Table of Contents

የአድ ህዝቦች በደቡባዊ አረብያ ከኦማን የአረቢያ ባህረሰላጤ እስከ የመን ሐድራሙት ደቡባዊ የቀይ ባህር ጫፍ ድረስ ባለው በጣም ሰፊ ሐገር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ህዝቦች ናቸው። ጡንቻቸው የፈረጠመ እና ድንቅ የግንባታ ጥበብ የነበራቸው ሰዎች ናቸው።

በሃብታቸው እና በሃይላቸው የተመኩ ፣ በዚህም ምክኒያት የአሏህን ምልክቶች የካዱ በጣም እብሪተኞች ነበሩ። በእርግጥ የጣኦት አምልኮ በጣም ተጋብቶባቸው ስለነበር የነብዩ ሑድ (   ) አስተምህሮት እና ቅን ምክር መቀበል አልቻሉም ነበር።

አሏህን ብቻ እንዲያመልኩና የጣኦቶችን አምልኮ እንዲተው ሑድ ያስጠነቅቃቸው ነበር። አሏህ በእነሱ ላይ ያደረገው አያሌ ችሮታ አስታወሳቸው።

ከእነሱ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይፈልግ እና ከእነሱ የሚፈልገው አሏህ እሱን በላከው ነገር ላይ እውነቱን እንዲቀበሉ መሆኑን ግልፅ አደረገላቸው። በእብሪት መልዕክቱን ውድቅ አደረጉ። እንዲያውም እነኳ ቀለዱ ተሳለቁበት፤ እሱማ እብድ ነው አሉም።

እንዲህም አሉ፡ ሁድ ሆይ! ማስረጃ አላመጣህልነም፤ ለማይረባ ንግግርህ ጣኦቶቻችነን አንተውም። እኛ በአንተ አማኞች አይደለንም። ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በእብደት ልክፍት ይዘውሃል እንጅ ሌላን አንልም። (አል-ቁርአን 11፡53-54)

አመታት እንዳለፉ በነብያቸው መልዕክት ላይ የበለጠ በጣም እብሪተኛ ፣ ግትር እና እምቢተኛ ሆኑ። ሑድ (    ) በአምልኮ ከአሏህ ጋር ከሚያጋሩት ነገር ሁሉ የጠራ መሆኑን አወጀ። ለእነሱ የሚያስፈራ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረውም።

ብትሸሹ እንኳ ለእናንተ የተላኩበትን (መልዕክት) አድርሻለሁ። ጌታየ ሌሎች ህዝቦች እንዲተኳችሁ ያደርጋል። ምንም ነገር አትጎዱትም። በእርግጥ ጌታየ በሁሉም ነገር ላይ ጠባቂ ነው።  (አል-ቁርአን 11፡57)

እናም ተዋቸው፤ በአሏህ ላይ ብቻ መመካትን አረጋገጠላቸው። የአሏህ ቅጣት በከሃዲ ህዝቦቹ ላይ እንደሚመጣባቸው እርግጠኛ ነበሩ።

ሑድ እና ህዝቦቹ የአሏህን ቃልኪዳን ጠበቁ። ከባድ ድርቅ በሁሉም አካባቢ በተከሰተ ጊዜ በንሰሃ ወደ እሱ እንዲመለሱ አስጠነቀቃቸው። ሆኖም ከጌታቸው ምህረት ከሰማይ ዝናብ እንደሚወርድላቸው ፣ ከጥንካሬያቸው ላይ ጥንካሬ እንደሚሰጣቸው ነገራቸው።

ነገርግን አፌዙበት፤ ውሸታም ሲሉ ኮነኑት። ድርቁ ሰብላቸውን አጠፋባቸው። ሁሉም ስለ ዝናብ ይበልጥ ተስፋ እንዲቆርጡ አደረጋቸው።

ዝናብ እንዲጥልላቸው ፈለጉ፤ ወደ አካባቢያቸው ደመና ሲመጣ ፣ ኮረብታዎችን ሲያለብስ ፣ አድማሱ ሲጠቁር ደስ አላቸው ፈነጠዙ። የመስኖ ግድቦቻቸው እንደሚሞሉ ፣ ማሳቸው ለምለም እና ወቅታቸው ፍሬያማ እንደሚሆን አሰቡ።

ነገርግን የተከሰተው ተስፋ ያደረጉበት ነገር አልነበረም።

ቅጣቱ በድንገት መጣ። አቧራ እና አሸዋ የቀላቀለ እጅግ ከባድ ነፋስ ቀያቸውን አናወጠው። ያገኘውን ሁሉ አጠፋባቸው። አሏህ ቁጣውን ለሰባት ተከታታይ ሌሊትና ለስምንት ተታታይ ቀን በእነሱ ላይ አደረገ።

አድ በሃይል በምትንሿሿ ንፋስ ጠፉ 7 ተከታታይ በሆኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት ቀናቶች ቁጣውን በእነሱ ላይ አደረገ። እናም ልክ ግንዱ ክፍት እንደሆነና ተገንድሰው እንደተጣሉ የዘንባበ ዛፍ ተገልብጠው በመንገዱ ታያቸዋለህ።

(አል-ቁርአን 69፡6-7)

የቤቶቻቸው ፍርስራሽ እንጅ ሌላ ምንም ነገር እስከማይታይ ድረስ ጠፍተዋል።

ሑድ (  ) እና ተከታዮቹ ብቻ ተረፉ። አሏህን በሰላም ወደ ሚያመልኩበትም ሐድራሙት ሄዱ።

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top