ሐውድ በፍርዱ ቀን የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተከታዮች የሚመጡበት ግዙፍ ሸለቆ ሲሆን የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መንገድ ያልተከተሉና በእስልምና ሃይማኖት ፈጠራን ያስተዋወቁ ሲቀሩ። በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐውድን ሲገልፁት እንዲህ ብለው ነበር።
“የኔ ሐውድ በጣም ትልቅ ነው። እሱን ለመሻገር የወር ጉዞ ይወስዳል። ውሃው ከወተት በላይ የነጣ ፣ ሽታው ከሚስክ በላይ የሚጣፍጥ ፣ መጠጫ ዋንጫዎቹ ልክ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዙ ናቸው። ከእሱ የጠጣ ሰው ፈፅሞ ድጋሚ አይጠማውም።” (ቡኻሪ)
እንዲህም ብለዋል፡-
“ሐውድ ላይ ቀዳሚያችሁ ነኝ። አንዳንዳቸው እስካያቸው ድረስ ከፊት ለፊቴ ይመጣሉ። እናም ከእኔ አርቀው ይወሰዳሉ። ጌታየ ሆይ! የኔ ሐዋሪያዎች ናቸው እላለሁ። ከአንተ ቡኋላ በሐይማኖቱ ላይ ስለ ፈጠሩት ፈጠራ (ቢድአ) አታውቅም እባላለሁ።” (ቡኻሪ)
በሌላ ዘገባ እንዲህ ብለዋል፡ “ከእናንተ መካከል ማን ወደ እኔ እንደሚመጣ ላይ ሐድው ላይ እቆማለሁ። አንዳንድ ሰዎች ከእኔ ርቀው ይወሰዳሉ። ጌታየ ሆይ! ከእኔ ናቸው፤ ተከታዮቼ እላለሁ። ከአንተ ቡኋላ የሰሩትን አይተሃልን? እባላለሁ። በአሏህ ይሁንብኝ በተረከዞቻቸው ዞረዋል (ሃይማኖታቸውን ትተዋል)።” (ቡኻሪ)
የውመል ቂያማን እና ቢድአን ተመልከቱ