ ሙቀት ውስጥ ካለፈ በኋላ መሆኑን አስታውስ።

ልክ እንደዚሁ ስኬት የሚገኘው በችግርና በውድቀት ከተፈተኑ በኋላ ነው። አዎንታዊ ሁን፤ እንቅፋቶችን ወደ ሃይል ምንጭነት ቀይር፤ በህይወትህ ውስጥ ከተለያዩ ሁኔታዎች ትምህርቶችን ውሰድ። ታጋሽ ሁን፤ ጉዞህንም ቀጥል!

ማጠቃለያ

ኢስላም ችግሮችን እንደ መጨረሻ ሳይሆን እንደ አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ እንድናይ ያስተምረናል። ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ መቀየር ይኖርብሃል፡፡

እያንዳንዱ ፈተና በትዕግስት እና በጥበብ ከተጋፈጥነው ፣ ለስብዕና እድገታችን ፣ ለኢማናችን ጥንካሬ እና ወደ አላህ ለመቃረብ ታላቅ አጋጣሚ ይሆናል።

የመከራን ገጽታ የሚወስነው የገጠመን ነገር ሳይሆን እኛ የምንሰጠው ምላሽ ነው። ስለዚህ ሁሌም በአላህ እዝነት ላይ ተስፋ በማድረግ መከራን ወደ ድል እንቀይር።

እርስዎስ በህይወትዎ ያጋጠመዎትን ከባድ ችግር ወደ መልካም አጋጣሚ የቀየሩበት አጋጣሚ አለ? ተሞክሮዎን ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ላይ በማካፈል ሌሎችን ያነሳሱ።

Related posts

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share