በ ቀዷ እና ቀደር ማመን በህይወት ፈተናዎች ውስጥ ሰላምን ያመጣል። በዚህ ጽሁፍ የአሏህን ውሳኔ የመቀበልን አስፈላጊነትና የመከራን ጥቅም ይረዳሉ። ህሊናዎን አረጋግተው በነፍስዎ ሰላምን ያግኙ።

በምድርም ሆነ በነፍሶቻችሁ ላይ ምንም መከራ አይገጥማችሁም፤ ከመከሰቱ በፊት በመፅሐፍ ውስጥ የተፃፈ ቢሆን እንጂ። ብዕሩ ደርቋል ፣ መዝገቡም ተነስቷል ፣ ጉዳዩም ተፈፀመ፤ ውሳኔዎችም ሁሉ ተፅፈዋል፤ አሏህ የፃፈልን እንጂ አይነካንም።

የሳተህ ነገር አያገኝህም ነበር ያገኘህም አይስትህም ነበር።

ይህ እምነት በነፍስህ ውስጥ ከፀና እና በህሊናህ ውስጥ ከተደላደለ መከራዎች ሁሉ ስጦታ ፣ ፈተናዎች ሁሉ ሽልማቶችና ኒሻኖች ይሆኑልሃል። አሏህ ኸይር ያሻለትን ሰው ይፈትነዋል።

ታመምኩ ፣ ልጄ ሞተ ብለህ አትጨነቅ። ከሰርኩ ፣ ቤቴ ተቃጠለ ብለህም አትረበሽ። ፈጣሪህ ወስኗል፤ ውሳኔውም ተፈፀመ። ምርጫውም እንዲህ ነው።

የሚሻለውም አሏህ የመረጠው ነው። ምንዳውም ተገኘ ፤ ወንጀሉም ተማረ።

የምስራች መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች……. መታገሳቸው እና ሰጭና ተቀባይ ፣ ሰብሳቢ ፣ የሚዘረጋና ስለሚሰራው የማይጠይቅ ፍጡሮቹ ግን የሚጠይቁ የሆነው ጌታቸው የመረጠላቸውን በደስታ በመቀበላቸው ደስ ይበላቸው።

ህሊናህ አያርፍም፤ ነፍስህም አትረጋም፤ የልብህ ጉትጎታም አይሰክንም በቀዷ እና ቀደር እስካላመንክ ድረስ።

የምታገኘውንና የሚያጋጥምህን ሁሉ የተፃፈበት የቀደር ብዕር ደረቀ ፤ ስለዚህ በቁጭት ራስህን አትጉዳ። ግድግዳው እንዳይፈርስ መከላከል እችል ነበር ብለህ አታስብ።

ውሃው እንዳይፈስ ፣ ነፋስም እንዳይነፍስ ፣ ብርጭቆውም እንዳይሰበር መከላከል ትችል እንደነበር እራስህን አትሸንግል።

ይሄ ብፈልግም ብትፈልግም ፣ ባልፈልግም ባትፈልግም ከቁጥጥራችን ውጭ ነው። የተወሰነው ነገር ይከሰታል ፤ የተፃፈውም ተግባራዊ ይሆናል።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ካህፍ 18:29)

«የሻም ሰው ይመን የሻም ይካድ»

የቁጣ ፣ የዋይታና ራስን የመውቀስ ወታደሮች ሳይከቡህ በፊት ለቀደር እጅህን ስጥ። የቁጭት ጎርፍ ሳያጥለቀልቅህ በፊት ለቀደር እውቅና ስጥ።

ስለዚህ ነገሮች እንዲሳኩልህ ምክኒያቶቹን ከፈፀምክና ዘዴዎችን ከተጠቀምክ በኋላ ግን ደግም ትጠነቀቀው የነበረውን ነገር ቢመጣብህ መሆን የነበረበትና መከሰት የነበረበት እሱ ነውና ራስህን አረጋጋ።

«እኔኮ እንዲህና እንዲህ ባደርግ እንዲህና እንዲህ ይሆን ነበር» አትበል ፤ ባይሆን «አሏህ ወሰነ ያሻውንም ፈፀመ» በል።

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share