ህይወትህን እንዳለች ተቀበላት! ይህ ነው የዱንያ ሁኔታ ወደ ጣፋጭ ነገሮች ታመራለች፤ ችግሮቿ ብዙ ናቸው፤ ገፅታዋ ያስበረግጋል፤ ሁሌም ትቀየራለች፤ ጠራች ሲባል ትደፈርሳለች፤ ከጭንቀት ጋር ተቀላቅላለች ሁሌም ታስተክዛለች።
አንድም ልጅ ሆነ ፣ ሚስት ፣ ጓደኛ ፣ የተከበረ ሰው ፣ ቤት ወይም ስራ አታገኝም የማያስደስት አንዳንዴም የሚያስከፋ ነገር ቢኖርበት እንጂ። ስለዚህ የመጥፎነቱን ግለት በጥሩ ጎኑ ቅዝቃዜ አብርደው።
አሏህ ይህች ህይወት ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ፣ ቡድኖችን ፣ ሃሳቦችን ፣ መልካምና መጥፎ፤ ጥሩና ብልሹ እንዲሁም ደስታና ሀዘን እንዲኖራት ፈለገ። ከዚያም ጀነት ውስጥ መልካም ሁሉ ያለ ተቃራኒው ደስታን ጨምሮ ይኖራል። ተንኮል ፣ ጥፋትና ሃዘን ደግሞ እሳት ውስጥ ይሰባሰባሉ። በሐዲስም ውስጥ:-
«ዱንያ እርጉም ነች በውስጧ ያለውም ሁሉ የተረገመ ነው። አሏህን ማውሳትና የመሳሰሉት እንዲሁም አዋቂ እና የእውቀት ፈላጊዎች ሲቀሩ።»
ስለዚህ ህይወትህን እንዳለች ኑራት፤ በምናቡም አለም ውስጥ አትንሳፈፍ። ዱንያህን እንዳለች ተቀበላት። ትኖርባትና ትረጋጋባት ዘንድ ራስህን አሳምን።
እንደምትፈልገው በዚህች ህይወት ጓደኛ ከችግር አይጠራልህም፤ ጉዳዮችም አይሟሉልህም ምክኒያቱም ጥራት ፣ ሙሉዕነትና ፍፁምነት መገለጫዋ አይደሉምና። ሚስትህ እንደምትፈልገው ላትሆንልህ ትችላለች። በሐዲስም:-
«አንድ አማኝ ከሚስቱ አይሽሽ ፤ አንድ ባህሪይ ቢጠላባት ሌላ ይወድላታልና»
ስለዚህ ትክክለኛ ለመሆን መጣር ይጠበቅብናል። ይቅርልንል ፣ የተገኘውን ልንቀበል ፣ የቸገረንን ልንተው ፣ አንዳንዴ እንዳላየን ልንሆን ፣ ጥፋቶችን ልናርምና አንዳንድ ነገሮችን እንዳላወቅን መሆን የግድ ይለናል።
Share