Table of Contents

ክፍል ሁለት

ኸድጇ (ረ.ዐ) በረካን እየተመለከተች በረካ ሆይ! ለሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ስትይ ወጣትነትሽን መስዋዕት አደረግሽ አሁን ደግሞ እሱ ሊክስሽ ይወዳል። ለሱም ለኔም ስትይ እርጅና ሳይጫጫንሽ አግቢ ትላታለች።

በረካም ማንነው የማገባው እመቤቴ? ስትል ትጠይቃታለች። ከኸዝረጅ ጐሳ የሆነ ኡበይድ ኢብን ዘይድ ለጋብቻ ፈልጐሽ ወደኛ መቶ ነበር። ለእኔስትይ እምቢ አትበይኝ?

በረካ ተስማምታ ኡበይድ ኢብን ዘይድን አገባች። ከእርሱም ጋር ወደ ያስሪብ ሄዳ እዚያው ልጅ ወለደች፤ ልጇንም አይመን ስትል ጠራችው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኡሙ አይመን (የአይመን እናት) እየተባለች ትጠራለች።

ባሏ ሲሞትባት ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ለመኖር ወደ መካ ሄደች። ከኸድጃ ቤት በረካን ጨምሮ አሊ ኢብን አቢጧሊብ እና ዘይድ ኢብን ሐሪሳ ነበሩ።

አንድ ቀን ምሽት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ዘወትር ሶኻባዎቻቸውን ሰብስበው ወደ ሚያስተምሩበት የሚወስደውን ምንገድ ሙሽሪኮች ዘጉት።

በዚህ ወቅት ኸድጃ ለረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አስቸኳይ መልዕክት ስለነበራት በረካ ህይወቷን መስዋዕት አድርጋ ከተሰባሰቡበት ቦታ ለመድረስ ሞከረች። በደረሰች ጊዜ መልዕክቱን ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አደረሰች።

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ፈገግ አሉና እንዲህ አሏት:- የአይመን እናት ሆይ! አንች የተባረክሽ ነሽ በእርግጥም በጀነት ቦታ አለሽ አሏት። ኡሙ አይመን በሄደች ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱኻባዎቹን ተመለከቱና ከጀነት የሆነችን ሴት ከእናንተ መካከል ማግባት የሚሻ አለን? ኡሙ አይመንን ያግባ አሉ።

ሁሉም ሱሃባዎች ፀጥ አሉ። አንዲትን ቃል እንኴ ትንፍሽ አላሉም። በጊዜው ኡሙ አይመን ወጣት ያልነበረች ሲሆን ውበቷ ጠውልጓል። በዚህ ወቅት 50 ዓመቷ ነበር።

ነገር ግን ዘይድ ኢብን አልሐሪሳ ወደ ፊት መጣ አለና የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እኔ ኡሙ አይመንን አገባታለሁ። በአሏህ ይሁንብኝ! ግርማሞገስና ውበት ካላት ሴት በላጭ ናት አለ።

ዘይድና ኡሙ አይመን ተጋብተው ልጅ ወለዱ፤ ልጃቸውንም ኡሳማ አሉት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ ልጃቸው ይወዱታል። ኡሳማ በወጣትነት ጊዜው እራሱን ለኢስላም ማገልገል ጀመረ። ብኋላ ላይ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከባድ ሃላፊነት ሰጡት።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ሲሰደዱ ኡሙ-አይመን ቤታቸውን እንድትቆጣጠርላቸው እዛው መካ ትተዋት ሄዱ። በመጨረሻ ላይ ግን በራሷ ወደ መዲና ተሰደደች። በዛ በረሃማና ተራራማ መሬት ረጅም እና አስቸጋሪ የሆነ ጉዞ በእግሯ ተጓዘች።

ሙቀቱ በጣም የሚያቃጥል ሲሆን አሸዋ ይዞ የሚነፍሰው ንፋስ መንገዱን ይጋርድባት ነበር። ነገርግን ለሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከነበራት ጥልቅ ፍቅር ምክኒያት ፀጥንታ ጉዞዋን ቀጠለች። መዲና ስትደርስ እግሮቿ አብጠውና ቆስለው፤ ፊቷ በአሸዋና በአፈር ተሸፍኖ ነበር።

ኡሙ አይመን ሆይ! እናቴ ሆይ! በእርግጥም በጀነት ቦታ አለሽ አሏት። አይኖቿን እና ፊቷን ጠረጉላት፤ እግሮቿን እና ትካሻዋንም አሻሿት።

በረካ በተለያዩ ዘመቻዎችና ጦርነቶች ተሳትፋለች። ለምሳሌ:- በኡኹድ ውሃ ለተጠሙት ውሃ ታከፋፍላለች፤ የቆሰሉትንም ትጠብቃለች። በኸይበር እና በኹነይን ዘመቻ ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) አጅባለች። ልጇ አይመን የተገደለው በኹነይን ዘመቻ ነበር።

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከሞቱ ቡኋላ ከበረካ አይኖች እንባ አይጠፋም ነበር። አንዴ ለምንድ ነው የምታለቅሽው ተብላ ተጠይቃ በአሏህ ይሁንብኝ የአሏህ መልዕክተኛ እንደሚሞቱ አውቃለሁ ነገርግን የማለቅሰው ወህዩ ስለተቋረጠብን ነው ስትል መለሰች።

በረካ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ እስከሞቱበት ጊዜ ድረስ ከጐናቸው ነበረች። ለእስልምና ሃይማኖት የነበራት ፍቅር እጅግ በጣም ጠንካራ ሲሆን የሞተችው በኸሊፋው ኡስማን ዘመን ነበር።

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top