ሙስሊሟ እህቴ ለባልሽ ታዛዥ ሁኝ

Author picture
ሴት ልጅ ከእናት አባቷ ቤት ከወጣችበት እለት አንስቶ በባል ቃልኪዳን ውስጥ ትገባለች። እስልምና ባል ለሚስቱ የሚያስፈልጋትን ሁሉ እንዲያሟላላት ሲያዘው፤ እሷን ደግሞ ለባሏ ታዛዥ እንድትሆን ያዛታል።
ሙስሊሟ እህቴ ለባልሽ ታዛዥ ሁኝ

ሙስሊሟ እህቴ ለባልሽ ታዛዥ ሁኝ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

የአሏህ ሰላምና እዝነት በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመልቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

ሴት ልጅ ከእናት አባቷ ቤት ከወጣችበት እለት አንስቶ በባል ቃልኪዳን ውስጥ ትገባለች። እስልምና ባል ለሚስቱ የሚያስፈልጋትን ሁሉ እንዲያሟላላት ሲያዘው፤ እሷን ደግሞ ለርሱ ታዛዥ እንድትሆን ያዛታል።

ይህ ማለት ደግሞ ስብዕናዋን አጥታ ፣ መብቷን ተነጥቃ ዝቅ ትበል ማለት አይደለም። እራስን በባል ስር በማድረግ ታዛዥ መሆን ማለት እንጂ መጨቆን ወይም ሃሳብን በነፃነት አለመግለፅ ማለት አይደለም።

ይልቁንስ ረዳት በመሆን ሃሳቧን ፣ አስተያየቷን እና ስሜቷን ለባሏ ማካፈል ማለት ነው። እንዲያውም ብልህ ወንድ ማለት በራሱ ሃሳብ ብቻ ተደግፎ የመጨረሻ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት የሚስቱን ሃሳብና አስተያየት የሚጠይቅ ነው።

ከመብት ጋር በተያያዘ በዘመናችን በርካታ ቤተሰቦች እሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች አሉ እነሱም:- ሴት የወንድ ረዳት አይደለችም ፣ የራሷ ነፃነት እና መብት ያላትናት ፣ የቤት ስራ የሴት የወንድ እየተባለ መለየት የለበትም ወ.ዘ.ተ የሚሉ ናቸው።

ነገር ግን ለአንድ ሙስሊም ሴት ትክክለኛ ክብር እና መብት ኢስላም ከሰጣት ውጭ የሚያስከብራት የለም። የሚገርመው ሴቶች እህቶቻችን ባሎታቻቸውን ሲሰድቡ፤ በአመፅ ቤታቸውን ሲንዱ በአሏህ (ሱ.ወ.ተ) ላይ እያመፁ መሆኑን አለመረዳታቸው ነው።

አንዲት ሙእሚን ሴት እራሷን በባሏ ስር በማድረግ ታዛዥ እምትሆነው ባሏ የሚወዳትና የሚጠነቀቅላት ጥሩ ባል በመሆኑ ነው።

ሌላው ቀርቶ ፅኑና ደስተኛ የቤተሰብ ፍቅርን መስርታ መኖርን የምትሻ ሴት የባህሪ ችግር ያለባት ቢሆንም እንኳ እራሷን በባሏ ስር ማድረጓን እና ታዛዥ መሆኗን አትተውም፤ ምክኒያቱም የባል ሐቅ ምን እንደሆነ የተረዳች ናትና።

ለባሏ ታዛዥ እማትሆን ጨቅጫቃ ሚስት ግን የባሏን ባህሪ ችክ የሚልና በቀላሉ የሚበሳጭ እንዲሆን ታረገዋለች።

እንግዲህ አንዲት ሙስሊም ሴት በባሏም ሆነ በአሏህ ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን የባሏን የቤት አስተዳዳሪ ሃላፊነት ተቀብላ ለባሏ ታዛዥ መሆን ይኖርባታል። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

‹‹አንድን ሰው ከአሏህ ሌላ ላለ እንዲሰግድ ባዝ ኖሮ ሴትን ለባሏ እንድትሰግድ አዛት ነበር አሉ፤ በመቀጠልም በዚያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ ሴት የጌታዋን ሐቅ አታደርስም የባሏን መብት እስካልፈፀመች ድረስ›› ብለዋል።

ይህ ሐዲስ እኛ ሴቶች ምን ያህል የባሎቻችንን ሐቅ መጠበቅ እንዳለብን እና ይህ ካላደረግን የከፋ ቅጣት እንደሚጠብቀን በሚገባ ይጠቁመናል። ስለዚህ እህቶቼ ይህንን አውቀን ተወዳጅ እና የባልን ሐቅ ጠባቂ እንሁን።

አሏህ ላላገባን ጥሩ ትዳርን፤ ላገባችሁ ደግሞ የተባረክ ትዳር ያድርግላችሁ። አሚን!

Related posts

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

አደም (ዐ.ሰ) ከተፈጠሩ በኋላ የተሰጣቸው የመጀመሪያው ትምህርት የስሞች ዕውቀት ነበር። ይህም ከመላእክት የላቀ ደረጃ እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መላእክትም ለእርሳቸው ሱጁድ እንዲያደርጉ (እንዲሰግዱ) ምክንያት ሆኗል። ምንም

Read More »
ወሲባዊ ግንኙነት በእስልምና እይታ

ወሲባዊ ግንኙነት በእስልምና እይታ

እስልምና ወሲባዊ ግንኙነት ሊታፈን የማይገባው እንደሆነና በተገቢው መንገድ ሊረካ የሚገባ አስፈላጊ የሰው ልጅ ፍላጎት እንደሆነ ያስተምራል። ወሲባዊ ግንኙነት እንደ ቀላል ነገር የሚታይ  አይደለም፤ እንዲሁም አንድ

Read More »

የልጆች መብት በእስልምና

የልጆች መብት በእስልምና በሚለው ትምህርት ውስጥ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸውን መብት ትማራላችሁ። ልጆችን በማሳደግ ዙሪያ ከሸሪአ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ነገሮችን ታውቃላችሁ።

Read More »

የጋብቻ ጥያቄ አደቦች (ስነ-ስርአቶች)

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ጋብቻ ጥያቄ ፅንሰ ሃሳብ እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስነ-ስርአቶችን ትማራላችሁ። በእስልምና ውስጥ የጋብቻ ጥያቄን ሲያቀርቡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶችን ታውቃላችሁ።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share